ወደ ቲቶ 1

AMHEVGአማርኛ14 ጥቅሶች2:22 አዳምጥ
አዳምጥ 2:22 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1የእግዚአብሔር ባሪያና የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ የሆነ ጳውሎስ፥ በእግዚአብሔር ለተመረጡት እምነት እንዲሆንላቸው በዘላለምም ሕይወት ተስፋ እንደ አምልኮት ያለውን እውነት እንዲያውቁ የተላከ፤ ስለዚህም ሕይወት የማይዋሽ እግዚአብሔር ከዘላለም ዘመናት በፊት ተስፋ ሰጠ፥

3በዘመኑም ጊዜ፥ መድኃኒታችን እግዚአብሔር እንዳዘዘ፥ ለእኔ አደራ በተሰጠኝ ስብከት ቃሉን ገለጠ፤

4በሃይማኖት ኅብረት እውነተኛ ልጄ ለሚሆን ለቲቶ፤ ከእግዚአብሔር አብ ከመድኃኒታችንም ከጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ምሕረት ሰላምም ይሁን።

5ስለዚህ ምክንያት የቀረውን እንድታደራጅ በየከተማውም፥ እኔ አንተን እንዳዘዝሁ፥ ሽማግሌዎችን እንድትሾም በቀርጤስ ተውሁህ፤

6የማይነቀፍና የአንዲት ሚስት ባል የሚሆን፥ የሚያምኑም ልጆች ያሉት፥ ስለ መዳራትም ወይም ስለ አለመታዘዝ የማይከሰስ ማንም ቢኖር፥ ሹመው።

7ኤጲስ ቆጶስ፥ እንደ እግዚአብሔር መጋቢ፥ የማይነቀፍ ሊሆን ይገባዋልና፤ የማይኮራ፥ የማይቆጣ፥ የማይሰክር፥ የማይጨቃጨቅ፥ ነውረኛ ረብ የማይወድ፥

8ነገር ግን እንግዳ ተቀባይ፥ በጎ የሆነውን ነገር የሚወድ፥ ጠንቃቃ፥ ጻድቅ፥ ቅዱስ፥ ራሱን የሚገዛ ይሁን፤

9ሕይወት በሚገኝበት ትምህርት ደግሞ ሊመክር ተቃዋሚዎቹንም ሊወቅስ ይችል ዘንድ፥ እንደተማረው በታመነ ቃል ይጽና።

10የማይታዘዙና ከንቱ የሚናገሩ የሚያታልሉ ይልቁንም ከተገረዙት ወገን የሚሆኑ ብዙ ናቸውና፤

11እነዚህም ስለ ነውረኛ ረብ የማይገባውን እያስተማሩ ቤቶችን በሞላው ስለ ሚገለብጡ፥ አፋቸውን መዝጋት ይገባል።

12የገዛ ራሳቸው ነቢይ የሆነ ከእነርሱ አንዱ፦ “የቀርጤስ ሰዎች ዘወትር ውሸተኞች፥ ክፉዎች አራዊት፥ በላተኞች፥ ሥራ ፈቶች ናቸው፡” ብሎአል።

13ይህ ምስክር እውነተኛ ነው። ስለዚህ ምክንያት የአይሁድን ተረትና ከእውነት ፈቀቅ የሚሉትን ሰዎች ትእዛዝ ሳያዳምጡ፥ በሃይማኖት ጤናሞች እንዲሆኑ በብርቱ ውቀሳቸው።

15ሁሉ ለንጹሖች ንጹሕ ነው፤ ለርኵሳንና ለማያምኑ ግን ንጹሕ የሆነ ምንም የለም፥ ነገር ግን አእምሮአቸውም ሕሊናቸውም ረክሶአል።

16እግዚአብሔርን እንዲያውቁ በግልጥ ይናገራሉ፥ ዳሩ ግን የሚያስጸይፉና የማይታዘዙ ለበጎ ሥራም ሁሉ የማይበቁ ስለ ሆኑ፥ በሥራቸው ይክዱታል።

ማብራሪያ

፩፥፩-፬ የኃጢአትና የሰይጣን ባሪያዎች ያልሆኑ ሁሉ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ናቸው። ሁሉም የወንጌል እውነት እግዚአብሔርን ከመምሰል ጋር የሚስማማና እግዚአብሔርን መፍራትን የሚያስተምር ነው። የወንጌል ዓላማ ተስፋንና እምነትን ከፍ ማድረግ፤ አእምሮንና ልብን ከዓለም ማስወገድ፤ ወደ ሰማይና ወደ ላይ ወዳሉት ነገሮች ከፍ ማድረግ ነው። እንግዲህ ወንጌል ምን ያህል ግሩም ነው! ከጥንት ጀምሮ የመለኮታዊ የተስፋ ቃል ርዕስ የነበረው ሲሆን፤ ስለ ልዩ መብቶቻችንም ምን ያህል ምስጋና ይገባናል! እምነት ከመስማት ይመጣል፤ መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው። የተሾመና የተጠራም ሁሉ ቃሉን መስበክ አለበት። ጸጋ የእግዚአብሔር ነፃ ሞገስና በእርሱ ዘንድ ያለን ተቀባይነት ነው። ምሕረት ደግሞ የሞገሱ ፍሬዎች ሲሆን በኃጢአት ስርየትና በዚህም ሆነ ከዚያ በኋላ ካሉ ሁሉ መከራዎች ነፃ መውጣት ነው። ሰላምም የምሕረት ውጤትና ፍሬ ነው። ሰላማችን በሆነው በክርስቶስ በኩል ከእግዚአብሔር ጋር፤ ከፍጥረታትና ከራሳችን ጋርም ሰላም ነው። ጸጋ የሁሉም በረከቶች ምንጭ ነው። ምሕረት፣ ሰላም፣ መልካም ነገር ሁሉ ከዚህ ይፈልቃል።

1:5-9 ፓስተሮች፣ በዚህ ስፍራ ሽማግሌዎችና ኤጲስ ቆጶሳት ተብለው የተጠሩት፣ ባሕርያቸውና ብቃታቸው ሐዋርያው ለጢሞቴዎስ ከጻፈው ጋር ይስማማል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV Paul, a servant of God and an apostle of Jesus Christ for the faith of God's elect and the knowledge of the truth that … English BCV ኣገልጋሊ እግዚኣብሄርን፥ ሃዋርያ ኢየሱስ ክርስቶስን፥ ናይቶም ሕሩያት ኣምላኽ ንእምነት ክሃንፅ፥ ነቲ ናብ ቅድስና ዘብፅሕ፥ ፍልጠት ሓቂ ኽሰብኽ ካብ ዝተፀውዐ ጳውሎስ። ትግርኛ GAZBIB Ani Phaawulos amantii fi dhugaa beekuu warra Waaqayyoof fo'amanii, akka namoota Waaqayyoof ta'utti dammaqsuudhaaf, hojj… Afaan Oromoo BCV GIZ እምጳውሎስ ገብሩ ለእግዚአብሔር ወሐዋርያሁ ለኢየሱስ ክርስቶስ በሃይማኖቶሙ ለኅሩያኒሁ ለእግዚአብሔር ወአእምሮ ጽድቅ ዘበጽድቁ ለእግዚአብሔር። giz GAZGAZ Ani Phaawulos amantii fi dhugaa beekuu warra Waaqayyoof fo'amanii, akka namoota Waaqayyoof ta'utti dammaqsuudhaaf, hojj… Afaan Oromoo BCV aksum ኣገልጋሊ እግዚኣብሄርን፥ ሃዋርያ ኢየሱስ ክርስቶስን፥ ናይቶም ሕሩያት ኣምላኽ ንእምነት ክሃንፅ፥ ነቲ ናብ ቅድስና ዘብፅሕ፥ ፍልጠት ሓቂ ኽሰብኽ ካብ ዝተፀውዐ ጳውሎስ። ትግርኛ AMHNIV የእግዚአብሔርን ምርጦች እምነትና ወደ እውነተኛ መንፈሳዊነት የሚመራውን የእውነት ዕውቀት ለማሳደግ የእግዚአብሔር ባሪያና የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ የሆነው ጳውሎስ፤ አማርኛ SWAHSUV Paulo, mtumwa wa Mungu, na mtume wa Yesu Kristo; kwa ajili ya imani ya wateule wa Mungu, na ujuzi wa kweli ile iletayo … Kiswahili