ወደ ቲቶ 1

AMHNIVአማርኛ16 ጥቅሶች3:09 አዳምጥ
አዳምጥ 3:09 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1የእግዚአብሔርን ምርጦች እምነትና ወደ እውነተኛ መንፈሳዊነት የሚመራውን የእውነት ዕውቀት ለማሳደግ የእግዚአብሔር ባሪያና የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ የሆነው ጳውሎስ፤

2እምነቱና ዕውቀቱ የተመሠረቱትም የማይዋሸው አምላክ ከዘመናት በፊት በገባው የዘላለም ሕይወት ተስፋ ላይ ነው።

3እርሱ በወሰነውም ጊዜ በአዳኛችን በእግዚአብሔር ትእዛዝ ለእኔ ዐደራ በተሰጠ ስብከት በኩል ቃሉን ይፋ አደረገ።

4የጋራችን በሆነው እውነተኛ እምነት ልጄ ለሆነው ለቲቶ፤ ከእግዚአብሔር አብ፣ ከአዳኛችንም ከክርስቶስ ኢየሱስ ጸጋና ሰላም ይሁን።

5አንተን በቀርጤስ የተውሁህ ገና ያልተስተካከለውን ነገር እንድታስተካክልና ባዘዝሁህ መሠረት በየከተማው ሽማግሌዎችን እንድትሾም ነው።

6ሽማግሌ ነቀፋ የሌለበት፣ የአንዲት ሚስት ባል፣ ልጆቹም አማኞችና በመዳራት ወይም ባለመታዘዝ ስማቸው የማይነሣ ይሁን።

7ኤጲስቆጶስ የእግዚአብሔር ሥራ ባለ ዐደራ እንደ መሆኑ የማይነቀፍ ሊሆን ይገባል፤ ይኸውም ትምክሕተኛ፣ ግልፍተኛ፣ ሰካራም፣ ጨቅጫቃና ተገቢ ባልሆነ መንገድ ለጥቅም የሚሮጥ ሊሆን አይገባም።

8ከዚህ ይልቅ እንግዳ ተቀባይ፣ በጎ የሆነውን ነገር የሚወድ፣ ራሱን የሚገዛ፣ ቅን፣ ቅዱስና ጠንቃቃ ሊሆን ይገባል።

9ሌሎችን ትክክል በሆነው ትምህርት እንዲያበረታታና ይህንኑ ትምህርት የሚቃወሙትን ይወቅስ ዘንድ እንደ ተማረው በታመነ ቃል የሚጸና መሆን አለበት።

10ዐመፀኞች፣ ለፍላፊዎችና አታላዮች የሆኑ ብዙ ሰዎች አሉና፤ በተለይም እነዚህ ከተገረዙት ወገን ናቸው።

11እነዚህን ዝም ማሰኘት ተገቢ ነው፤ ምክንያቱም ትክክል ባልሆነ መንገድ ጥቅም ለማግኘት ሲሉ ማስተማር የማይገባቸውን ነገር በማስተማር ቤተ ሰብን ሁሉ በመበከል ላይ ናቸውና።

12ከራሳቸው ነቢያት አንዱ ስለ እነርሱ ሲናገር፣ “የቀርጤስ ሰዎች ዘወትር ውሸታሞች፣ ክፉ አውሬዎችና ሰነፍ ሆዳሞች ናቸው” ብሎአል።

13ይህ ምስክርነት እውነት ነው፤ ስለዚህ አጥብቀህ ገሥጻቸው፤ ይኸውም ትክክለኛ እምነት እንዲኖራቸውና

14የአይሁድን ተረት ወይም ከእውነት የራቁትን ሰዎች ትእዛዝ እንዳያዳምጡ ነው።

15ለንጹሓን ሁሉም ነገር ንጹሕ ነው፤ ለርኵሳንና ለማያምኑ ግን ንጹሕ የሆነ ምንም ነገር የለም፤ እንዲያውም አእምሮአቸውና ኅሊናቸው የረከሰ ነው።

16እግዚአብሔርን እናውቃለን ይላሉ፤ ዳሩ ግን በተግባራቸው ይክዱታል፤ አስጸያፊዎች፣ የማይታዘዙና ለበጎ ሥራ የማይበቁ ናቸው።

ማብራሪያ

፩፥፩-፬ የኃጢአትና የሰይጣን ባሪያዎች ያልሆኑ ሁሉ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ናቸው። ሁሉም የወንጌል እውነት እግዚአብሔርን ከመምሰል ጋር የሚስማማና እግዚአብሔርን መፍራትን የሚያስተምር ነው። የወንጌል ዓላማ ተስፋንና እምነትን ከፍ ማድረግ፤ አእምሮንና ልብን ከዓለም ማስወገድ፤ ወደ ሰማይና ወደ ላይ ወዳሉት ነገሮች ከፍ ማድረግ ነው። እንግዲህ ወንጌል ምን ያህል ግሩም ነው! ከጥንት ጀምሮ የመለኮታዊ የተስፋ ቃል ርዕስ የነበረው ሲሆን፤ ስለ ልዩ መብቶቻችንም ምን ያህል ምስጋና ይገባናል! እምነት ከመስማት ይመጣል፤ መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው። የተሾመና የተጠራም ሁሉ ቃሉን መስበክ አለበት። ጸጋ የእግዚአብሔር ነፃ ሞገስና በእርሱ ዘንድ ያለን ተቀባይነት ነው። ምሕረት ደግሞ የሞገሱ ፍሬዎች ሲሆን በኃጢአት ስርየትና በዚህም ሆነ ከዚያ በኋላ ካሉ ሁሉ መከራዎች ነፃ መውጣት ነው። ሰላምም የምሕረት ውጤትና ፍሬ ነው። ሰላማችን በሆነው በክርስቶስ በኩል ከእግዚአብሔር ጋር፤ ከፍጥረታትና ከራሳችን ጋርም ሰላም ነው። ጸጋ የሁሉም በረከቶች ምንጭ ነው። ምሕረት፣ ሰላም፣ መልካም ነገር ሁሉ ከዚህ ይፈልቃል።

1:5-9 ፓስተሮች፣ በዚህ ስፍራ ሽማግሌዎችና ኤጲስ ቆጶሳት ተብለው የተጠሩት፣ ባሕርያቸውና ብቃታቸው ሐዋርያው ለጢሞቴዎስ ከጻፈው ጋር ይስማማል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG የእግዚአብሔር ባሪያና የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ የሆነ ጳውሎስ፥ በእግዚአብሔር ለተመረጡት እምነት እንዲሆንላቸው በዘላለምም ሕይወት ተስፋ እንደ አምልኮት ያለውን እውነት እንዲያውቁ የተላከ፤… አማርኛ ENGNIV Paul, a servant of God and an apostle of Jesus Christ for the faith of God's elect and the knowledge of the truth that … English BCV ኣገልጋሊ እግዚኣብሄርን፥ ሃዋርያ ኢየሱስ ክርስቶስን፥ ናይቶም ሕሩያት ኣምላኽ ንእምነት ክሃንፅ፥ ነቲ ናብ ቅድስና ዘብፅሕ፥ ፍልጠት ሓቂ ኽሰብኽ ካብ ዝተፀውዐ ጳውሎስ። ትግርኛ GAZBIB Ani Phaawulos amantii fi dhugaa beekuu warra Waaqayyoof fo'amanii, akka namoota Waaqayyoof ta'utti dammaqsuudhaaf, hojj… Afaan Oromoo BCV GIZ እምጳውሎስ ገብሩ ለእግዚአብሔር ወሐዋርያሁ ለኢየሱስ ክርስቶስ በሃይማኖቶሙ ለኅሩያኒሁ ለእግዚአብሔር ወአእምሮ ጽድቅ ዘበጽድቁ ለእግዚአብሔር። giz GAZGAZ Ani Phaawulos amantii fi dhugaa beekuu warra Waaqayyoof fo'amanii, akka namoota Waaqayyoof ta'utti dammaqsuudhaaf, hojj… Afaan Oromoo BCV aksum ኣገልጋሊ እግዚኣብሄርን፥ ሃዋርያ ኢየሱስ ክርስቶስን፥ ናይቶም ሕሩያት ኣምላኽ ንእምነት ክሃንፅ፥ ነቲ ናብ ቅድስና ዘብፅሕ፥ ፍልጠት ሓቂ ኽሰብኽ ካብ ዝተፀውዐ ጳውሎስ። ትግርኛ SWAHSUV Paulo, mtumwa wa Mungu, na mtume wa Yesu Kristo; kwa ajili ya imani ya wateule wa Mungu, na ujuzi wa kweli ile iletayo … Kiswahili