መኃልየ መኃልይ 4

AMHNIVአማርኛ16 ጥቅሶች3:03 አዳምጥ
አዳምጥ 3:03 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ውዴ ሆይ፤ እንዴት ውብ ነሽ! እንዴትስ ያለሽ ቈንጆ ነሽ ከመሸፈኛሽ ውስጥ ያሉት ዐይኖችሽ እንደ ርግብ ዐይኖች ናቸው፤ ጠጕርሽም ከገለዓድ ተራራ እንደሚወርድ፣ የፍየል መንጋ ነው።

2ጥርሶችሽ ወዲያው ተሸልተው፣ ከመታጠቢያ እንደ ወጡ የበግ መንጋ ናቸው፤ ሁሉም መንታ መንታ የወለዱ፣ ከመካከላቸውም መካን የሌለባቸው ናቸው።

3ከንፈሮችሽ ቀይ የሐር ፈትል ይመስላሉ፤ አፍሽም ውብ ነው፤ ከመሸፈኛሽ ውስጥ ያሉት ጒንጮችሽ፣ ለሁለት የተከፈለ ሮማን ይመስላሉ።

4ዐንገትሽ አምሮ የተሠራውን፣ በላዩም የጦረኞች ጋሻዎች ሁሉ ያሉበትን፣ ሺህ ጋሻዎች የተንጠለጠሉበትን፣ የዳዊትን የመጠበቂያ ማማ ይመስላል።

5ሁለቱ ጡቶችሽ መንታ ሆነው የተወለዱ፣ በውብ አበቦች መካከልም የተሰማሩ፣ ሁለት የሚዳቋ ግልገሎችን ይመስላሉ።

6ጎሕ ከመቅደዱ በፊት፣ ጥላውም ሳይሸሽ፣ ወደ ከርቤ ተራራ፣ ወደ ዕጣኑም ኰረብታ እወጣለሁ።

7ውዴ ሆይ፤ ሁለንተናሽ ውብ ነው፤ እንከንም አይወጣልሽም።

8ሙሽራዬ ሆይ፤ ከሊባኖስ አብረሽኝ ነዪ፤ አዎን ከሊባኖስ አብረሽኝ ነዪ፤ ከአንበሶች ዋሻ፣ ከነብሮች ተራራ፣ ከኤርሞን ራስ፣ ከሳኔር ጫፍ፣ ከአማና ዐናት ውረጂ።

9እኅቴ ሙሽራዬ፣ ልቤን ሰርቀሽዋል፤ በአንድ አፍታ እይታሽ፣ ከሐብልሽም በአንዱ ዕንቊ፣ ልቤን ሰርቀሽዋል።

10እኅቴ ሙሽራዬ፣ ፍቅርሽ እንዴት ደስ ያሰኛል! ፍቅርሽ ከወይን ጠጅ ይልቅ ምንኛ የሚያረካ ነው፤ የሽቱሽም መዐዛ ከቅመም ሁሉ ይልቅ የቱን ያህል ይበልጥ!

11ሙሽራዬ ሆይ፤ ከንፈሮችሽ የማር ወለላ ያንጠባጥባሉ፤ ከአንደበትሽም ወተትና ማር ይፈልቃል፤ የልብስሽም መዐዛ እንደ ሊባኖስ ሽታ ነው።

12እኅቴ ሙሽራዬ፤ የታጠረ የአትክልት ቦታ፣ ዙሪያውን የተከበበ ምንጭ፣ የታተመም ፏፏቴ ነሽ።

13ተክልሽ ሮማን፣ ምርጥ ፍሬዎች፣ ሄናና ናርዶስ ያሉበት ነው።

14እንዲሁም ናርዶስና ቀጋ፣ ጠጅ ሣርና ቀረፋ፣ የተለያዩ የዕጣን ዛፎች፣ ከርቤና እሬት፣ ምርጥ ቅመሞች ሁሉ አሉበት።

15አንቺ የአትክልት ቦታ ፏፏቴ፣ ከሊባኖስ የሚወርድ፣ የፈሳሽ ውሃ ጒድጓድ ነሽ።

16የሰሜን ነፋስ ሆይ፤ ንቃ፤ የደቡብም ነፋስ ሆይ፤ ና! መዐዛው ያውድ ዘንድ፣ በአትክልት ቦታዬ ላይ ንፈስ፤ ውዴ ወደ አትክልት ቦታው ይግባ፤ ምርጥ ፍሬዎቹንም ይብላ።

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG ወዳጄ ሆይ፥ እነሆ፥ ውብ ነሽ፤ እነሆ፥ አንቺ ውብ ነሽ፤ በዓይነ ርግብ መሸፈኛሽ ውስጥ ዓይኖችሽ እንደ ርግቦች ናቸው፤ ጠጕርሽ በገለዓድ ተራራ እንደሚወርድ፡ እንደ ፍየል መንጋ ነው። አማርኛ ENGNIV How beautiful you are, my darling! Oh, how beautiful! Your eyes behind your veil are doves. Your hair is like a flock o… English BCV ኣቲ ፍቕርተይ ክንደይ ትፅብቒ! ከመይ ዝበልኪ ቘንጆኸ ኢኺ! ኣዒንትኺ ኣብ ውሽጢ ጕልባብኪ፥ ከም ርግቢታት እየን፤ ፀጕሪ ርእስኺ ኸም እተን ካብ እምባ ገለዓድ ዝወርዳ መጓሰ ኣጣል እዩ። ትግርኛ GAZBIB “Kunoo ati miidhagduu dha yaa hiriyee ko! Ati miidhagduu dha, iji kees akka ija gugee kuullee dha, innis shaashii ati h… Afaan Oromoo BCV GIZ ነያ ሠናይት እንተ ኀቤየ ነያ ሠናይት፤ አዕይንትኪ ዘርግብ እንበለ አርምሞትኪ፤ ሥዕርትኪ ከመ መርዔተ አጣሊ እለ ተከሥታ እምአድባረ ገላዐድ። giz GAZGAZ “Kunoo ati miidhagduu dha yaa hiriyee ko! Ati miidhagduu dha, iji kees akka ija gugee kuullee dha, innis shaashii ati h… Afaan Oromoo BCV aksum ኣቲ ፍቕርተይ ክንደይ ትፅብቒ! ከመይ ዝበልኪ ቘንጆኸ ኢኺ! ኣዒንትኺ ኣብ ውሽጢ ጕልባብኪ፥ ከም ርግቢታት እየን፤ ፀጕሪ ርእስኺ ኸም እተን ካብ እምባ ገለዓድ ዝወርዳ መጓሰ ኣጣል እዩ። ትግርኛ SWAHSUV Tazama, u mzuri, mpenzi wangu, U mzuri, macho yako ni kama ya hua, Nyuma ya barakoa yako. Nywele zako ni kama kundi la … Kiswahili