መኃልየ መኃልይ 4

AMHEVGአማርኛ16 ጥቅሶች2:45 አዳምጥ
አዳምጥ 2:45 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ወዳጄ ሆይ፥ እነሆ፥ ውብ ነሽ፤ እነሆ፥ አንቺ ውብ ነሽ፤ በዓይነ ርግብ መሸፈኛሽ ውስጥ ዓይኖችሽ እንደ ርግቦች ናቸው፤ ጠጕርሽ በገለዓድ ተራራ እንደሚወርድ፡ እንደ ፍየል መንጋ ነው።

2ጥርሶችሽ ታጥበው እንደ ተሸለቱ፡ ሁሉም መንታ እንደ ወለዱ፡ ከእነርሱም መካን እንደሌለባቸው መንጎች ናቸው።

3ከንፈሮችሽ እንደ ቀይ ሐር ፈትል ናቸው፥ አፍሽም ያማረ ነው፤ በዓይነ ርግብ መሸፈኛሽ ውስጥ ጕንጭና ጕንጭሽ፤ እንደ ተከፈለ ሮማን ናቸው።

4አንገትሽ ለሰልፍ ዕቃ መስቀያ እንደ ተሠራው እንደ ዳዊት ግንብ ነው፤ ሺህ ጋሻ የኃያላንም መሣሪያ ሁሉ ተንጠልጥሎበታል።

5ሁለቱ ጡቶችሽ መንታ እንደ ተወለዱ፥ በሱፍ አበባ መካከል እንደሚሰማሩ፡ እንደ ሚዳቋ ግልገሎች ናቸው።

6ቀኑ እስኪነፍስ ጥላውም እስኪያልፍ ድረስ፥ ወደ ከርቤው ተራራ ወደ ዕጣኑም ኮረብታ እሄዳለሁ።

7ወዳጄ ሆይ፥ ሁለንተናሽ ውብ ነው፥ ነውርም የለብሽም።

8ሙሽራዬ ሆይ፥ ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነዪ፡ ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነዪ፡ ከአማና ራስ ከሳኔርና ከኤርሞን ራስ፥ ከአንበሶች መኖሪያ ከነብሮችም ተራራ ተመልከች።

9እኅቴ ሙሽራ ሆይ፥ ልቤን በደስታ አሳበድሽው፡ አንድ ጊዜ በዓይኖችሽ፥ ከአንገትሽ ድሪ በአንዱ፡ ልቤን በደስታ አሳበድሽው።

10እኅቴ ሙሽራ ሆይ፥ ፍቅርሽ እንዴት መልካም ነው! ፍቅርሽ ከወይን ጠጅ ይልቅ እንዴት ይሻላል! የዘይትሽም መዓዛ ከሽቱ ሁሉ!

11ሙሽራዬ ሆይ፥ ከከንፈሮችሽ ማር ይንጠበጠባል፤ ከምላስሽ በታች ማርና ወተት አለ፥ የልብስሽም መዓዛ እንደ ሊባኖስ ሽታ ነው።

12እኅቴ ሙሽራ የተቈለፈ ገነት፥ የተዘጋ ምንጭ የታተመም ፈሳሽ ናት።

13ቡቃያሽ ሮማንና የተመረጠ ፍሬ፥ ቆዕ ከናርዶስ ጋር ያለበት ገነት ነው፥

14ናርዶስ ከቀጋ ጋር፥ የሽቱ ሣርና ቀረፋ፥ ከልዩ ልዩ ዕጣን ጋር፥ ከርቤና እሬት ከክቡር ሽቱ ሁሉ ጋር።

15አንቺ የገነት ምንጭ፥ የሕይወት ውኃ ጕድጓድ፥ ከሊባኖስም የሚፈስስ ወንዝ ነሽ።

16የሰሜን ነፋስ ሆይ፥ ተነሥ፥ የደቡብም ነፋስ ና፤ በገነቴ ላይ ንፈስ፥ ሽቱውም ይፍሰስ፤ ውዴ ወደ ገነቱ ይግባ፥ መልካሙንም ፍሬ ይብላ።

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV How beautiful you are, my darling! Oh, how beautiful! Your eyes behind your veil are doves. Your hair is like a flock o… English BCV ኣቲ ፍቕርተይ ክንደይ ትፅብቒ! ከመይ ዝበልኪ ቘንጆኸ ኢኺ! ኣዒንትኺ ኣብ ውሽጢ ጕልባብኪ፥ ከም ርግቢታት እየን፤ ፀጕሪ ርእስኺ ኸም እተን ካብ እምባ ገለዓድ ዝወርዳ መጓሰ ኣጣል እዩ። ትግርኛ GAZBIB “Kunoo ati miidhagduu dha yaa hiriyee ko! Ati miidhagduu dha, iji kees akka ija gugee kuullee dha, innis shaashii ati h… Afaan Oromoo BCV GIZ ነያ ሠናይት እንተ ኀቤየ ነያ ሠናይት፤ አዕይንትኪ ዘርግብ እንበለ አርምሞትኪ፤ ሥዕርትኪ ከመ መርዔተ አጣሊ እለ ተከሥታ እምአድባረ ገላዐድ። giz GAZGAZ “Kunoo ati miidhagduu dha yaa hiriyee ko! Ati miidhagduu dha, iji kees akka ija gugee kuullee dha, innis shaashii ati h… Afaan Oromoo BCV aksum ኣቲ ፍቕርተይ ክንደይ ትፅብቒ! ከመይ ዝበልኪ ቘንጆኸ ኢኺ! ኣዒንትኺ ኣብ ውሽጢ ጕልባብኪ፥ ከም ርግቢታት እየን፤ ፀጕሪ ርእስኺ ኸም እተን ካብ እምባ ገለዓድ ዝወርዳ መጓሰ ኣጣል እዩ። ትግርኛ AMHNIV ውዴ ሆይ፤ እንዴት ውብ ነሽ! እንዴትስ ያለሽ ቈንጆ ነሽ ከመሸፈኛሽ ውስጥ ያሉት ዐይኖችሽ እንደ ርግብ ዐይኖች ናቸው፤ ጠጕርሽም ከገለዓድ ተራራ እንደሚወርድ፣ የፍየል መንጋ ነው። አማርኛ SWAHSUV Tazama, u mzuri, mpenzi wangu, U mzuri, macho yako ni kama ya hua, Nyuma ya barakoa yako. Nywele zako ni kama kundi la … Kiswahili