ወደ ሮሜ 14

AMHEVGአማርኛ23 ጥቅሶች3:02 አዳምጥ
አዳምጥ 3:02 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1በእምነት የደከመውንም ተቀበሉት፥ በአሳቡም ላይ አትፍረዱ።

2ሁሉን ይበላ ዘንድ እንደ ተፈቀደለት የሚያምን አለ፥ ደካማው ግን አትክልት ይበላል።

3የሚበላ የማይበላውን አይናቀው የማይበላውም በሚበላው አይፍረድ፥ እግዚአብሔር ተቀብሎታልና።

4አንተ በሌላው ሎሌ የምትፈርድ ማን ነህ? እርሱ ቢቆም ወይም ቢወድቅ ለገዛ ጌታው ነው፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ሊያቆመው ይችላልና ይቆማል።

5ይህ ሰው አንድ ቀን ከሌላ ቀን እንዲሻል ያስባል፥ ያ ግን ቀን ሁሉ አንድ እንደ ሆነ ያስባል፤ እያንዳንዱ በገዛ አእምሮው አጥብቆ ይረዳ።

6ቀንን የሚያከብር ለጌታ ብሎ ያከብራል፤ የሚበላም እግዚአብሔርን ያመሰግናልና ለጌታ ብሎ ይበላል፤ የማይበላም ለጌታ ብሎ አይበላም እግዚአብሔርንም ያመሰግናል።

7ከእኛ አንድ ስንኳ ለራሱ የሚኖር የለምና፥ ለራሱም የሚሞት የለም፤

8በሕይወት ሆነን ብንኖር ለጌታ እንኖራለንና፥ ብንሞትም ለጌታ እንሞታለን። እንግዲህ በሕይወት ሆነን ብንኖር ወይም ብንሞት የጌታ ነን።

9ስለዚህ ነገር ሙታንንም ሕያዋንንም ይገዛ ዘንድ ክርስቶስ ሞቶአልና ሕያውም ሆኖአልና።

10አንተም በወንድምህ ላይ ስለ ምን ትፈርዳለህ? ወይስ አንተ ደግሞ ወንድምህን ስለ ምን ትንቃለህ? ሁላችን በክርስቶስ ፍርድ ወንበር ፊት እንቆማለንና።

11እንዲህ ተብሎ ተጽፎአልና፦ “እኔ ሕያው ነኝ፡ ይላል ጌታ፥ ጉልበት ሁሉ ለእኔ ይንበረከካል፡ መላስም ሁሉ እግዚአብሔርን ያመሰግናል።”

12እንግዲያስ እያንዳንዳችን ስለ ራሳችን ለእግዚአብሔር መልስ እንሰጣለን።

13እንግዲህ ከዛሬ ጀምሮ እርስ በርሳችን አንፈራረድ፤ ይልቁን ግን ለወንድም እንቅፋትን ወይም ማሰናከያን ማንም እንዳያኖርበት ይህን ቍረጡ።

14በራሱ ርኵስ የሆነ ነገር እንደ ሌለ በጌታ በኢየሱስ ሆኜ አውቄአለሁ ተረድቼአለሁም፤ ነገር ግን ምንም ርኵስ እንዲሆን ለሚቆጥር ለእርሱ ርኵስ ነው።

15ወንድምህንም በመብል ምክንያት የምታሳዝን ከሆንህ እንግዲህ በፍቅር አልተመላለስህም። ክርስቶስ ስለ እርሱ የሞተለትን እርሱን በመብልህ አታጥፋው።

16እንግዲህ ለእናንተ ያለው መልካም ነገር አይሰደብ፤

17የእግዚአብሔር መንግሥት ጽድቅና ሰላም በመንፈስ ቅዱስም የሆነ ደስታ ናት እንጂ መብልና መጠጥ አይደለችምና።

18እንደዚህ አድርጎ ለክርስቶስ የሚገዛ እግዚአብሔርን ደስ ያሰኛልና፥ በሰውም ዘንድ የተመሰገነ ነው።

19እንግዲያስ ሰላም የሚቆምበትን እርስ በርሳችንም የምንታነጽበትን እንከተል።

20በመብል ምክንያት የእግዚአብሔርን ሥራ አታፍርስ። ሁሉ ንጹሕ ነው፥ በመጠራጠር የተበላ እንደ ሆነ ግን ለዚያ ሰው ክፉ ነው።

21ሥጋን አለመብላት ወይንንም አለመጠጣት ወንድምህም የሚሰናከልበትን አለማድረግ መልካም ነው።

22ለአንተ ያለህ እምነት በእግዚአብሔር ፊት ለራስህ ይሁንልህ። ፈትኖ መልካም እንዲሆን በሚቈጥረው ነገር በራሱ ላይ የማይፈርድ ብፁዕ ነው።

23የሚጠራጠረው ግን ቢበላ በእምነት ስላልሆነ ተኮንኖአል፤ በእምነትም ያልሆነ ሁሉ ኃጢአት ነው።

ማብራሪያ

፲፬፥፩-፮ በክርስቶስ ቀጥተኛ ተከታዮችና ደቀ መዛሙርት መካከልም ጭምር የአመለካከት ልዩነቶች ይስተዋሉ ነበር። ቅዱስ ጳውሎስም ሊያቆማቸው አልሞከረም። ማንኛውንም ትምህርት በግድ መቀበል ወይም የውጭ ሥርዓቶችን ሳያምኑበት መፈጸም ግብዝነትና ከንቱ ይሆናል። በክርስቲያኖች ዘንድ ፍጹም የአመለካከት አንድነት ለማምጣት የሚደረጉ ጥረቶች ከንቱ ይሆናሉ። የክርስቲያናዊ ኅብረት በቃል ንትርኮች አይረበሽ። ወንድሞቻችንን ለመናቅና ለመውቀስ ስንፈተን ራሳችንን እንድንጠይቅ መልካም ነው፤ እግዚአብሔር የራሱ አላደረጋቸውምን? እርሱም ካደረጋቸው፣ እኔ ልክዳቸው እደፍራለሁን? ነጻነቱን የሚጠቀም ክርስቲያን ደካማ ወንድሙን እንደማያውቅና በአጉል እምነት እንደተያዘ አድርጎ አይናቀው። ጥንቁቁ አማኝ ወንድሙን አይውቀሰው፣ እግዚአብሔር የምግብን ልዩነት ሳይመለከት ተቀብሎታልና። ከእኛ እይታ ውጪ የሆኑ የሌሎችን ሐሳቦችና ውስጣዊ ዓላማዎች ለመፍረድ ስንነሳ የእግዚአብሔርን ስፍራ እንቀማለን። ቀናትን ስለማክበርም ጉዳዩ ተመሳሳይ ነበር። እነዚህ ሁሉ ነገሮች በክርስቶስ መምጣት እንደተወገዱ ያወቁት የአይሁድን በዓላት አላከበሩም ነበር። ነገር ግን ሕሊናችን ለምናደርገው ነገር መስማማቱ ብቻ በቂ አይደለም፤ ከእግዚአብሔር ቃል የተረጋገጠ መሆን አለበት። የሚጠራጠር ሕሊናህን በመቃረን ከመሥራት ተጠንቀቅ። ሁላችንም የራሳችንን አመለካከት የእውነት መስፈርት ለማድረግ፣ ለሌሎች አጠራጣሪ የሚመስሉ ነገሮችን ደግሞ እርግጠኛ አድርገን ለመቁጠር ዝንባሌ አለን። በዚህም ምክንያት ክርስቲያኖች በአጠራጣሪና አስፈላጊ ባልሆኑ ጉዳዮች ላይ ብዙ ጊዜ እርስ በእርሳቸው ይናናቃሉ ወይም ይወጋገዛሉ። የምሕረታችን ሁሉ ባለቤትና ሰጪ ለሆነው ለእግዚአብሔር የሚኖረን ምስጋና የተሞላበት አመለካከት ይቀድሳቸዋል እንዲሁም ያጣፍጣቸዋል።

14:7-13 አንዳንዶች ደካሞች ቢሆኑም፣ ሌሎችም ብርቱዎች ቢሆኑም፣ ሁሉም ለራሳቸው ላለመኖር መስማማት አለባቸው። ስሙን ለክርስቶስ የሰጠ ማንም ሰው፣ ራስ ወዳድ እንዲሆን አይፈቀድለትም፤ ይህ ከእውነተኛው ክርስትና ጋር የሚጻረር ነው። የሕይወታችን ዋናው ዓላማ ራሳችንን ማስደሰት ሳይሆን፣ እግዚአብሔርን ማስደሰት ነው። ክርስቶስን ሁሉ በሁሉ የሚያደርግ እውነተኛ ክርስትና ያ ነው። ምንም እንኳን ክርስቲያኖች በኃይል፣ በችሎታ፣ እና በጥቃቅን ነገሮች አፈጻጸም ቢለያዩም፣ ሁሉም የጌታ ናቸው፤ ሁሉም የሚመለከቱትና የሚያገለግሉት፣ ራሳቸውንም ለክርስቶስ የሚያስመሰግኑ ናቸው። የሕያዋን ጌታ ነው፣ ሊገዛቸው፤ የሙታንም ጌታ ነው፣ ሊያነሣቸውና ከሞት ሊያስነሣቸው። ክርስቲያኖች እርስ በርሳቸው ሊፈርዱ ወይም ሊንቁ አይገባም፣ ምክንያቱም ሁለቱም በቅርቡ መልስ መስጠት አለባቸው።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6