ወደ ሮሜ 12

AMHNIVአማርኛ21 ጥቅሶች3:30 አዳምጥ
አዳምጥ 3:30 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፤ ሰውነታችሁን ቅዱስና እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሕያው መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፤ ይህም እንደ ባለ አእምሮ የምታቀርቡት አምልኮአችሁ ነው።

2መልካም፣ ደስ የሚያሰኝና ፍጹም የሆነውን የእግዚአብሔር ፈቃድ ምን እንደሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በአእምሮአችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።

3እግዚአብሔር ለእያንዳንዳችሁ በሰጣችሁ እምነት መጠን ራሳችሁን በአግባቡ መዝኑ እንጂ፣ ከሆናችሁት በላይ ራሳችሁን ከፍ አድርጋችሁ እንዳታስቡ በተሰጠኝ ጸጋ እያንዳንዳችሁን እመክራለሁ።

4እያንዳንዳችን በአንዱ አካላችን ብዙ ብልቶች እንዳሉን፣ እነዚህም ብልቶች አንድ ዐይነት ተግባር እንደሌላቸው ሁሉ፣

5እንዲሁም እኛ ብዙዎች ስንሆን በክርስቶስ አንድ አካል ነን። እያንዳንዳችንም የሌላው ብልት ነን።

6እንደ ተሰጠን ጸጋ የተለያዩ ስጦታዎች አሉን፤ ለአንዱ የተሰጠው ስጦታ ትንቢት መናገር ከሆነ፣ እንደ እምነቱ መጠን ይናገር።

7ማገልገል ቢሆን ያገልግል፤ ማስተማርም ከሆነ ያስተምር፤

8መምከር ከሆነ ይምከር፤ ለሌላቸው መለገስ ከሆነም አብዝቶ ይለግስ፤ ማስተዳደር ከሆነም በትጋት ያስተዳድር፤ ምሕረት ማድረግ ከሆነም በደስታ ይማር።

9ፍቅራችሁ ያለ ግብዝነት ይሁን፤ ክፉ የሆነውን ሁሉ ተጸየፉ፤ በጎ ከሆነው ነገር ጋር ተቈራኙ።

10እርስ በርሳችሁ በወንድማማች መዋደድ አጥብቃችሁ ተዋደዱ፤ አንዱ ሌላውን ከራሱ በማስበለጥ እርስ በርሳችሁ ተከባበሩ።

11ጌታን ለማገልገል በመንፈስ የጋላችሁ ሁኑ እንጂ ከዚህ ትጋት ወደ ኋላ አትበሉ።

12በተስፋ ደስተኞች ሁኑ፤ በመከራ ታገሡ፤ በጸሎት ጽኑ።

13ችግረኛ ለሆኑ ቅዱሳን ካላችሁ አካፍሉ፤ እንግዶችን ተቀበሉ።

14የሚያሳድዷችሁን መርቁ፤ መርቁ እንጂ አትርገሙ።

15ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችሁ፤ ከሚያዝኑም ጋር እዘኑ።

16እርስ በርሳችሁ በመስማማት ኑሩ። ዝቅተኛ ኑሮ ውስጥ ካሉ ጋር አብራችሁ ለመሆን ፍቀዱ እንጂ አትኵራሩ፤ በራሳችሁም አትመኩ።

17ለማንም ክፉን በክፉ አትመልሱ፤ በሰው ሁሉ ፊት በጎ የሆነውን ነገር ለማድረግ ትጉ።

18ቢቻላችሁስ በበኩላችሁ ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ።

19ወዳጆቼ ሆይ፤ ለእግዚአብሔር ቊጣ ፈንታ ስጡ እንጂ አትበቀሉ፤ “በቀል የእኔ ነው፤ እኔ ብድራትን እመልሳለሁ” ይላል ጌታ ተብሎ ተጽፎአልና።

20ይልቁንስ፣ “ጠላትህ ቢራብ አብላው፤ ቢጠማም አጠጣው። ይህን በማድረግህም የእሳት ፍም በራሱ ላይ ትከምራለህ።”

21ክፉን በመልካም አሸንፍ እንጂ በክፉ አትሸነፍ።

ማብራሪያ

12:1,2 ሐዋርያው በተግባር የሚተገበሩ የተለያዩ አስተምህሮዎችን ሲያብራራና ሲያረጋግጥ የቆየበትን የመልእክቱን ክፍል ካጠናቀቀ በኋላ፣ አሁን ደግሞ ከወንጌል መርሆች የሚመነጩ ወሳኝ ግዴታዎችን ያሳስባል። ሮማውያንን በክርስቶስ ወንድሞቹ እንደመሆናቸው መጠን፣ በእግዚአብሔር ምሕረት አማካኝነት አካሎቻቸውን ለእርሱ ሕያው መስዋዕት አድርገው እንዲያቀርቡ ለመናቸው። ይህ ኃይለኛ ጥሪ ነው። በየቀኑ ከጌታ የምሕረቱን ፍሬዎች እንቀበላለን። ራሳችንን እንስጥ፤ ማንነታችንን በሙሉ፣ ያለንን ሁሉ፣ ማድረግ የምንችለውን ሁሉ፤ ከሁሉም በኋላ ግን፣ ለዚህ ሁሉ እጅግ ለበዛው በረከት ምን ምላሽ ይሆን? ለእግዚአብሔር የተወደደ ነው፤ ምክንያት ልንሰጥለት የምንችልበት፣ የምንረዳውም ምክንያታዊ አገልግሎት ነው።

መመለስና ቅድሳት የአእምሮ መታደስ ናቸው፤ የነፍስ ባሕሪይ (ጥራት) ለውጥ እንጂ፣ የነፍስ ምንነት ለውጥ አይደለም። የቅድሳት ሂደት፣ ለኃጢአት እየሞትን ለጽድቅም እየኖርን ስንሄድ፣ በክብር እስኪፈጸም ድረስ ይህንን የማደስ ሥራ ማስቀጠል ነው። የዚህ መታደስ ዋነኛ ጠላት ግን፣ ከዚህ ዓለም ጋር መመሳሰል ነው። ደስታ በቅርቡ በሚያልፉት የዚህ ዓለም ነገሮች ውስጥ እንዳለ በማሰብ፣ የደስታ እቅዶችን ከመቀየስ ተጠንቀቁ። በሥጋ ምኞት ከሚሄዱና ምድራዊ ነገሮችን ከሚያስቡት ልማዶች ጋር አትመሳሰሉ። የመንፈስ ቅዱስ ሥራ መጀመሪያ የሚጀምረው በማስተዋል ውስጥ ነው፤ ከዚያም መላው ሰው በእውቀት፣ በጽድቅና በእውነተኛ ቅድስና የእግዚአብሔርን መልክ እስከሚመስል ድረስ ወደ ፈቃድ፣ ወደ ስሜቶችና ወደ የኑሮ ምግባር ይቀጥላል። ስለዚህም፣ እግዚአብሔርን የሚመስል መሆን ማለት፣ ራሳችንን ለእግዚአብሔር አሳልፎ መስጠት ነው።

፲፪፡፫-፰ ትዕቢት በተፈጥሮአችን ያለ ኃጢአት ነው። ከእርሱ መጠንቀቅና የታጠቅን መሆን ያስፈልገናል። ቅዱሳን ሁሉ በክርስቶስ አንድ አካልን ይመሠርታሉ፤ እርሱም የዚህ አካል ራስና የአንድነታቸው የጋራ ማዕከል ነው። በመንፈሳዊው አካል ውስጥ፣ አንዳንዶች ለአንድ ዓይነት ሥራ የተዘጋጁና የተጠሩ ሲሆኑ፤ ሌሎች ደግሞ ለሌላ ዓይነት ሥራ የተጠሩ ናቸው። እርስ በርስ ልንሠራው የምንችለውን መልካም ነገር ሁሉ፣ ለጋራ ጥቅማችንም ጭምር፣ ማድረግ አለብን። ስላለን አቅም በአግባቡ ብናስብና እነርሱን በአግባቡ ለማበልጸግ ምን ያህል እንደምንሳነው ብናስተውል፣ ትሕትናን ያጎናጽፈን ነበር። ነገር ግን በችሎታችን መኩራት እንደሌለብን ሁሉ፣ በትሕትናና ራስን በመካድ ሽፋን የሌሎችን ጥቅም ለማስጠበቅ ራሳችንን ከመስጠት ወደ ኋላ እንዳንል መጠንቀቅ ይገባናል። እኔ ምንም አይደለሁም፤ ስለዚህ ዝም ብዬ እቀመጣለሁ፣ ምንም አላደርግም ማለት የለብንም፤ ነገር ግን፣ እኔ በራሴ ምንም አይደለሁም፣ ስለዚህ በክርስቶስ ጸጋ ኃይል ራሴን እስከ መጨረሻው እሰጣለሁ።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ሰውነታችሁን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና ሕያው ቅዱስም መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፥ እርሱም ለአእምሮ የሚመች አገልግ… አማርኛ ENGNIV Therefore, I urge you, brothers, in view of God's mercy, to offer your bodies as living sacrifices, holy and pleasing t… English BCV እምበኣር ኣሕዋተይ፥ ሰብነትኩም ህያውን ቅዱስን ንእግዚኣብሄር ዘሐጕስን፥ መስዋእቲ ጌርኩም ክተቕርብዎ፥ ብምሕረት እግዚኣብሄር እልምነኩም ኣለኹ፤ እዙይ ድማ እቲ ግቡእ መንፈሳዊ ኣገልግሎትኩም… ትግርኛ GAZBIB Ammas yaa obboloota ko, araara Waaqayyoof jedhaatii namummaan keessan qulqullaa'aadhaa fi Waaqayyo duratti fudhatamaa a… Afaan Oromoo BCV GIZ አስተበቍዐክሙ አኀዊነ በሣህሉ ለእግዚአብሔር ረስዩ ነፍስተክሙ መሥዋዕተ ቅዱሰ ለእግዚአብሔር ወሕያወ ወሥሙረ ወኅሩየ ይኩን ቍርባንክሙ ወቅኔክሙ ነባቢ። giz GAZGAZ Ammas yaa obboloota ko, araara Waaqayyoof jedhaatii namummaan keessan qulqullaa'aadhaa fi Waaqayyo duratti fudhatamaa a… Afaan Oromoo BCV aksum እምበኣር ኣሕዋተይ፥ ሰብነትኩም ህያውን ቅዱስን ንእግዚኣብሄር ዘሐጕስን፥ መስዋእቲ ጌርኩም ክተቕርብዎ፥ ብምሕረት እግዚኣብሄር እልምነኩም ኣለኹ፤ እዙይ ድማ እቲ ግቡእ መንፈሳዊ ኣገልግሎትኩም… ትግርኛ SWAHSUV Basi, ndugu zangu, nawasihi, kwa huruma zake Mungu, itoeni miili yenu iwe dhabihu iliyo hai, takatifu, ya kumpendeza Mu… Kiswahili