ወደ ሮሜ 11

AMHEVGአማርኛ35 ጥቅሶች4:57 አዳምጥ
አዳምጥ 4:57 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1እንግዲህ፦ “እግዚአብሔር ሕዝቡን ጣላቸውን?” እላለሁ። አይደለም፡ እኔ ደግሞ እስራኤላዊና ከአብርሃም ዘር ከብንያምም ወገን ነኝና።

2እግዚአብሔር አስቀድሞ ያወቃቸውን ሕዝብ አልጣላቸውም። መጽሐፍ ስለ ኤልያስ በተጻፈው የሚለውን፥ በእግዚአብሔር ፊት እስራኤልን እንዴት እንደሚከስ፥ አታውቁምን?

3“ጌታ ሆይ፥ ነቢያትህን ገደሉ መሠዊያዎችህንም አፈረሱ እኔም ብቻዬን ቀረሁ ነፍሴንም ይሹአታል።”

4ነገር ግን አምላካዊ መልስ ምን አለው? “ለበአል ያልሰገዱትን ሰባት ሺህ ሰዎች ለእኔ አስቀርቼአለሁ።”

5እንደዚሁም በአሁን ዘመን ደግሞ በጸጋ የተመረጡ ቅሬታዎች አሉ።

6በጸጋ ከሆነ ግን ከሥራ መሆኑ ቀርቶአል፤ ጸጋ ያለዚያ ጸጋ መሆኑ ቀርቶአል።

7እንግዲህ ምንድር ነው? እስራኤል የሚፈልጉትን አላገኙትም፤ የተመረጡት ግን አገኙት፤ ሌሎቹም ደነዘዙ፤

8እንዲሁም እንዲህ ተብሎ ተጽፎአል፦ “ዓይኖቻቸው እንዳያዩ ጆሮቻቸውም እንዳይሰሙ እግዚአብሔር የእንቅልፍ መንፈስን እስከ ዛሬ ድረስ ሰጣቸው።”

9ዳዊትም እንዲህ ብሎአል፦ “ማዕዳቸው ወጥመድና አሽክላ ማሰናከያም ፍዳም ይሁንባቸው፤

10ዓይኖቻቸው እንዳያዩ ይጨልሙ፥ ጀርባቸውንም ዘወትር አጉብጥ።”

11እንግዲህ፦ “የተሰናከሉ እስኪወድቁ ድረስ ነውን?” እላለሁ። አይደለም፤ ነገር ግን እነርሱን ያስቀናቸው ዘንድ በእነርሱ በደል መዳን ለአሕዛብ ሆነ።

12ዳሩ ግን በደላቸው ለዓለም ባለ ጠግነት መሸነፋቸውም ለአሕዛብ ባለ ጠግነት ከሆነ፥ ይልቁንስ መሙላታቸው እንዴት ይሆን?

13ለእናንተም ለአሕዛብ እናገራለሁ። እኔ የአሕዛብ ሐዋርያ በሆንሁ መጠን ሥጋዬ የሆኑትን አስቀንቼ ምናልባት ከእነርሱ አንዳንዱን አድን እንደሆነ አገልግሎቴን አከብራለሁ።

15የእነርሱ መጣል ለዓለም መታረቅ ከሆነ ከሙታን ከሚመጣ ሕይወት በቀር መመለሳቸው ምን ይሆን?

16በኵራቱም ቅዱስ ከሆነ ብሆው ደግሞ ቅዱስ ነው፤ ሥሩም ቅዱስ ከሆነ ቅርንጫፎቹ ደግሞ ቅዱሳን ናቸው።

17ነገር ግን ከቅርንጫፎች አንዳንዱ ቢሰበሩ አንተም የበረሀ ወይራ የሆንህ በመካከላቸው ገብተህ ከእነርሱ ጋር የወይራ ዘይት ከሚወጣው ሥር ተካፋይ ከሆንህ፥ በቅርንጫፎች ላይ አትመካ፤

18ብትመካባቸው ግን ሥሩ አንተን ይሸከምሃል እንጂ ሥሩን የምትሸከም አንተ አይደለህም።

19እንግዲህ፦ “እኔ እንድገባ ቅርንጫፎች ተሰበሩ፡” ትል ይሆናል።

20መልካም፤ እነርሱ ከአለማመን የተነሣ ተሰበሩ አንተም ከእምነት የተነሣ ቆመሃል። ፍራ እንጂ የትዕቢትን ነገር አታስብ።

21እግዚአብሔር እንደ ተፈጠሩት ለነበሩት ቅርንጫፎች የራራላቸው ካልሆነ ለአንተ ደግሞ አይራራልህምና።

22እንግዲህ የእግዚአብሔርን ቸርነትና ጭከና ተመልከት፤ ጭከናው በወደቁት ላይ ነው፥ በቸርነቱ ግን ጸንተህ ብትኖር የእግዚአብሔር ቸርነት በአንተ ላይ ነው፤ ያለዚያ አንተ ደግሞ ትቆረጣለህ።

23እነዚያም ደግሞ በአለማመናቸው ጸንተው ባይኖሩ በዛፉ ውስጥ ይገባሉ፤ እግዚአብሔር መልሶ ሊያገባቸው ይችላልና።

24አንተ በፍጥረቱ የበረሀ ከነበረ ወይራ ተቆርጠህ እንደ ፍጥረትህ ሳትሆን በመልካም ወይራ ከገባህ፥ ይልቁንስ እነዚያ በፍጥረታቸው ያሉት ቅርንጫፎች በራሳቸው ወይራ እንዴት አይገቡም?

25ወንድሞች ሆይ፥ ልባሞች የሆናችሁ እንዳይመስላችሁ ይህን ምሥጢር ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ፤ የአሕዛብ ሙላት እስኪገባ ድረስ ድንዛዜ በእስራኤል በአንዳንድ በኩል ሆነባቸው፤

26እንደዚሁም እስራኤል ሁሉ ይድናል፤ እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፦ “መድኃኒት ከጽዮን ይወጣል ከያዕቆብም ኃጢአተኛነትን ያስወግዳል።

27ኃጢአታቸውንም ስወስድላቸው ከእነርሱ ጋር የምገባው ኪዳን ይህ ነው።”

28በወንጌልስ በኩል ስለ እናንተ ጠላቶች ናቸው፥ በምርጫ በኩል ግን ስለ አባቶች ተወዳጆች ናቸው፤

29እግዚአብሔር በጸጋው ስጦታና በመጥራቱ አይጸጸትምና።

30እናንተም ቀድሞ ለእግዚአብሔር እንዳልታዘዛችሁ፥ አሁን ግን ከአለመታዘዛቸው የተነሣ ምሕረት እንዳገኛችሁ፥

31እንዲሁ በተማራችሁበት ምሕረት እነርሱ ደግሞ ምሕረትን ያገኙ ዘንድ እነዚህ ደግሞ አሁን አልታዘዙም።

32እግዚአብሔር ሁሉን ይምር ዘንድ ሁሉን በአለመታዘዝ ዘግቶታልና።

33የእግዚአብሔር ባለ ጠግነትና ጥበብ እውቀቱም እንዴት ጥልቅ ነው፤ ፍርዱ እንዴት የማይመረመር ነው፥ ለመንገዱም ፍለጋ የለውም።

34የጌታን ልብ ያወቀው ማን ነው?

35ወይስ አማካሪው ማን ነበር? ወይስ ብድራቱን ይመልስ ዘንድ ለእርሱ አስቀድሞ የሰጠው ማን ነው?

36ሁሉ ከእርሱና በእርሱ ለእርሱም ነውና፤ ለእርሱ ለዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን።

ማብራሪያ

፲፩፥፩-፲ በኢየሱስ ክርስቶስ የሚያምኑ የተመረጡ የአይሁድ ቅሬቶች ነበሩ፤ እነዚህም በኢየሱስ ክርስቶስ ባላቸው እምነት ጽድቅንና ሕይወትን ያገኙ ነበር። እነዚህም እንደ ጸጋ ምርጫ ተጠብቀው ነበር። ይህ ምርጫም በጸጋ ከሆነ፣ በተደረገም ሆነ አስቀድሞ በተተነበየ ሥራ ሊሆን አይችልም። በወደቀ ፍጥረት ውስጥ ያለ እውነተኛ መልካም ዝንባሌ ሁሉ በእርሱ ላይ ከዋለለት የእግዚአብሔር ጸጋ ውጤት መሆን አለበት እንጂ ምክንያት ሊሆን አይችልም። ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ያለው መዳን በጸጋ ወይም በዕዳ መሆን አለበት። እነዚህ ነገሮች እርስ በርሳቸው እጅግ ተቃራኒዎች ከመሆናቸው የተነሳ በአንድ ላይ ሊደባለቁ አይችሉም። እግዚአብሔር የዐመፀኞችን ልብና ጠባይ በመለወጥ ጸጋውን ያከብራል። ታዲያ እንዴት ሊደነቁና ሊያመሰግኑት አይገባም! የአይሁድ ሕዝብ በጥልቅ እንቅልፍ ውስጥ ነበሩ፤ የአደጋቸውን እውቀት ወይም ስለእሱ የሚያሳስባቸው ነገር ሳይኖራቸው፤ አዳኙ እንደሚያስፈልጋቸው ወይም የዘላለም ጥፋት አፋፍ ላይ መሆናቸውን ሳይገነዘቡ ነበሩ። ዳዊት በመንፈስ የክርስቶስን መከራ ከራሱ ሕዝብ ከአይሁድ ዘንድ እንደሚመጣ አስቀድሞ በመተንበይ፣ በዚህ ምክንያት በእነሱ ላይ የሚመጡትን የእግዚአብሔር አስከፊ ፍርዶች ይተነብያል (መዝ ፷፱)። ይህም ሌሎች የዳዊት በጠላቶቹ ላይ የሰጣቸውን ጸሎቶች እንዴት መረዳት እንዳለብን ያስተምረናል፤ እነሱ የእግዚአብሔር ፍርዶች ትንቢቶች እንጂ የእርሱ የራሱ ቁጣ መግለጫዎች አይደሉም። መለኮታዊ እርግማኖች ለረጅም ጊዜ ይሠራሉ፤ በዚህ ዓለም ጉዳይ ከተጠመድን ደግሞ ዓይኖቻችን ይጨልማሉ።

11:11-21 ወንጌል ባለበት ስፍራ ሁሉ ታላቅ ሀብት ነው። ስለዚህ፣ የማያምኑት አይሁዶች በትክክል ውድቅ መሆናቸው እጅግ ብዙ የአሕዛብ ብዛት ከእግዚአብሔር ጋር እንዲታረቁና ከእርሱ ጋር ሰላም እንዲያገኙ ምክንያት እንደሆነ፤ ወደፊት አይሁዶች ወደ ቤተክርስቲያን መቀበላቸው በኃጢአት የሞቱት ሁሉ ለጽድቅ ሕይወት ከሞት መነሣትን የሚመስል እንዲህ ያለ ለውጥ ይሆናል። አብርሃም የቤተክርስቲያን ሥር ነበር። አይሁዶች እንደ አንድ ሕዝብ፣ መሲሑን እስኪጥሉ ድረስ የዚህ ዛፍ ቅርንጫፎች ሆነው ቀጥለዋል፤ ከዚያ በኋላ ከአብርሃምም ሆነ ከእግዚአብሔር ጋር የነበራቸው ግንኙነት፣ እንደምሳሌ፣ ተቆረጠ። አሕዛብ በቦታቸው ወደዚህ ዛፍ ተቀጠፉ፤ ወደ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያንም ገብተዋል። እጅግ ብዙዎች የአብርሃም እምነት፣ ቅድስናና በረከት ወራሾች ሆኑ። በተፈጥሮአችን የዱር መሆናችን የሁላችንም የተፈጥሮ ሁኔታ ነው። ልብ መመለስ የዱር ቅርንጫፎችን ወደ መልካም ወይራ እንደመቅጠፍ ነው።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV I ask then: Did God reject his people? By no means! I am an Israelite myself, a descendant of Abraham, from the tribe o… English BCV እምበኣር እግዚኣብሄር ንህዝቡ ገዲፍዎም እዩዶ ኽብል? ኣይፋሉን፤ ኣነ እኳ ንባዕለይ እስራኤላዊ፥ ካብ ዘርኢ ኣብርሃም፥ ካብ ነገድ ብንያም እየ። ትግርኛ GAZBIB Egaa ani nan gaafadha, Waaqayyo saba isaa gateeraa ree? Matumaa kun ta'uu hin danda'u! Ani ofii kootii nama Israa'el, s… Afaan Oromoo BCV GIZ እብል እንከ ገደፎሙኑ እግዚአብሔር ለሕዝቡ? ሐሰ። አኮኑ አነ እስራኤላዊ አነ ዘርዐ አርብሃም እምሕዝበ ብንያም። giz GAZGAZ Egaa ani nan gaafadha, Waaqayyo saba isaa gateeraa ree? Matumaa kun ta'uu hin danda'u! Ani ofii kootii nama Israa'el, s… Afaan Oromoo BCV aksum እምበኣር እግዚኣብሄር ንህዝቡ ገዲፍዎም እዩዶ ኽብል? ኣይፋሉን፤ ኣነ እኳ ንባዕለይ እስራኤላዊ፥ ካብ ዘርኢ ኣብርሃም፥ ካብ ነገድ ብንያም እየ። ትግርኛ AMHNIV እንግዲህ እግዚአብሔር ሕዝቡን ተዋቸውን? ብዬ እጠይቃለሁ፤ በፍጹም! እኔ ራሴ ከብንያም ነገድ፣ የአብርሃም ዘር የሆንሁ እስራኤላዊ ነኝ። አማርኛ SWAHSUV Basi, nauliza, Je! Mungu aliwasukumia mbali watu wake? Hasha! Kwa kuwa mimi nami ni Mwisraeli, mmoja wa wazao wa Ibrahi… Kiswahili