ራእይ ዮሃንስ 2

AMHEVGአማርኛ28 ጥቅሶች5:02 አዳምጥ
አዳምጥ 5:02 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1“በኤፌሶን ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦ በቀኝ እጁ ሰባቱን ከዋክብት የያዘው በሰባቱም የወርቅ መቅረዞች መካከል የሚሄደው እንዲህ ይላል፦

2ሥራህንና ድካምህን ትዕግሥትህንም አውቃለሁ፤ ክፉዎችንም ልትታገሥ እንዳትችል፥ እንዲሁም ሳይሆኑ፦ ሐዋርያት ነን፡ የሚሉቱን መርምረህ ሐሰተኞች ሆነው እንዳገኘሃቸው አውቃለሁ፤

3ታግሠህማል፥ ስለ ስሜም ብለህ ጸንተህ አልደከምህም።

4ዳሩ ግን የምነቅፍብህ ነገር አለኝ፡ የቀደመውን ፍቅርህን ትተሃልና።

5እንግዲህ ከወዴት እንደ ወደቅህ አስብ ንስሐም ግባ የቀደመውንም ሥራህን አድርግ፤ አለዚያ እመጣብሃለሁ ንስሐም ባትገባ መቅረዝህን ከስፍራው እወስዳለሁ።

6ነገር ግን ይህ አለህ፤ እኔ ደግሞ የምጠላውን የኒቆላውያንን ሥራ ጠልተሃልና።

7መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ። ድል ለነሣው በእግዚአብሔር ገነት ካለው ከሕይወት ዛፍ እንዲበላ እሰጠዋለሁ።”

8“በሰምርኔስም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦ ሞቶ የነበረው ሕያውም የሆነው ፊተኛውና መጨረሻው፡ እንዲህ ይላል፦

9መከራህንና ድህነትህን አውቃለሁ፥ ነገር ግን ባለ ጠጋ ነህ፤ የሰይጣንም ማኅበር ናቸው እንጂ አይሁድ ሳይሆኑ፦ አይሁድ ነን፡ የሚሉት የሚሳደቡትን ስድብ አውቃለሁ።

10ልትቀበለው ያለህን መከራ አትፍራ። እነሆ፥ እንድትፈተኑ ዲያብሎስ ከእናንተ አንዳንዶቻችሁን በወኅኒ ሊያገባችሁ አለው፥ አሥር ቀንም መከራን ትቀበላላችሁ። እስከሞት ድረስ የታመንህ ሁን የሕይወትንም አክሊል እሰጥሃለሁ።

11መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ። ድል የነሣው በሁለተኛው ሞት አይጐዳም።”

12“በጴርጋሞንም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦ በሁለት ወገን የተሳለ ስለታም ሰይፍ ያለው እንዲህ ይላል፦

13የሰይጣን ዙፋን ባለበት የምትኖርበትን አውቃለሁ፤ ስሜንም ትጠብቃለህ፥ ሰይጣንም በሚኖርበት፥ በእናንተ ዘንድ የተገደለው የታመነው ምስክሬ አንቲጳስ በነበረበት ዘመን እንኳ ሃይማኖቴን አልካድህም።

14ዳሩ ግን ለጣዖት የታረደውን እንዲበሉና እንዲሴስኑ በእስራኤል ልጆች ፊት ማሰናከያን ሊያኖርባቸው ባላቅን ያስተማረ የበልዓምን ትምህርት የሚጠብቁ በዚያ ከአንተ ጋር ስላሉ፥ የምነቅፍብህ ጥቂት ነገር አለኝ።

15እንዲሁ የኒቆላውያንን ትምህርት እንደ እነዚህ የሚጠብቁ ሰዎች ከአንተ ጋር ደግሞ አሉ።

16እንግዲህ ንስሐ ግባ፤ አለዚያ ፈጥኜ እመጣብሃለሁ፥ በአፌም ሰይፍ እዋጋቸዋለሁ።

17መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ። ድል ለነሣው ከተሰወረ መና እሰጠዋለሁ፥ ነጭ ድንጋይንም እሰጠዋለሁ፥ በድንጋዩም ላይ ከተቀበለው በቀር አንድ ስንኳ የሚያውቀው የሌለ አዲስ ስም ተጽፎአል።”

18“በትያጥሮንም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦ እንደ እሳት ነበልባል የሆኑ ዓይኖች ያሉት በእቶንም የነጠረ የጋለ ናስ የሚመስሉ እግሮች ያሉት የእግዚአብሔር ልጅ እንዲህ ይላል፦

19ሥራህንና ፍቅርህን እምነትህንም አገልግሎትህንም ትዕግሥትህንም ከፊተኛውም ሥራህ ይልቅ የኋለኛው እንዲበዛ አውቃለሁ።

20ዳሩ ግን፦ ነቢይ ነኝ የምትለውን ባሪያዎቼንም እንዲሴስኑና ለጣዖት የታረደውን እንዲበሉ የምታስተምረውንና የምታስተውን ያችን ሴት ኤልዛቤልን ስለምትተዋት የምነቅፍብህ ነገር አለኝ፤

21ንስሐም እንድትገባ ጊዜ ሰጠኋት ከዝሙትዋም ንስሐ እንድትገባ አልወደደችም።

22እነሆ፥ በአልጋ ላይ እጥላታለሁ፥ ከእርስዋም ጋር የሚያመነዝሩትን ከሥራዋ ንስሐ ባይገቡ በታላቅ መከራ እጥላቸዋለሁ፤

23ልጆችዋንም በሞት እገድላቸዋለሁ፤ አብያተ ክርስቲያናትም ሁሉ ኵላሊትንና ልብን የምመረምር እኔ እንደ ሆንሁ ያውቃሉ፥ ለእያንዳንዳችሁም እንደ ሥራችሁ እሰጣችኋለሁ።

24ዳሩ ግን ይህን ትምህርት ለማትይዙ ሁሉ የሰይጣንንም ጥልቅ ነገር እነርሱ እንደሚሉት ለማታውቁ ለእናንተ በትያጥሮን ለቀራችሁት እላለሁ፤ ሌላ ሸክም አልጭንባችሁም፥

25ነገር ግን እስክመጣ ድረስ ያላችሁን ጠብቁ።

26ድል ለነሣውና እስከ መጨረሻም ሥራዬን ለጠበቀው እኔ ደግሞ ከአባቴ እንደ ተቀበልሁ በአሕዛብ ላይ ሥልጣንን እሰጠዋለሁ፥ በብረትም በትር ይገዛቸዋል፥ እንደ ሸክላ ዕቃም ይቀጠቀጣሉ፤

28የንጋትንም ኮከብ እሰጠዋለሁ።

29መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ።

ማብራሪያ

ራዕይ 2:1-7 እነዚህ አብያተ ክርስቲያናት በትምህርተ ሃይማኖት ንጽህና እና በሃይማኖታዊ ሕይወት ኃይል የተለያየ ሁኔታ ላይ ነበሩ፤ ስለዚህም የክርስቶስ ቃል ለእነርሱ የተሰጠው ሁልጊዜም ለሌሎች አብያተ ክርስቲያናት እና ለምእመናን ሁኔታ ተስማሚ ይሆናል። ክርስቶስ ሁኔታቸውን ያውቃል ይመለከታቸውማል፤ እርሱ በሰማይ ቢሆንም፣ በምድር ባሉት አብያተ ክርስቲያናቱ መካከል ይሄዳል፤ በእነርሱ ውስጥ ያለውን ስህተትና የጎደላቸውን ነገር ይመለከታል። የኤፌሶን ቤተ ክርስቲያን በሥራዋ ትጋት ትመሰገን ነበር። ክርስቶስ አገልጋዮቹ ለእርሱ የሚያደርጉትን እያንዳንዱን ሰዓት ሥራ ይይዛል፣ ሥራቸውም በጌታ ከንቱ አይሆንም። ነገር ግን ትጉህ መሆናችን ብቻ በቂ አይደለም፤ ታጋሽነት መኖር አለበት፣ መጠበቅ የሚችል ትዕግስትም መኖር አለበት። ለሰው ሁሉ ትህትናን ማሳየት ቢገባንም፣ በኃጢአታቸው ላይ ግን ቅን ቅንዓትን ማሳየት አለብን። ክርስቶስ ይህችን ቤተ ክርስቲያን የከሰሰባት ኃጢአት፣ የፍቅሩን መሠረት ትተው መካድ ሳይሆን፣ መጀመሪያ ላይ የነበረውን የጋለ ፍቅር ደረጃ ማጣት ነው። ክርስቶስ ሕዝቡ ለእርሱ ሲቀዘቅዙና ሲዝሉ ሲያያቸው ቅር ይሰኘባቸዋል። በእርግጥ፣ ይህ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ክርስቲያኖች የመጀመሪያ ፍቅራቸውን እንደተዉ የተጠቀሰው ቃል፣ ስለ ጉዳዩ በቸልታ የሚናገሩትን፣ እና በዚህም በእነርሱ እና በሌሎች ውስጥ ያለውን ግዴለሽነትና ስንፍና ለማስረዳት የሚሞክሩትን ይገሥጻል፤ መድኃኒታችን ይህንን ግዴለሽነት ኃጢአት አድርጎ ይቆጥረዋል። ንስሐ መግባት አለባቸው፤ ስለ ኃጢአት መዳከማቸው ማዘንና ማፈር፣ በእግዚአብሔር ፊትም በትህትና መናዘዝ አለባቸው። የመጀመሪያ ትጋታቸውን፣ ርኅራኄአቸውን እና ቁምነገረኝነታቸውን ለማስመለስ ሙሉ በሙሉ መጣር አለባቸው፤ እንዲሁም በእግዚአብሔር መንገድ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደወጡት ሁሉ በቅንዓት መጸለይ እና በትጋት መጠንቀቅ አለባቸው። የክርስቶስ ጸጋና የመንፈሱ መገኘት ችላ ከተባለ፣ የእርሱን ቁጣ መገኘት እንጠብቅ ይሆናል። በእነርሱ መካከል መልካም የነበረው ነገር በአድናቆት ተጠቅሷል። ለእውነትና ለስህተት፣ ለበጎና ለክፉ ግድየለሽነት ምናልባት ፍቅርና ትህትና ተብሎ ሊጠራ ይችላል፣ ግን እንደዚያ አይደለም፤ ለክርስቶስም ደስ አያሰኝም። የክርስቲያን ሕይወት በኃጢአት፣ በሰይጣን፣ በዓለምና በሥጋ ላይ የሚደረግ መንፈሳዊ ውጊያ ነው። ለመንፈሳዊ ጠላቶቻችን ፈጽሞ መገዛት የለብንም፣ ያን ጊዜም የከበረ ድልና ሽልማት እናገኛለን። ጽኑዓን ሁሉ ከክርስቶስ፣ ከሕይወት ዛፍ እንደመሆኑ መጠን፣ በቅድስና እና በደስታ ውስጥ ፍጹምነትንና ማረጋገጫን ያገኛሉ፤ በምድራዊ ገነት ሳይሆን፣ በሰማያዊው። ይህ ከኤደን ገነት ታሪክ የተወሰደ ምሳሌያዊ አነጋገር ነው፤ የሰማይን ንጹህ፣ አርኪ እና ዘላለማዊ ደስታዎች የሚያመለክት፤ በዚህ ዓለምም በእምነት፣ ከክርስቶስ ጋር ባለው ህብረትና በመንፈስ ቅዱስ በሚሰጠው መጽናናት ወደ እነዚህ ደስታዎች በጉጉት መጠበቅን ነው። ምእመናን ሆይ፣ የትግል ሕይወታችሁን እዚህ ተቀበሉ፣ ከዚህ በኋላም ጸጥ ያለ ሕይወትን ጠብቁና ፈልጉ፤ ግን እስከዚያው ድረስ አይደለም፤ የእግዚአብሔር ቃል እዚህ (ምድር) ላይ ጸጥታንና ከግጭት ሙሉ በሙሉ ነጻ መሆንን ፈጽሞ ቃል አይገባም።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV “To the angel of the church in Ephesus write: These are the words of him who holds the seven stars in his right hand an… English BCV “ናብ መልኣኽ ቤተ ክርስቲያን ኤፌሶን፥ ከምዙይ ኢልካ ፀሓፍ፦ “ ‘እቲ ኣብ የማናይ ኢዱ፥ ሸውዓተ ኸዋኽብቲ ዝሓዘ፥ ኣብ ማእኸል እተን ሸውዓተ ቐወምቲ ናይ ወርቂ ቐናዲል ዝመላለስ፥ ከምዙይ … ትግርኛ GAZBIB ?Gara ergamaa waldaa Efesoonitti, ?Ergaan kun kan isa harka isaa mirgaatiin urjoota torban qabee, baattuu ibsaa torban … Afaan Oromoo BCV GIZ “ወጸሐፍ ሎቱ ለመልአከ ቤተ ክርስቲያን ዘኤፌሶን፣ ከመዝ ይቤለከ አኃዜ ኵሉ ዘያጸንዕ ሰብዐተ ከዋክብተ በየማኑ ወዘየሐውር በማእከለ ሰብዑ መኃትው ዘወርቅ። giz GAZGAZ ?Gara ergamaa waldaa Efesoonitti, ?Ergaan kun kan isa harka isaa mirgaatiin urjoota torban qabee, baattuu ibsaa torban … Afaan Oromoo BCV aksum “ናብ መልኣኽ ቤተ ክርስቲያን ኤፌሶን፥ ከምዙይ ኢልካ ፀሓፍ፦ “ ‘እቲ ኣብ የማናይ ኢዱ፥ ሸውዓተ ኸዋኽብቲ ዝሓዘ፥ ኣብ ማእኸል እተን ሸውዓተ ቐወምቲ ናይ ወርቂ ቐናዲል ዝመላለስ፥ ከምዙይ … ትግርኛ AMHNIV “በኤፌሶን ላለው ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፤ ሰባቱን ከዋክብት በቀኝ እጁ የያዘው፣ በሰባቱም የወርቅ መቅረዞች መካከል የሚመላለሰው እንዲህ ይላል፤ አማርኛ SWAHSUV Kwa malaika wa kanisa lililoko Efeso andika; Haya ndiyo anenayo yeye azishikaye hizo nyota saba katika mkono wake wa ku… Kiswahili