ራእይ ዮሃንስ 13

AMHEVGአማርኛ18 ጥቅሶች3:23 አዳምጥ
አዳምጥ 3:23 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1አንድም አውሬ ከባሕር ሲወጣ አየሁ፤ አሥር ቀንዶችና ሰባት ራሶች ነበሩት፥ በቀንዶቹም ላይ አሥር ዘውዶች በራሶቹም ላይ የስድብ ስም ነበረ።

2ያየሁትም አውሬ ነብር ይመስል ነበር፥ እግሮቹም እንደ ድብ እግሮች፥ አፉም እንደ አንበሳ አፍ ነበሩ። ዘንዶውም ኃይሉንና ዙፋኑን ትልቅም ሥልጣን ሰጠው።

3ከራሶቹም ለሞት እንደ ታረደ ሆኖ አንዱን አየሁ፥ ለሞቱ የሆነውም ቍስል ተፈወሰ። ምድርም ሁሉ አውሬውን እየተከተለ ተደነቀ፥

4ለዘንዶውም ሰገዱለት፥ ለአውሬው ሥልጣንን ሰጥቶታልና፤ ለአውሬውም፦ “አውሬውን ማን ይመስለዋል፥ እርሱንስ ሊዋጋ ማን ይችላል?” እያሉ ሰገዱለት።

5ታላቅንም ነገርና ስድብን የሚናገርበት አፍ ተሰጠው፥ በአርባ ሁለት ወርም እንዲሠራ ሥልጣን ተሰጠው።

6እግዚአብሔርንም ለመሳደብ ስሙንና ማደሪያውንም በሰማይም የሚያድሩትን ሊሳደብ አፉን ከፈተ።

7ቅዱሳንንም ይዋጋ ዘንድ ድልም ያደርጋቸው ዘንድ ተሰጠው፥ በነገድና በወገንም በቋንቋም በሕዝብም ሁሉ ላይ ሥልጣን ተሰጠው።

8ከዓለምም ፍጥረት ጀምሮ በታረደው በግ ሕይወት መጽሐፍ ስሞቻቸው ያልተጻፉ በምድር የሚኖሩ ሁሉ ይሰግዱለታል።

9ጆሮ ያለው ቢኖር ይስማ።

10ይማረክ ዘንድ ያለው ማንም ቢኖር ወደ ምርኮነት ይሄዳል፤ በሰይፍ የሚገድል ማንም ቢኖር ራሱ በሰይፍ እንዲገደል ይገባዋል። የቅዱሳን ትዕግሥትና እምነት በዚህ ነው።

11ሌላም አውሬ ከምድር ሲወጣ አየሁ፥ የበግ ቀንዶችን የሚመስሉ ሁለት ቀንዶችም ነበሩት እንደ ዘንዶም ይናገር ነበር።

12በፊተኛውም አውሬ ሥልጣን በእርሱ ፊት ሁሉን ያደርጋል። ለሞቱ የሆነውም ቍስል ተፈወሰለት ለፊተኛው አውሬ ምድርና በእርሱ የሚኖሩት እንዲሰግዱለት ያደርጋል።

13እሳትንም እንኳ ከሰማይ ወደ ምድር በሰው ፊት እስኪያወርድ ድረስ ታላላቆችን ምልክቶች ያደርጋል።

14በአውሬውም ፊት ያደርግ ዘንድ ከተሰጡት ምልክቶች የተነሣ በምድር የሚኖሩትን ያስታል፤ የሰይፍም ቍስል ለነበረውና በሕይወት ለኖረው ለአውሬው ምስልን እንዲያደርጉ በምድር የሚኖሩትን ይናገራል።

15የአውሬው ምስል ሊናገር እንኳ ለአውሬውም ምስል የማይሰግዱለትን ሁሉ ሊያስገድላቸው፥ ለአውሬው ምስል ትንፋሽ እንዲሰጠው ተሰጠው።

16ታናናሾችና ታላላቆችም ባለ ጠጋዎችና ድሆችም ጌታዎችና ባሪያዎችም ሁሉ በቀኝ እጃቸው ወይም በግምባራቸው ምልክትን እንዲቀበሉ፥

17የአውሬውም ስም ወይም የስሙ ቍጥር ያለው ምልክት የሌለበት ማንም ሊገዛ ወይም ሊሸጥ እንዳይችል ያደርጋል። ጥበብ በዚህ አለ።

18አእምሮ ያለው የአውሬውን ቍጥር ይቍጠረው፤ ቍጥሩ የሰው ቍጥር ነውና፥ ቍጥሩም ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት ነው።

ማብራሪያ

13:1-10 ሐዋርያው በባሕር ዳር ቆሞ ከባሕር ሲወጣ አንድ ጨካኝ አውሬ አየ፤ ይህ አውሬ የተከሰቱትን ችግሮች ተከትሎ የተነሳ ጨካኝ፣ ጣዖትን የሚያመልክና የሚያሳድድ ኃይል ነበር። አስፈሪ ጭራቅ ነበር! ይህ አውሬ ለብዙ ዘመናት፣ ከባቢሎን ምርኮ ዘመን ጀምሮም፣ ለቤተ ክርስቲያን ጠላት የነበረውን ዓለማዊ፣ ጨቋኝ ግዛት የሚያመለክት ይመስላል። የመጀመሪያው አውሬም ጻድቃንን ስለ ጽድቅ ማሰቃየትና ማሳደድ ጀመረ፤ ነገር ግን እነርሱ እጅግ የተሰቃዩት በዳንኤል አራተኛው አውሬ (በሮም ግዛት) ሥር ሲሆን፣ እሱም ቅዱሳንን በብዙ አሰቃቂ ስደቶች አሰቃይቷል።

የዚህ ኃይል ምንጭ ዘንዶው ነበር። በዲያብሎስ ተመሥርቶ በእሱም ይደገፍ ነበር። ራሱን መቁሰል የአረማዊውን ጣዖት አምልኮ ማጥፋት ሊሆን ይችላል፤ የቁስሉ መዳን ደግሞ በባሕርይው ተመሳሳይ የሆነውን፣ በአዲስ መልክ ብቻ የቀረበውን የጵጵስና ጣዖት አምልኮን ማስተዋወቅ ሲሆን፣ ይህም የዲያብሎስን ዓላማ ሙሉ በሙሉ የሚያሳካ ነበር።

ዓለም ኃይሉን፣ ብልሃቱንና ስኬቱን አደነቀ። ለዲያብሎስና ለመሣሪያዎቹ ክብርና መገዛት ሰጡ። ለፍጥረታት ብቻ ለእግዚአብሔር ብቻ የሚገባውን ክብር እንዲሰጡ ሰዎችን የሚያስገድድ የሲኦል ኃይልና ብልሃት ይጠቀም ነበር። ሆኖም የዲያብሎስ ኃይልና ስኬት የተገደበ ነው። ክርስቶስ በደሙ የዳኑ (በቤዛነት)፣ በመጽሐፉ የተጻፉ፣ በመንፈሱ የታተሙ የተመረጠ ቀሪ ክፍል አለው፤ ዲያብሎስና የክርስቶስ ተቃዋሚ አካልን ሊያሸንፉና የተፈጥሮን ሕይወት ሊወስዱ ቢችሉም፣ ነፍስን ግን ሊያሸንፉ አይችሉም፣ እንዲሁም እውነተኛ አማኞችን አዳኛቸውን ትተው ከጠላቶቹ ጋር እንዲቀላቀሉ ሊያሳምኑ አይችሉም።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV And the dragon stood on the shore of the sea. And I saw a beast coming out of the sea. He had ten horns and seven heads… English BCV ሓደ ኣራዊት፥ ካብ ባሕሪ ኽወፅእ እንተሎ ረአኹ። ንሱ ዓሰርተ ኣቕርንትን ሸውዓተ ኣራእስን ነበሮ። ኣብ ኣቕርንቱ ዓሰርተ ዘውዲ፥ ኣብ ኣራእሱውን ስማት ፀርፊ ነበሮ። ትግርኛ GAZBIB Kana booddee immoo bineensi tokko galaana keessaa utuu ba'uu nan arge; bineensichis gaanfa kudhanii fi mataa torba, gaa… Afaan Oromoo BCV GIZ ወወፅአ ካልእ አርዌ እምነ ባሕር፤ ዘዐሠርቱ አቅርንቲሁ ወሰብዐቱ አርእስቲሁ፤ ወውስተ አቅርንቲሁ ዐሠርቱ ቀጸላ፤ ወውስተ አርእስቲሁ ስመ ፅርፈት። giz GAZGAZ Kana booddee immoo bineensi tokko galaana keessaa utuu ba'uu nan arge; bineensichis gaanfa kudhanii fi mataa torba, gaa… Afaan Oromoo BCV aksum እቲ ገበል ድማ፥ ኣብ ልዕሊ እቲ ወሰን ባሕሪ ዘሎ ሑፃ ደው በለ። ሓደ ኣራዊት፥ ካብ ባሕሪ ኽወፅእ እንተሎ ረአኹ። ንሱ ዓሰርተ ኣቕርንትን ሸውዓተ ኣራእስን ነበሮ። ኣብ ኣቕርንቱ ዓሰርተ ዘ… ትግርኛ AMHNIV ዘንዶውም በባሕሩ ዳር ቆሞ ነበር። ከዚያም አንድ አውሬ ከባሕር ሲወጣ አየሁ፤ እርሱም ዐሥር ቀንዶችና ሰባት ራሶች ነበሩት፤ በቀንዶቹም ላይ ዐሥር ዘውዶች፣ በራሶቹም ላይ የስድብ ስሞች ነበሩ… አማርኛ SWAHSUV Kisha nikaona mnyama akitoka katika bahari, mwenye pembe kumi, na vichwa saba, na juu ya pembe zake ana vilemba kumi, n… Kiswahili