መጽሐፈ ምሳሌ 15

AMHNIVአማርኛ33 ጥቅሶች4:08 አዳምጥ
አዳምጥ 4:08 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1የለዘበ መልስ ቊጣን ያበርዳል፤ ክፉ ቃል ግን ቊጣን ይጭራል።

2የጠቢብ አንደበት ዕውቀትን ታወድሳለች፤ የተላሎች አንደበት ግን ቂልነትን ያፈልቃል።

3የእግዚአብሔር ዐይኖች በሁሉም ስፍራ ናቸው፤ ክፉዎችንም ደጎችንም ነቅተው ይመለከታሉ።

4ፈውስ የምታመጣ ምላስ የሕይወት ዛፍ ናት፤ አታላይ ምላስ ግን መንፈስን ትሰብራለች።

5ተላላ የአባቱን ምክር ይንቃል፤ መታረምን የሚቀበል ግን አስተዋይነቱን ያሳያል።

6የጻድቃን ቤት በብዙ ሀብት የተሞላ ነው፤ የክፉዎች ገቢ ግን መከራን ታመጣባቸዋለች።

7የጠቢባን ከንፈር ዕውቀትን ታስፋፋለች፤ የተላሎች ልብ ግን እንዲህ አይደለም።

8እግዚአብሔር የክፉዎችን መሥዋዕት ይጸየፋል፤ የቅኖች ጸሎት ግን ደስ ያሰኘዋል።

9እግዚአብሔር የክፉዎችን መንገድ ይጸየፋል፤ ጽድቅን የሚከታተሉትን ግን ይወዳቸዋል።

10ከመንገድ የሚወጣ ሰው ጥብቅ ቅጣት ይጠብቀዋል፤ ዕርምትን የሚጠላ ይሞታል።

11ሲኦልና የሙታን ዓለም በእግዚአብሔር ፊት የተገለጡ ናቸው፤ የሰዎች ልብ ማየቱን ያህል የታወቀ ነው!

12ፌዘኛ መታረምን ይጠላል፤ ጠቢባንንም አያማክርም።

13ደስተኛ ልብ ፊትን ያፈካል፤ የልብ ሐዘን ግን መንፈስን ይሰብራል።

14አስተዋይ ልብ ዕውቀትን ይሻል፤ የተላላ አፍ ግን ቂልነትን ያመነዥካል።

15የተጨቈኑ ሰዎች ዘመናቸው ሁሉ የከፋ ነው፤ በደስታ የተሞላ ልብ ግን የማይቋረጥ ፈንጠዝያ አለው።

16እግዚአብሔርን ከመፍራት ጋር ያለ ጥቂት ነገር፣ ሁከት ካለበት ትልቅ ሀብት ይበልጣል።

17ፍቅር ባለበት ጐመን መብላት፣ ጥላቻ ባለበት የሰባ ፍሪዳ ከመብላት ይሻላል።

18ግልፍተኛ ሰው ጠብ ያነሣሣል፤ ታጋሽ ሰው ግን ጠብን ያበርዳል።

19የሀኬተኛ መንገድ በእሾህ የታጠረች ናት፤ የቅኖች መንገድ ግን የተጠረገ አውራ ጐዳና ነው።

20ጠቢብ ልጅ አባቱን ደስ ያሰኛል፤ ተላላ ሰው ግን እናቱን ይንቃል።

21ማመዛዘን የጐደለው ሰው ቂልነት ያስደስተዋል፤ አስተዋይ ሰው ግን ቀጥተኛውን መንገድ ይከተላል።

22ምክር ሲጓደል ዕቅድ ይፋለሳል፤ በብዙ አማካሪዎች ግን ይሳካል።

23ሰው ተገቢ መልስ በመስጠት ደስታን ያገኛል፤ በወቅቱም የተሰጠ ቃል ምንኛ መልካም ነው!

24ወደ ሲኦል ከመውረድ እንዲድን፣ የሕይወት መንገድ ጠቢቡን ሰው ወደ ላይ ትመራዋለች።

25እግዚአብሔር የትዕቢተኛውን ቤት ያፈርሰዋል፤ የመበለቲቱን ዳር ድንበር ግን እንዳይደፈር ይጠብቃል።

26እግዚአብሔር የክፉውን ሰው ሐሳብ ይጸየፋል፤ የንጹሓን ሐሳብ ግን ደስ ያሰኘዋል።

27ስስታም ሰው በቤተ ሰቡ ላይ ችግር ያመጣል፤ ጒቦን የሚጠላ ግን በሕይወት ይኖራል።

28የጻድቅ ሰው ልብ የሚሰጠውን መልስ ያመዛዝናል፤ የክፉ ሰው አፍ ግን ክፋትን ያጐርፋል።

29እግዚአብሔር ከክፉዎች ሩቅ ነው፤ የጻድቃንን ጸሎት ግን ይሰማል።

30ብሩህ ገጽታ ልብን ደስ ያሰኛል፤ መልካም ዜናም ዐጥንትን ያለመልማል።

31ሕይወት ሰጪ የሆነውን ተግሣጽ የሚሰማ፣ በጠቢባን መካከል ይኖራል።

32ተግሣጽን የሚንቅ ራሱን ይንቃል፤ ዕርምትን የሚቀበል ግን ማስተዋልን ያገኛል።

33እግዚአብሔርን መፍራት ጥበብን መማር ነው፤ ትሕትናም ክብርን ትቀድማለች።

ማብራሪያ

1. ቅን የሆነን ጉዳይ በገርነት ማቅረብ ከስሜታዊ ንግግር ይልቅ ይበልጥ ውጤታማ ነው። እንደሚያስከፉ ቃላት ቊጣን የሚያነሳሳ ምንም የለም። 2. ዕውቀት ያለው ሁሉ በትክክል ለሌሎች መልካም ሊጠቀምበት ይገባል።

15:3. የተሰወሩ ኃጢአቶች፣ አገልግሎቶች፣ እና ሐዘኖች ሁሉ በእግዚአብሔር ዐይን ፊት ናቸው። ይህ ለቅዱሳን መጽናናትን ሲሰጥ፣ ለኃጢአተኞች ግን ፍርሃት ነው። 15:4. መልካም ምላስ ለቆሰሉ ሕሊናዎች በማጽናናት ፈዋሽ ሲሆን፣ በኃጢአት የታመሙ ነፍሳትንም በማሳመን ትፈውሳለች። በተጨማሪም የተጣሉ ወገኖችን ታስታርቃለች። 15:5. ትምህርት ከተናቀ፣ ሰዎች ወደ ጥፋት መንገድ ሳይረበሹ እንዲሄዱ ከመፍቀድ ይልቅ ገሥጹአቸው። 15:6. የዓለማዊያን ሰዎች ሀብት ፍርሃታቸውንና ጥርጣሬያቸውን ያበዛል፣ ለስሜቶቻቸውም ኃይል ይጨምራል፣ የሞትንም ፍርሃት ይበልጥ አስጨናቂ ያደርገዋል። 15:7. እውቀትን በአግባቡ የምንጠቀመው ስንበትነው ነው። የሰነፍ ልብ ግን ሊበትነው የሚችል መልካም ነገር የለውም። 15:8,9. ክፉዎች በክርስቶስ ቤዛነት ፋንታ፣ ወይም በቅዱስ መታዘዝ ቦታ ሌሎች ነገሮችን ያቀርባሉ። የጸሎት ጸጋዎች የእርሱ ስጦታ፣ የመንፈሱም ሥራ ናቸው፤ በዚህም ደስ ይሰኛል። 15:10. ተግሳጽን የሚጠላ ሰው፣ ከኃጢአቶቹ ሊለይ ስላልፈለገ፣ በኃጢአቶቹ ውስጥ ይጠፋል።

15:11.

ከእግዚአብሔር ዐይን የሚሰወር ምንም ነገር የለም፤ የሰው ሐሳብ ሳይቀር። 12. ፌዘኛ በልቡ ውስጥ በቁም ነገር ሊያሰላስል አይችልም። 13. ከትዕቢትና ለዓለማዊ ነገሮች ካለው ከልክ ያለፈ ቁርኝት የተነሣ የሚመነጭ የጨለመ፣ ትዕግሥት የሌለውና የማያመሰግን መንፈስ፣ ሰውን ለራሱም ሆነ ለሌሎች እረፍት ያሳጣል።

ምዕራፍ ፲፭፥፲፬።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6