መጽሐፈ ምሳሌ 14

AMHNIVአማርኛ35 ጥቅሶች4:20 አዳምጥ
አዳምጥ 4:20 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ጠቢብ ሴት ቤቷን ትሠራለች፤ ተላላ ሴት ግን በገዛ እጇ ታፈርሰዋለች።

2አካሄዱ ቅን የሆነ ሰው እግዚአብሔርን ይፈራል፤ መንገዱ ጠማማ የሆነ ግን ይንቀዋል።

3የተላላ ሰው ንግግር ለጀርባው በትር ታስከትልበታለች፤ የጥበበኛ ከንፈር ግን ትጠብቃቸዋለች።

4በሬዎች በሌሉበት ገንዳው ባዶ ይሆናል፤ በበሬ ጒልበት ግን ብዙ ምርት ይገኛል።

5ታማኝ ምስክር አይዋሽም፤ ሐሰተኛ ምስክር ግን ውሸትን ይዘከዝካል።

6ፌዘኛ ጥበብን ይሻል፤ ሆኖም አያገኛትም፤ ዕውቀት ግን ለአስተዋዮች በቀላሉ ትገኛለች።

7ከተላላ ሰው ራቅ፤ ከከንፈሮቹ ዕውቀት አታገኝምና።

8የአስተዋዮች ጥበብ መንገዳቸውን ልብ ማለት ነው፤ የተላሎች ሞኝነት ግን መታለል ነው።

9ተላሎች በሚያቀርቡት የበደል ካሳ ያፌዛሉ፤ በቅኖች መካከል ግን በጎ ፈቃድ ትገኛለች።

10እያንዳንዱ ልብ የራሱን መራራ ሐዘን ያውቃል፤ ደስታውንም ማንም ሊጋራው አይችልም።

11የክፉዎች ቤት ይፈርሳል፤ የቅኖች ድንኳን ግን ይስፋፋል።

12ለሰው ቀና መስሎ የሚታይ መንገድ አለ፤ በመጨረሻ ግን ወደ ሞት ያደርሳል።

13በሣቅ ጊዜ እንኳ ልብ ይተክዛል፤ ደስታም በሐዘን ሊፈጸም ይችላል።

14ልባቸውን ከጽድቅ የሚመልሱ የእጃቸውን ሙሉ ዋጋ ይቀበላሉ፤ ደግ ሰውም ወሮታውን ያገኛል።

15ተላላ ሰው ሁሉን ያምናል፤ አስተዋይ ግን ርምጃውን ያስተውላል።

16ጠቢብ ሰው ጥንቁቅ ነው፤ ከክፉም ይርቃል፤ ተላላ ግን ችኵልና ደንታ ቢስ ነው።

17ግልፍተኛ ሰው የቂል ተግባር ይፈጽማል፤ መሠሪም ሰው አይወደድም።

18ብስለት የሌላቸው ተላላነትን ይወርሳሉ፤ አስተዋዮች ግን ዕውቀትን እንደ ዘውድ ይጭናሉ።

19ክፉዎች በደጎች ፊት፣ ኀጥኣንም በጻድቃን ደጅ ያጐነብሳሉ።

20ድኾችን ወዳጆቻቸው እንኳ ይጠሏቸዋል፤ ባለጠጎች ግን ብዙ ወዳጆች አሏቸው።

21ጎረቤቱን የሚንቅ ኀጢአት ይሠራል፤ ለተቸገሩት የሚራራ ግን ቡሩክ ነው።

22ክፉ ነገር የሚያቅዱ ከትክክለኛው መንገድ ይወጡ የለምን? በጎ ነገር የሚያቅዱ ግን ፍቅርንና ታማኝነትን ያተርፋሉ።

23ለፍተው የሠሩት ሁሉ ትርፍ ያስገኛል፤ ከንቱ ወሬ ግን ወደ ድኽነት ያመራል።

24ጠቢባን ብልጥግና ዘውዳቸው ነው፤ የተላሎች ተላላነት ግን ፍሬው ከንቱነት ነው።

25እውነተኛ ምስክር ሕይወት ያድናል፤ ሐሰተኛ ምስክር ግን አባይ ነው።

26እግዚአብሔርን የሚፈራ ጽኑ አምባ አለው፤ ልጆቹም መጠጊያ ይኖራቸዋል።

27እግዚአብሔርን መፍራት የሕይወት ምንጭ ነው፤ ሰውን ከሞት ወጥመድ ያድነዋል።

28የሕዝብ ብዛት የንጉሥ ክብር ሲሆን፣ የዜጐች ማነስ ግን ለገዥ መጥፊያው ነው።

29ታጋሽ ሰው ትልቅ ማስተዋል አለው፤ ግልፍተኛ ሰው ግን ቂልነትን ይገልጣል።

30ሰላም ያለው ልብ ለሰውነት ሕይወት ይሰጣል፤ ቅናት ግን ዐጥንትን ያነቅዛል።

31ድኾችን የሚያስጨንቅ ፈጣሪያቸውን ይንቃል፤ ለተቸገሩ የሚራራ ሁሉ ግን አምላክን ያከብራል።

32ክፉዎች በክፋታቸው ይወድቃሉ፤ ጻድቃን ግን በሞት ጊዜ እንኳ መጠጊያ አላቸው።

33ጥበብ በአስተዋዮች ልብ ታድራለች፤ በተላሎች መካከል ራሷን ትገልጣለች።

34ጽድቅ ሕዝብን ከፍ ከፍ ታደርጋለች፤ ኀጢአት ግን ለየትኛውም ሕዝብ ውርደት ነው።

35ጠቢብ አገልጋይ ንጉሥን ደስ ያሰኛል፤ አሳፋሪ አገልጋይ ግን ቊጣውን በራሱ ላይ ያመጣል።

ማብራሪያ

14:1 እግዚአብሔርን የማትፈራ፣ የገዛ ፈቃዷን የምትከተልና አባካኝ የሆነች፣ እንዲሁም ለራሷ ምቾት የምትገዛ ሴት ቤቷን እንደምታፈርስ ሁሉ ቤተሰቧንም በእርግጥ ታፈርሳለች።

2. እውነተኛ የጸጋና የኃጢአት መልክ እዚህ ይታያል። የእግዚአብሔርን ትእዛዛትና ተስፋዎች የሚንቁ ሰዎች እግዚአብሔርን፣ ሁሉንም ኀይሉንና ምሕረቱንም ይንቃሉ።

3. ትዕቢት በልብ ውስጥ ካለው የመራርነት ሥር ይበቅላል። ያ ሥር መነቀል አለበት፤ አለዚያም ይህንን ቅርንጫፍ ማሸነፍ አንችልም። የጠቢባን ጥንቁቅ ቃላት ከችግሮች ያወጧቸዋል።

4. ትንሽ ነገር ቢሆንም እንኳ ሰነፉን የሚያስፈራ ነገር ከሌለ ምንም ጥቅም ሊገኝ አይችልም።

5. ኅሊናዊ ምስክር ከሚያውቀው ውጪ የሆነን ነገር ለመግለጽ አይደፍርም።

6. ተሳዳቢ መለኮታዊ ነገሮችን በንቀት ይመለከታል። የራሱን ድንቁርናና ብቁ አለመሆን የተረዳ ሰው ግን መጻሕፍትን በትሑት መንፈስ ይመረምራል።

7. ንግግሩ የአምልኮ መንፈስ የሌለው ከሆነ ክፉ ሰውን እናውቃለን።

8. እኛ ተጓዦች ነን፤ ጭንቀታችንም ድንቆችን መመልከት ሳይሆን ጉዟችንን ወደ ፍጻሜ ማድረስ ነው። የምንሄድባቸውን ሕጎች፣ እንዲሁም የምንሄድላቸውን መዳረሻዎች መረዳት ይገባናል። ክፉ ሰው ራሱን ያታልላል፣ በስህተቱም ይቀጥላል።

9. ሰነፎችና ሃይማኖት የለሾች ሰዎች ኃጢአትን ቀላል ነገር አድርገው ይመለከታሉ፤ ሊያዝኑበት ይልቅ ሊያቃልሉት ይመርጣሉ። ሰነፎች በኃጢአት መሥዋዕት ያፌዛሉ፤ ነገር ግን ኃጢአትን ቀላል አድርገው የሚመለከቱ ክርስቶስንም ቀላል አድርገው ይመለከቱታል።

10. የበለጸገውን ኃጢአተኛ የሚያሠቃዩትን የኅሊና ውጋቶች ወይም የሚያቃጥሉ ምኞቶች አናውቅም። እንዲሁም ዓለም በድህነትና በበሽታ ውስጥ እንኳ በቁም ነገር ያለ ክርስቲያን የሚያገኘውን የአእምሮ ሰላም አያውቅም።

11.

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6