ወደ ፊልጵስዩስ 2

AMHEVGአማርኛ29 ጥቅሶች3:44 አዳምጥ
አዳምጥ 3:44 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1በክርስቶስም አንዳች ምክር ቢሆን፥ የፍቅር መጽናናት ቢሆን፥ የመንፈስ ኅብረት ቢሆን፥ ምሕረትና ርኅራኄ ቢሆኑ፥ ደስታዬን ፈጽሙልኝ፤

2በአንድ አሳብ ተስማሙ፥ አንድ ፍቅር አንድም ልብ አንድም አሳብ ይሁንላችሁ፤

3ለወገኔ ይጠቅማል በማለት ወይም በከንቱ ውዳሴ ምክንያት አንድ እንኳ አታድርጉ፥ ነገር ግን እያንዳንዱ ባልንጀራው ከራሱ ይልቅ እንዲሻል በትሕትና ይቍጠር፤

4እያንዳንዱ ለራሱ የሚጠቅመውን አይመልከት፥ ለባልንጀራው ደግሞ እንጂ።

5በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረ ይህ አሳብ በእናንተ ዘንድ ደግሞ ይሁን።

6እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቈጠረውም፥

7ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ፥

8በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፥ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ።

9በዚህ ምክንያት ደግሞ እግዚአብሔር ያለ ልክ ከፍ ከፍ አደረገው፥ ከስምም ሁሉ በላይ ያለውን ስም ሰጠው፤

10ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ፥

11መላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደ ሆነ ይመሰክር ዘንድ ነው።

12ስለዚህ፥ ወዳጆቼ ሆይ፥ ሁልጊዜ እንደ ታዘዛችሁ፥ በእናንተ ዘንድ በመኖሬ ብቻ ሳይሆን ይልቁን አሁን ስርቅ፥ በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ፤

13ስለ በጎ ፈቃዱ መፈለግንም ማድረግንም በእናንተ የሚሠራ እግዚአብሔር ነውና።

14በመጥፎና በጠማማ ትውልድ መካከል ያለ ነቀፋ የዋሆችም ነውርም የሌለባቸው የእግዚአብሔር ልጆች እንድትሆኑ ሳታንጐራጉሩ ክፉም ሳታስቡ ሁሉን አድርጉ፤

16በእነርሱም መካከል የሕይወትን ቃል እያቀረባችሁ በዓለም እንደ ብርሃን ትታያላችሁ፥ ስለዚህም በከንቱ እንዳልሮጥሁ በከንቱም እንዳልደከምሁ በክርስቶስ ቀን የምመካበት ይሆንልኛል።

17ነገር ግን በእምነታችሁ መሥዋዕትና አገልግሎት ተጨምሬ ሕይወቴ እንኳ ቢፈስ፥ ደስ ብሎኛል፤ ከሁላችሁም ጋር አብሬ ደስ ብሎኛል፤

18እናንተም ደግሞ እንዲሁ ደስ ይበላችሁ ከእኔም ጋር አብራችሁ ደስ ይበላችሁ።

19ነገር ግን ኑሮአችሁን ሳውቅ እኔ ደግሞ ደስ እንዲለኝ ፈጥኜ ጢሞቴዎስን ልልክላችሁ በጌታ በኢየሱስ ተስፋ አደርጋለሁ።

20እንደ እርሱ ያለ፥ ስለ ኑሮአችሁ በቅንነት የሚጨነቅ፥ ማንም የለኝምና፤

21ሁሉ የራሳቸውን ይፈልጋሉና፥ የክርስቶስ ኢየሱስን አይደለም።

22ነገር ግን ልጅ ለአባቱ እንደ ሚያገለግል ከእኔ ጋር ሆኖ ለወንጌል እንደ አገለገለ መፈተኑን ታውቃላችሁ።

23እንግዲህ እንዴት እንደምሆን ባየሁ ጊዜ፥ እርሱን ቶሎ እንድልክ ተስፋ አደርጋለሁ፤

24ራሴ ደግሞ ግን ፈጥኜ እንድመጣ በጌታ ታምኜአለሁ።

25ነገር ግን ወንድሜንና ከእኔ ጋር አብሮ ሠራተኛ ወታደርም የሚሆነውን፥ የእናንተ ግን መልእክተኛ የሆነውና የሚያስፈልገኝን የሚያገለግለውን አፍሮዲጡን እንድልክላችሁ በግድ አስባለሁ፤

26ሁላችሁን ይናፍቃልና፥ እንደ ታመመም ስለ ሰማችሁ ይተክዛል።

27በእውነት ታሞ ለሞት እንኳ ቀርቦ ነበርና፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ማረው፥ ኀዘን በኀዘን ላይ እንዳይጨመርብኝ ለእኔ ደግሞ እንጂ ለእርሱ ብቻ አይደለም።

28እንግዲህ እንደ ገና ስታዩት ደስ እንዲላችሁ ለእኔም ኀዘኔ እንዲቃለል በብዙ ፍጥነት እልከዋለሁ።

29እንግዲህ በሙሉ ደስታ በጌታ ተቀበሉት፥ እርሱን የሚመስሉትንም አክብሩአቸው፤

30በእኔ ዘንድ ካላችሁ አገልግሎት እናንተ ስለሌላችሁ የጎደለኝን እንዲፈጽም፥ በነፍሱ ተወራርዶ ከጌታ ሥራ የተነሣ እስከ ሞት ቀርቦአልና።

ማብራሪያ

2:1-4 በዚህ ክፍል ለክርስትና ተግባራት፤ በተለይም በጌታችን በኢየሱስ ምሳሌ መሠረት ለአንድ ልብ መሆንና ለትሕትና መንፈስ ተጨማሪ ማበረታቻዎች ቀርበዋል። ደግነት የክርስቶስ መንግሥት ሕግ፣ የእርሱ ትምህርት ቤት መሠረታዊ ትምህርት፣ የቤተሰቡም መለያ ነው። ለወንድማዊ ፍቅር በርካታ ምክንያቶች ተጠቅሰዋል። የእግዚአብሔርን ምሕረትና ርኅራኄ ጥቅም ለራሳችሁ የምትጠብቁት ወይም የተለማመዳችሁት እንደሆነ፣ እርስ በርሳችሁ ርኅሩኆች ሁኑ። ሰዎች አንድ ልብ ሆነው ማየት የአገልጋዮች ደስታ ነው። ክርስቶስ እኛ ትሑታን እንድንሆን መጣ፤ ስለዚህ በእኛ መካከል የትዕቢት መንፈስ አይኖር። በራሳችን ስህተቶች ላይ ጥብቅ መሆን፣ የራሳችንንም ጉድለቶች በፍጥነት ልናስተውል ይገባናል፤ ነገር ግን ለሌሎች ለመቻቻል ዝግጁ መሆን ይገባናል። ሌሎችን በደግነት ልንከባከብ ይገባናል፣ ነገር ግን በሌሎች ጉዳይ ጣልቃ መግባት የለብንም። የውስጥም ሆነ የውጭ ሰላም ያለ ትሕትና መንፈስ ሊገኝ አይችልም።

2:5-11 የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ በፊታችን ቀርቦልናል። ከሞቱ ጥቅም ለማግኘት ከፈለግን፣ በሕይወቱ ልንመስለው ይገባል። የክርስቶስን ሁለት ባሕርያት—መለኮታዊ ባሕርዩንና ሰብዓዊ ባሕርዩን—ልብ በሉ። እርሱ በእግዚአብሔር መልክ የነበረ፣ መለኮታዊውን ባሕርይ የተካፈለ፣ የዘላለምና የአንድያ የእግዚአብሔር ልጅ እንደመሆኑ መጠን (ዮሐንስ 1:1)፣ ከእግዚአብሔር ጋር እኩል መሆንን እንደ ዘረፋ አልቆጠረውም ነበር፣ ከሰውም የእግዚአብሔርን አምልኮ መቀበልን። የእርሱ ሰብዓዊ ባሕርይ፤ በዚህም ነገር ከኃጢአት በቀር በሁሉ ነገር እኛን መሰለ። ዓለም ሳይፈጠር ከአብ ጋር የነበረውን ክብር በራሱ ፈቃድ ትቶ፣ እንዲህ ዝቅ ብሎ ወረደ። የክርስቶስ ሁለት ሁኔታዎች—የውርደትና የከፍታው—ልብ ተብለዋል። ክርስቶስ የሰውን ምሳሌና መልክ ብቻ ሳይሆን ያዘ፤ ነገር ግን ዝቅተኛ በሆነ ሁኔታ ውስጥ ያለን ሰው መልክ ያዘ፤ በክብር ሳይገለጥ። ሕይወቱ በሙሉ የድህነትና የመከራ ሕይወት ነበር። ነገር ግን እጅግ ዝቅተኛው እርምጃው የመስቀል ሞትን መሞቱ፣ የክፉ አድራጊና የባሪያ ሞት፣ ለሕዝብ ጥላቻና ንቀት የተጋለጠ ነበር። ከፍ ከፍ ማለቱ የክርስቶስ ሰብዓዊ ባሕርይ ከመለኮቱ ጋር ተዋሕዶ የነበረ ነው።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV If you have any encouragement from being united with Christ, if any comfort from his love, if any fellowship with the S… English BCV እምበኣር ናይ ክርስቶስ ብምዃንኩም፥ ምትብባዕ እንተ ሃልዩኩም፥ ናይ ፍቕሪ ምፅንናዕ እንተ ሃልዩኩም፥ ምስ መንፈስ ቅዱስ ሕብረት እንተ ሃልዩኩም፥ ለውሃትን ርህራሀን እንተ ሃልዩኩም፥ ትግርኛ GAZBIB Egaa karaa Kristos wal gorsuun, jaalala isaatiin wal jajjabeessuun, karaa hafuura qulqulluu tokkummaa qabaachuun, gara-… Afaan Oromoo BCV GIZ ወእምከመ ሀለወ ኀቤክሙ ይእዜ ፍሥሓ በክርስቶስ አው ዘይናዝዝ ልበ በተፋቅሮ፣ አው ዘይሳተፍ በመንፈስ፣ አው በምሒር ወተሣህሎ። giz GAZGAZ Egaa karaa Kristos wal gorsuun, jaalala isaatiin wal jajjabeessuun, karaa hafuura qulqulluu tokkummaa qabaachuun, gara-… Afaan Oromoo BCV aksum እምበኣር ናይ ክርስቶስ ብምዃንኩም፥ ምትብባዕ እንተ ሃልዩኩም፥ ናይ ፍቕሪ ምፅንናዕ እንተ ሃልዩኩም፥ ምስ መንፈስ ቅዱስ ሕብረት እንተ ሃልዩኩም፥ ለውሃትን ርህራሀን እንተ ሃልዩኩም፥ ትግርኛ AMHNIV ከክርስቶስ ጋር ካላችሁ አንድነት የተነሣ የትኛውም መበረታታት፣ ከፍቅር የሆነ መጽናናት፣ የመንፈስ ኅብረት፣ ምሕረትና ርኅራኄ ካላችሁ፣ አማርኛ SWAHSUV Basi ikiwako faraja yo yote katika Kristo, yakiwako matulizo yo yote ya mapenzi, ukiwako ushirika wo wote wa Roho, ikiw… Kiswahili