ወደ ፊልጵስዩስ 1

AMHNIVአማርኛ30 ጥቅሶች4:35 አዳምጥ
አዳምጥ 4:35 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1የክርስቶስ ኢየሱስ አገልጋዮች የሆኑ ጳውሎስና ጢሞቴዎስ፤ ከቤተ ክርስቲያን ኤጲስ ቆጶሳትና ከዲያቆናት ጋር በፊልጵስዩስ ላሉ በክርስቶስ ኢየሱስ ቅዱሳን ለሆኑ ሁሉ፤

2ከእግዚአብሔር ከአባታችን፣ ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።

3እናንተን ባስታወስሁ ቍጥር አምላኬን አመሰግናለሁ።

4ዘወትር ስለ ሁላችሁ ስጸልይ፣ በደስታ እጸልያለሁ፤

5ከመጀመሪያው ቀን አንሥቶ እስካሁን ድረስ በወንጌል አገልግሎት ተካፋይ ሆናችኋልና።

6በእናንተ መልካምን ሥራ የጀመረው እርሱ እስከ ክርስቶስ ኢየሱስ ቀን ድረስ ከፍጻሜው እንደሚያደርሰው ርግጠኛ ነኝ።

7በልቤ ስላላችሁ፣ ስለ ሁላችሁ እንዲህ ማሰቤ ተገቢ ነው፤ በእስራቴም ሆነ ለወንጌል ስመክትና ሳጸናው ሁላችሁም ከእኔ ጋር የእግዚአብሔር ጸጋ ተካፋዮች ናችሁና።

8በክርስቶስ ኢየሱስ ፍቅር ሁላችሁንም ምን ያህል እንደምናፍቃችሁ እግዚአብሔር ምስክሬ ነው።

9ፍቅራችሁ በጥልቅ እውቀትና በማስተዋል ሁሉ በዝቶ እንዲትረፈረፍ እጸልያለሁ።

10ይኸውም ከሁሉ የሚሻለውን ለይታችሁ እንድታውቁ፣ እስከ ክርስቶስም ቀን ድረስ ንጹሓንና ነቀፋ የሌለባችሁ እንድትሆኑ፣

11ለእግዚአብሔር ክብርና ምስጋና በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በሚገኘው የጽድቅ ፍሬ እንድትሞሉ ነው።

12አሁንም ወንድሞች ሆይ፤ በእኔ ላይ የደረሰው ነገር ወንጌል በይበልጥ እንዲስፋፋ መርዳቱን ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ።

13ከዚህ የተነሣ እስራቴ ስለ ክርስቶስ እንደሆነ፣ በቤተ መንግሥት ዘበኞችና በሌሎችም ሁሉ ዘንድ ታውቆአል።

14በእኔ መታሰር ምክንያት በጌታ ካሉት ወንድሞች ብዙዎቹ የእግዚአብሔርን ቃል ያለ ፍርሀት፣ በድፍረት ለመናገር ብርታት አግኝተዋል።

15አንዳንዶች ከቅናትና ከፉክክር የተነሣ፣ ሌሎች ግን ከበጎ ፈቃድ የተነሣ ክርስቶስን ይሰብካሉ።

16እነዚህ፣ እኔ ለወንጌል ለመሟገት እዚህ እንዳለሁ ስለሚያውቁ፣ በፍቅር ይህን ያደርጋሉ፤

17እነዚያ ግን በእስራቴ ላይ ሳለሁ መከራ ሊያጸኑብኝ አስበው በቅንነት ሳይሆን ለግል ምኞታቸው ሲሉ ክርስቶስን ይሰብካሉ።

18ታዲያ ችግሩ ከምኑ ላይ ነው? ቁም ነገሩ በቅንነትም ይሁን በማስመሰል በማንኛውም መንገድ ክርስቶስ መሰበኩ ነው። በዚህም ደስ ይለኛል። አዎን፤ ደስ ይለኛል፤

19በእኔ ላይ የደረሰው ነገር፣ በጸሎታችሁ አማካይነትና ከኢየሱስ ክርስቶስ መንፈስ በተሰጠ ረድኤት ለመዳኔ እንደሚሆን ዐውቃለሁና።

20በምንም ዐይነት መንገድ ዐፍሬ እንዳልገኝ ጽኑ ናፍቆትና ተስፋ አለ፤ ነገር ግን እንደ ወትሮው ሁሉ ዛሬም በሕይወትም ሆነ በሞት ክርስቶስ በሥጋዬ እንዲከበር ሙሉ ድፍረት ይኖረኛል።

21ለእኔ፣ መኖር ክርስቶስ ነው፤ ሞትም ማትረፍ ነው።

22በሥጋ ከቈየሁ፣ ፍሬያማ ተግባር ይኖረኛል፤ ነገር ግን የትኛውን እንደምመርጥ አላውቅም።

23በእነዚህ በሁለቱ እጨነቃለሁ፤ ልሄድ፣ ከክርስቶስም ጋር ልሆን እናፍቃለሁ፤ ይህ እጅግ የተሻለ ነውና።

24ነገር ግን በሥጋ መኖሬ ለእናንተ ይበልጥ አስፈላጊ ነው።

25ይህን በማስተዋል፣ በእምነት እንድታድጉና ደስ እንዲላችሁ፣ በሁላችሁ ዘንድ እንደምቈይና እንደምኖር ተረድቻለሁ።

26እንደ ገና መጥቼ በእናንተ ዘንድ በምሆንበት ጊዜ በእኔ ምክንያት በክርስቶስ ኢየሱስ ያላችሁ ደስታ ይበዛላችኋል።

27ብቻ ለክርስቶስ ወንጌል እንደሚገባ ኑሩ፤ ይህ ከሆነ መጥቼ ባያችሁ ወይም በርቀት ሆኜ ስለ እናንተ ብሰማ፣ ለወንጌል እምነት እንደ አንድ ሰው ሆናችሁ በመጋደል በአንድ መንፈስ ጸንታችሁ እንደምትቆሙ ዐውቃለሁ።

28በማንኛውም መንገድ በተቃዋሚዎቻችሁ አትሸበሩ፤ ይህ እነርሱ እንደሚጠፉ፣ እናንተ ግን እንደምትድኑ ከእግዚአብሔር የተሰጠ ምልክት ነው።

29በክርስቶስ እንድታምኑ ብቻ ሳይሆን ስለ እርሱ መከራ እንድትቀበሉም ይህ ጸጋ ተሰጥቶአችኋልና፤

30ቀድሞ እንዳያችሁት አሁንም በእኔ እንዳለ በምትሰሙት በዚያው ዐይነት ተጋድሎ እናንተም እያለፋችሁ ነውና።

ማብራሪያ

1:1-7 የላቁ አገልጋዮች ከሁሉ የላቀ ክብራቸው የክርስቶስ ባሪያዎች መሆን ነው። በእውነት በምድር ላይ ቅዱሳን ያልሆኑ ሰዎች በሰማይም ቅዱሳን አይሆኑም። ከክርስቶስ ውጭ፣ ከሁሉ የተሻሉ ቅዱሳን እንኳን ኃጢአተኞች ናቸውና በእግዚአብሔር ፊት መቆም አይችሉም። ያለ ጸጋ ሰላም የለም። ውስጣዊ ሰላም የሚመነጨው የእግዚአብሔርን ሞገስ ከመገንዘብ ነው። ጸጋና ሰላም ደግሞ ከሁሉም በረከቶች ምንጭና መነሻ ከሆነው ከእግዚአብሔር አባታችን በቀር የለም። በፊልጵስዩስ ሐዋርያው ክፉኛ ተስተናግዶ የሥራውን ፍሬ ጥቂት ብቻ አይቶ ነበር፤ ሆኖም ፊልጵስዩስን በደስታ ያስታውሳል። እኛ ጥቅሙን ስለምንቀበል፣ እግዚአብሔርም ክብሩን ስለሚቀበል፣ የሌሎችን ጸጋዎችና መጽናናቶች፣ ስጦታዎችና አገልግሎቶች ምክንያት አምላካችንን ማመስገን አለብን። የጸጋ ሥራ በፍጹም ፍጹም አይሆንም እስከ ኢየሱስ ክርስቶስ ቀን ድረስ፣ እርሱ እስከሚገለጥበት ቀን ድረስ። ነገር ግን፣ በእውነት እንደገና በመወለድ (regeneration) የእርሱን መልካም ሥራ የጀመረው እግዚአብሔር ያንን ሥራ ደግሞ እንደሚፈጽም ሁልጊዜ ልንተማመን እንችላለን፤ ምንም እንኳን በውጫዊ መገለጫዎች ወይም ወደ ቅድስና በሚያደርስ አዲስ ፍጥረት በቀር በሌላ በማንኛውም ነገር መታመን የለብንም። ሰዎች በአገልጋዮቻቸው አገልግሎት ጥቅም ሲያገኙ ለእነሱ ውድ ይሆናሉ። በእግዚአብሔር ዓላማ ምክንያት አብረው የሚሰቃዩ እርስ በእርሳቸው ውድ መሆን አለባቸው።

1:8-11 ክርስቶስ የሚወዳቸውንና የሚራራላቸውን እነዚያን ነፍሳት እኛስ ልንራራላቸውና ልንወዳቸው አይገባምን? በማንኛውም ጸጋ የሞሉ ሰዎች ይበልጥ ሊሞሉ ይገባቸዋል። የሚለያዩትን ነገሮች ፈትኑ፤ ይህም የላቁትን ነገሮች እንድናስተውል ነው። የክርስቶስ እውነቶችና ሕጎች የላቁ ናቸውና፤ እነርሱም ራሳቸውን ለእያንዳንዱ አስተዋይ አእምሮ እንደ ምርጥ አድርገው ያቀርባሉ። በዓለም ውስጥ የምንኖረው ኑሮ በቅንነት ሊሆን ይገባል፤ እርሱም የሁሉም ጸጋዎቻችን ክብር ነው። ክርስቲያኖች በቀላሉ የሚቀየሙ መሆን የለባቸውም፤ እንዲሁም እግዚአብሔርን ወይም ወንድሞቻቸውን እንዳያስቀይሙ በጣም መጠንቀቅ አለባቸው። እግዚአብሔርን ከሁሉ በላይ የሚያከብሩ ነገሮች ለእኛም ከሁሉ በላይ ይጠቅሙናል። በእኛ ዘንድ መልካም ፍሬ መገኘቱን ወይም አለመገኘቱን አጠራጣሪ አናድርገው። አነስተኛ የክርስቲያናዊ ፍቅር፣ እውቀትና ፍሬአማነት ማንንም ሊያረካ አይገባም።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያዎች የሆኑ ጳውሎስና ጢሞቴዎስ በፊልጵስዩስ ለሚኖሩ ከኤጲስ ቆጶሳትና ከዲያቆናት ጋር በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት ቅዱሳን ሁሉ፤ አማርኛ ENGNIV Paul and Timothy, servants of Christ Jesus, To all the saints in Christ Jesus at Philippi, together with the overseers … English BCV ኣገልገልቲ ኢየሱስ ክርስቶስ ካብ ዝኾኑ ጳውሎስን ጢሞቴዎስን፥ ናብቶም ኣብ ፊልጵስዩስ ብኢየሱስ ክርስቶስ ዘለዉ ዅሎም ቅዱሳን፥ ምስ ኤጲስ ቆጶሳትን(ሀ) ዲያቆናትን። ትግርኛ GAZBIB Nuyi Phaawulosii fi Ximotewos hojjetoonni Kristos Yesus, gara warra karaa Kristos Yesus Waaqayyoof qulqullaa'anii manda… Afaan Oromoo BCV GIZ እምጳውሎስ ወጢሞቴዎስ አግብርተ ኢየሱስ ክርስቶስ ለኵሎሙ ቅዱሳን እለ ተቀደሱ በኢየሱስ ክርስቶስ እለ ሀለዉ ፊልጵስዩስ ምስለ ቀሳውስት ወዲያቆናት። giz GAZGAZ Nuyi Phaawulosii fi Ximotewos hojjetoonni Kristos Yesus, gara warra karaa Kristos Yesus Waaqayyoof qulqullaa'anii manda… Afaan Oromoo BCV aksum ኣገልገልቲ ኢየሱስ ክርስቶስ ካብ ዝኾኑ ጳውሎስን ጢሞቴዎስን፥ ናብቶም ኣብ ፊልጵስዩስ ብኢየሱስ ክርስቶስ ዘለዉ ዅሎም ቅዱሳን፥ ምስ ኤጲስ ቆጶሳትን(ሀ) ዲያቆናትን። ትግርኛ SWAHSUV Paulo na Timotheo, watumwa wa Kristo Yesu, kwa watakatifu wote katika Kristo Yesu, walioko Filipi, pamoja na maaskofu Kiswahili