የማርቆስ ወንጌል 14

AMHNIVአማርኛ72 ጥቅሶች11:04 አዳምጥ
አዳምጥ 11:04 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ፋሲካና የቂጣ በዓል ሊከበር ሁለት ቀን ሲቀረው፣ የካህናት አለቆችና ጸሐፍት ኢየሱስን የሚይዙበትና የሚገድሉበትን ዘዴ ይፈልጉ ነበር።

2ሆኖም፣ “ሕዝቡ ዐመፅ እንዳያነሣ በበዓሉ ሰሞን መሆን የለበትም” ይባባሉ ነበር።

3እርሱም በቢታንያ በለምጻሙ ስምዖን ቤት በማእድ ተቀምጦ ሳለ፣ አንዲት ሴት ዋጋው እጅግ ውድ የሆነ ንጹሕ የናርዶስ ሽቱ የተሞላበት የአልባስጥሮስ ቢልቃጥ ይዛ መጣች፣ ቢልቃጡንም ሰብራ ሽቱውን በራሱ ላይ አርከፈከፈችው።

4በዚያ ከነበሩት አንዳንዶቹ በድርጊቱ ተቈጥተው እንዲህ ይባባሉ ነበር፤ “ሽቱው ለምን በከንቱ ይባክናል?

5ከሦስት መቶ ዲናር በላይ ተሸጦ፣ ገንዘቡን ለድኾች መስጠት ይቻል ነበር።” ሴትየዋንም ነቀፏት።

6ኢየሱስ ግን እንዲህ አላቸው፤ “ተዉአት፣ ለምን ታስቸግሯታላችሁ? መልካም ነገር አድርጋልኛለች።

7ድኾች ምንጊዜም ከእናንተ ጋር ናቸው፤ በፈለጋችሁ ጊዜ ልትረዷቸው ትችላላችሁ፤ እኔ ግን ሁል ጊዜ ከእናንተ ጋር አልኖርም፤

8እርሷ ማድረግ የምትችለውን ያህል አድርጋለች፤ ለመቃብሬ እንዲሆን ሰውነቴን አስቀድማ ቀብታለች።

9እውነት እላችኋለሁ፤ ይህ ወንጌል በዓለም ሁሉ በሚሰበክበት በማንኛውም ስፍራ እርሷ ያደረገችው መታሰቢያ ሆኖ ይነገርላታል።”

10ከዚህ በኋላ ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ የሆነው የአስቆሮቱ ይሁዳ አሳልፎ ሊሰጠው ወደ ካህናት አለቆች ሄደ።

11እነርሱም ይህን ሲሰሙ ደስ አላቸው፤ ገንዘብ ሊሰጡትም ቃል ገቡለት፤ ስለዚህ እርሱን አሳልፎ የሚሰጥበትን ምቹ ጊዜ ይጠባበቅ ነበር።

12የፋሲካ በግ በሚታረድበት በቂጣ በዓል የመጀመሪያው ቀን፣ ደቀ መዛሙርቱ ወደ ኢየሱስ ቀርበው፣ “የፋሲካ እራት የት እንድናዘጋጅልህ ትፈልጋለህ?” አሉት።

13እርሱም ከደቀ መዛሙርቱ ሁለቱን እንዲህ ሲል ላካቸው፤ “ወደ ከተማ ሂዱ፤ እንስራ ውሃ የተሸከመ ሰው ይገናኛችኋል፤

14ወደሚገባበት ቤትም ተከተሉት፤ የቤቱንም ጌታ፣ ‘መምህሩ፣ ከደቀ መዛሙርቴ ጋር የፋሲካን ራት የምበላበት የእንግዳ ማረፊያ የትኛው ነው?’ ብሎአል በሉት፤

15እርሱም በሰገነቱ ላይ የተሰናዳና የተነጠፈ ሰፊ አዳራሽ ያሳያችኋል፤ እዚያ አዘጋጁልን።”

16ደቀ መዛሙርቱም ወጥተው ወደ ከተማዪቱ ሄዱ፤ ማንኛውም ነገር ኢየሱስ እንዳላቸው ሆኖ አገኙት፤ ፋሲካውንም አሰናዱ።

17በመሸም ጊዜ ኢየሱስ ከዐሥራ ሁለቱ ጋር መጣ።

18በማእድ ላይ ሳሉም፣ “እውነት እላችኋለሁ፣ ከመካከላችሁ አንዱ፣ አብሮኝ የሚበላው እርሱ አሳልፎ ይሰጠኛል” አላቸው።

19እነርሱም አዘኑ፤ እያንዳንዳቸውም፣ “እኔ እሆንን?” ይሉት ጀመር።

20እርሱም እንዲህ አላቸው፤ “ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ፣ ከእኔ ጋር እጁን በወጭቱ ውስጥ የሚያጠልቀው ነው።

21የሰው ልጅስ ስለ እርሱ እንደ ተጻፈው ይሄዳል፤ የሰውን ልጅ አሳልፎ ለሚሰጥ ለዚያ ሰው ግን ወዮለት፤ ያ ሰው ባይወለድ ይሻለው ነበር።”

22ሲበሉም እንጀራ አንሥቶ ባረከ፤ ቈርሶም ለደቀ መዛሙርቱ ሰጣቸውና፣ “እንኩ፤ ይህ ሥጋዬ ነው” አላቸው፣

23ጽዋውንም አነሣ፤ አመስግኖም ሰጣቸው፤ ሁሉም ከዚያ ጠጡ።

24ደግሞም እንዲህ አላቸው፤ “ይህ ስለ ብዙዎች የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ነው፤

25እውነት እላችኋለሁ፤ በእግዚአብሔር መንግሥት አዲሱን የወይን ፍሬ እስከምጠጣበት እስከዚያች ቀን ድረስ ዳግም ይህን አልጠጣም።”

26ከዚህ በኋላ መዝሙር ዘምረው ወደ ደብረ ዘይት ተራራ ወጡ።

27ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ “እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፣ ሁላችሁ ትክዱኛላችሁ፤ “ ‘እረኛውን እመታለሁ በጎቹም ይበተናሉ’ ”

28ከተነሣሁ በኋላ ግን፣ ቀድሜአችሁ ወደ ገሊላ እሄዳለሁ።”

29ጴጥሮስም፣ “ሁሉም ቢሰናከሉ እንኳ እኔ አላደርገውም” አለ።

30ኢየሱስም፣ “እውነት እልሃለሁ፤ በዚህች ሌሊት ዶሮ ሁለት ጊዜ ሳይጮኽ፣ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ” አለው።

31ጴጥሮስም፣ “ከአንተ ጋር ብሞት እንኳ ከቶ አልክድህም” በማለት ይበልጥ አጽንቶ ተናገረ። ሁሉም ደግሞ እንደዚሁ አሉ።

32ከዚህ በኋላ ጌቴሴማኒ ወደሚባል ስፍራ ሄዱ፤ ኢየሱስም ደቀ መዛሙርቱን፣ “እኔ ስጸልይ እናንተ እዚህ ቈዩ” አላቸው።

33ጴጥሮስን፣ ያዕቆብንና ዮሐንስንም ይዞ ሄደ፤ እጅግ ያዝን ይጨነቅ ጀመር።

34ደግሞም፣ “ነፍሴ እስከ ሞት ድረስ እጅግ አዘነች፤ እዚሁ ሁኑና ነቅታችሁ ጠብቁ” አላቸው።

35ጥቂት ዕልፍ ብሎም በምድር ላይ በመውደቅ ቢቻል ሰዓቱ ከእርሱ እንዲያልፍ ጸለየና፣

36“አባ፤ አባት ሆይ፤ ሁሉ ነገር ይቻልሃልና ይህን ጽዋ ከእኔ አርቀው፤ ነገር ግን የእኔ ፈቃድ ሳይሆን የአንተ ፈቃድ ይሁን” አለ።

37ተመልሶም ሲመጣ ደቀ መዛሙርቱን ተኝተው አገኛቸው፤ ጴጥሮስንም እንዲህ አለው፣ “ስምዖን ሆይ፣ ተኝተሃልን? አንድ ሰዓት እንኳ ነቅተህ መጠበቅ አቃተህ?

38ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉ፤ ጸልዩም፤ መንፈስ ዝግጁ ነው፣ ሥጋ ግን ደካማ ነው።”

39እንደ ገናም ሄዶ መጀመሪያ የጸለየውን ደግሞ ጸለየው።

40ዳግመኛም ሲመለስ ዐይናቸውን እንቅልፍ ከብዶት ተኝተው አገኛቸው፤ የሚመልሱለትንም አያውቁም ነበር።

41ሦስተኛ ጊዜም መጥቶ እንዲህ አላቸው፤ “አሁንም እንደ ተኛችሁና እንዳረፋችሁ ናችሁ? ይበቃል! ሰዓቲቱ ደርሳለች፤ እነሆ፤ የሰው ልጅ ለኀጢአተኞች እጅ አልፎ ይሰጣል።

42ተነሡ፤ እንሂድ፤ አሳልፎ የሚሰጠኝ መጥቶአል።”

43ወዲያው እየተናገረ ሳለ ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ ይሁዳ መጣ፤ አብረውትም ሰይፍና ዱላ የያዙ፣ ከካህናት አለቆች፣ ከጸሓፍትና ከሽማግሌዎች የተላኩ ብዙ ሰዎች ነበሩ።

44አሳልፎ የሚሰጠውም፣ “እኔ የምስመው እርሱ ነውና ያዙት፤ ተጠንቅቃችሁም ውሰዱት” በማለት አስቀድሞ ምልክት ሰጥቶአቸው ነበር።

45እንደ ደረሰም ወዲያው ወደ ኢየሱስ ቀርቦ፣ “መምህር ሆይ!” ብሎ ሳመው፤

46ሰዎቹም ኢየሱስን ያዙት አሰሩትም።

47በአቅራቢያው ቆመው ከነበሩት አንዱ ሰይፉን መዞ የሊቀ ካህናቱን አገልጋይ ጆሮ ቈረጠ።

48ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ “እንደ ወንበዴ በሰይፍና በቈመጥ ልትይዙኝ መጣችሁን?

49በየዕለቱም በቤተ መቅደስ እያስተማርሁ ከእናንተ ጋር ስኖር አልያዛችሁኝም፤ መጻሕፍት ይፈጸሙ ዘንድ ይህ ሆነ።”

50በዚህ ጊዜ ሁሉም ትተውት ሸሹ።

51ዕርቃኑን ለመሸፈን በፍታ ያገለደመ አንድ ወጣት ኢየሱስን ይከተል ነበር። ሰዎቹም ይህን ወጣት በያዙት ጊዜ፣

52ግልድሙን ጥሎ ዕራቍቱን ሸሸ።

53ኢየሱስንም ወደ ሊቀ ካህናቱ ወሰዱት፤ በዚያም የካህናት አለቆች፣ ሽማግሌዎችና ጸሓፍት ሁሉ ተሰበሰቡ።

54ጴጥሮስም ከሩቅ እየተከተለው፣ እስከ ሊቀ ካህናቱ ግቢ ዘለቀ፤ በዚያም ተቀምጦ ከሎሌዎቹ ጋር እሳት ይሞቅ ነበር።

55የካህናት አለቆችና ሸንጎው በሙሉ ኢየሱስን ለመግደል ምስክር ፈለጉ፤ ነገር ግን ማግኘት አልቻሉም።

56ብዙዎች በሐሰት ቢመሰክሩበትም፣ ቃላቸው አንድ ሊሆን አልቻለም።

57አንዳንዶቹም ተነሥተው እንዲህ ሲሉ በሐሰት መሰከሩበት፤

58“ይህ፣ ‘የሰው እጅ የሠራውን ቤተ መቅደስ አፍርሼ፣ በሦስት ቀን ሌላ የሰው እጅ ያልሠራውን እሠራለሁ’ ሲል ሰምተነዋል።”

59ይህም ሆኖ፣ እንኳ ምስክርነታቸው አንድ አልሆነም።

60ሊቀ ካህናቱም ተነሥቶ በፊታቸው በመቆም፣ “እነዚህ በአንተ ላይ የሚመሰክሩት ምንድን ነው? ለምን አትመልስም?” በማለት ኢየሱስን ጠየቀው።

61ኢየሱስ ግን ዝም አለ፤ ምንም መልስ አልሰጠም። ሊቀ ካህናቱም እንደ ገና፣ የቡሩኩ ልጅ፣ ክርስቶስ አንተ ነህን? ሲል ጠየቀው።

62ኢየሱስም፣ “አዎን ነኝ፤ የሰው ልጅ በኀያሉ ቀኝ ሲቀመጥ፣ በሰማይ ደመናም ሲመጣ ታዩታላችሁ” አለ።

63ሊቀ ካህናቱም ልብሱን ቀደደና፣ እንዲህ አለ፤ “ሌላ ምን ምስክር ያስፈልገናል?

64ስድቡን ሰምታችኋል፤ ታዲያ፣ ምን ይመስላችኋል?”፤ እነርሱም ሞት ይገባዋል በማለት በአንድ ቃል ፈረዱበት።

65በዚህ ጊዜ አንዳንዶቹ ይተፉበት ጀመር፤ ዐይኑንም ሸፍነው በጡጫ እየመቱት፣ “እስቲ ትንቢት ተናገር!” ይሉት ነበር። ሎሌዎችም በጥፊ እየመቱ ወሰዱት።

66ጴጥሮስ በግቢው ውስጥ በታችኛው በኩል ሳለ፣ ከሊቀ ካህናቱ ገረዶች አንዲቱ መጣች፤

67ጴጥሮስ እሳት ሲሞቅ አይታ ትኵር ብላ ተመለከተችውና፣ “አንተም ከናዝሬቱ ኢየሱስ ጋር ነበርህ” አለችው።

68እርሱ ግን፣ “የምትዪውን አላውቅም፤ አይገባኝምም” በማለት ካደ። ከዚያም ወደ መግቢያው በር ወጣ አለ፤ በዚህ ጊዜ ዶሮ ጮኸ።

69ገረዲቱም ባየችው ጊዜ እዚያ ለቆሙት፣ “ይህ ሰው ከእነርሱ አንዱ ነው” ብላ እንደ ገና ተናገረች።

70እርሱ ግን አሁንም ካደ። ከጥቂት ጊዜ በኋላ፣ በዚያ የቆሙት ሰዎች ጴጥሮስን፣ “የገሊላ ሰው እንደ መሆንህ መጠን፣ በእርግጥ አንተ ከእነርሱ አንዱ ነህ” አሉት።

71እርሱ ግን፣ “እናንተ የምትሉትን ሰው እኔ አላውቀውም” እያለ ይምል ይገዘት ጀመር።

72ወዲያውም ዶሮ ሁለተኛ ጮኸ። ጴጥሮስም፣ “ዶሮ ሁለት ጊዜ ከመጮኹ በፊት ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ” ያለው የኢየሱስ ቃል ትዝ አለው። ከዚያም ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ።

ማብራሪያ

14:1-11 ክርስቶስ ነፍሱን እስከ ሞት ድረስ ስለ እኛ አፈሰሰልን፤ ታዲያ ለእርሱ ለመስጠት እጅግ ውድ የምንለው ነገር ይኖር ይሆን? የምርጥ ፍቅራችንን የከበረውን ሽቱ እንሰጠዋለን? በሙሉ ልባችን እንውደደው፤ ቅንዓትና ፍቅር በስህተት ተረድተው ቢወቀሱም እንኳ። ለድሆች ምጽዋት መስጠት አንድንም ከጌታ ኢየሱስ ጋር ካሉ ልዩ የአምልኮ ተግባራት ነፃ እንደማያደርገው አስታውሱ። ክርስቶስ የዚህችን ሴት አምላካዊ አገልግሎት በሁሉም ዘመናት ያሉ ምእመናን እንዲያስተውሉት አወደሰ። ክርስቶስን የሚያከብሩትን እርሱ ያከብራቸዋል። ስግብግብነት የይሁዳ ዋነኛ ምኞት ነበር፤ ይህም ጌታውን ለመክዳት ወደሚያደርሰው ኃጢአት ዳረገው፤ ዲያብሎስም ፈተናውን ከዚሁ ምኞት ጋር አጣጥሞ በማቅረብ አሸነፈው። እንዴት ያሉ ክፉ ሴራዎች ብዙዎች ኃጢአታዊ ፍለጋዎቻቸውን ሲያሳድዱ እንዳሏቸው ተመልከቱ፤ ነገር ግን እቅዳቸውን የሚያስኬድ የሚመስላቸው ነገር በመጨረሻው እርግማን ሆኖ ይገኛል።

፲፬፥፲፪-፳፩

እዚህ የተዘገቡት ክስተቶች የሰው ልጅ አስተዋይነት ወይም ትንበያ ውጤት ሊሆኑ ከቶ አይችሉም። ነገር ግን ጌታችን ስለ እኛ ሁሉንም ነገር ሳያደርጉ በፊት ያውቃል። እርሱን ወደ ልባችን እንዲገባ ከፈቀድንለት፣ በልባችን ይኖራል። የሰው ልጅ፣ ስለ እርሱ እንደተጻፈው፣ እንደሚታረድ በግ ወደ እልቂት ይሄዳል። ነገር ግን እርሱን አሳልፎ ለሰጠው ሰው ወዮለት! እግዚአብሔር የሰዎችን ኃጢአት መፍቀዱና ከእነሱም ለራሱ ክብር ማምጣቱ ኃጢአት እንዲሠሩ አያስገድዳቸውም። እንዲሁም ይህ ለጥፋታቸው ምንም ዓይነት ሰበብ አይሆንም፣ ወይም ቅጣታቸውን አያሳንስም።

14:22-31 የጌታ እራት ለነፍስ ምግብ ነው፤ ስለዚህም ለሥጋ ከሆነው ነገር ምልክት ለመሆን የሚያበቃ በጣም ትንሽ ነገር በቂ ነው። ይህም ጌታችን በራሱ ምሳሌና ተግባር የመሰረተው ሲሆን፣ እርሱ እስኪመለስ ድረስ እንዲቀጥል ነው። በበረከትና በምስጋና የተመሰረተ ሲሆን፣ የክርስቶስን ሞት መታሰቢያ እንዲሆን ነው። የከበረው ደሙ ስለ ቤዛነታችን ዋጋ እንደሆነ በተደጋጋሚ ተጠቅሷል። የክርስቶስ ደም ለብዙዎች እንደፈሰሰ ይህ ለድሆች፣ ለንስሐ ለሚገቡ ኃጢአተኞች ምንኛ የሚያጽናና ነው! ለብዙዎች ከሆነ፣ ለኔ ለምን አይሆንም? ይህም እርሱ በሞቱ የገዛልንን በረከቶች ወደ እኛ መተላለፋቸውን የሚያሳይ ምልክት ነበር። የተሰቀለውን ክርስቶስን ትምህርት በራሳችሁ ላይ ተግብሩት፤ ለነፍሳችሁ ምግብና መጠጥ ሆኖ፣ መንፈሳዊ ህይወታችሁን የሚያበረታና የሚያድስ ይሁን። የሰማይን ደስታ ቅድመ ሁኔታና ቅምሻ ሲሆን፣ በዚህም የስሜትን ደስታዎችና ፍላጎቶች እንዳንመኝ የሚያደርግ ነው። መንፈሳዊ ደስታን የቀመሰ ሁሉ ወዲያውኑ የዘላለምን ደስታ ይመኛል። ታላቁ እረኛ መከራውን ያለ ምንም ስህተት ያለፈ ቢሆንም፣ ተከታዮቹ ግን በተመደቡላቸው ትንሽ መከራ ምክንያት ብዙ ጊዜ ተበታትነዋል። ራሳችንን ጥሩ አድርገን ለማሰብና የራሳችንን ልብ ለመታመን ምንኛ ተጋላጮች ነን! ጴጥሮስ ጌታውን ያለ ፍርሃትና መንቀጥቀጥ በዚህ መንገድ መመለሱ መልካም አልነበረም።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG ከሁለት ቀን በኋላ ፋሲካና የቂጣ በዓል ነበረ። የካህናት አለቆችም ጻፎችም እንዴት አድርገው በተንኰል እንደሚይዙትና እንደሚገድሉት ይፈልጉ ነበር። አማርኛ ENGNIV Now the Passover and the Feast of Unleavened Bread were only two days away, and the chief priests and the teachers of t… English BCV ፋሲካን በዓል ቅጫን ክኸውን ክልተ መዓልቲ ተሪፍዎ ነበረ። ሊቃነ ካህናትን መምህራን ሕግን ንኢየሱስ ብተንኰል ሒዞም ክቐትልዎ ይደልዩ ነበሩ። ትግርኛ GAZBIB Ayyaanni Faasiikaa fi, ayyaanni Maxinoo guyyaa lamatti galee ture. Luboonni warri angafoonnii fi barsiisonni seeraa kar… Afaan Oromoo BCV GIZ ወእስከ ሰኑይ መዋዕል ፋሲካ በዓለ መጸለት ወኀሠሡ ሊቃነ ካህናት ወጸሐፍት ይትመየንዎ ወየአኀዝዎ ወይቅትልዎ። giz GAZGAZ Ayyaanni Faasiikaa fi, ayyaanni Maxinoo guyyaa lamatti galee ture. Luboonni warri angafoonnii fi barsiisonni seeraa kar… Afaan Oromoo BCV aksum ፋሲካን በዓል ቅጫን ክኸውን ክልተ መዓልቲ ተሪፍዎ ነበረ። ሊቃነ ካህናትን መምህራን ሕግን ንኢየሱስ ብተንኰል ሒዞም ክቐትልዎ ይደልዩ ነበሩ። ትግርኛ SWAHSUV Baada ya siku mbili ilikuwa sikukuu ya Pasaka, na mikate isiyochachwa; wakuu wa makuhani na waandishi wakatafuta njia y… Kiswahili