ትንቢተ ሚክያስ 6

AMHEVGአማርኛ16 ጥቅሶች2:46 አዳምጥ
አዳምጥ 2:46 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1አሁን፦ “ተነሣ፥ በተራሮችም ፊት ተፋረድ፥ ኮረብቶችም ቃልህን ይስሙ” ብሎ እግዚአብሔር የሚለውን ስሙ።

2ተራሮች ሆይ፥ ጠንካሮች የምድር መሠረቶችም ሆይ፥ እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር ክርክር አለውና፥ ከእስራኤልም ጋር ይፋረዳልና የእግዚአብሔርን ክርክር ስሙ።

3“ሕዝቤ ሆይ፥ ምን አድርጌሃለሁ? በምንስ አድክሜሃለሁ? መስክርብኝ።

4ከግብፅ ምድር አውጥቼሃለሁ፥ ከባርነት ቤትም ተቤዥቼሃለሁ፤ በፊትህም ሙሴንና አሮንን ማርያምንም ልኬልህ ነበር።

5ሕዝቤ ሆይ፥ የሞዓብ ንጉሥ ባላቅ የመከረውን፥ የቢዖርም ልጅ በለዓም የመለሰለትን አሁን አስብ፤ የእግዚአብሔርንም የጽድቅ ሥራ ታውቅ ዘንድ ከሰጢም ጀምሮ እስከ ጌልገላ ድረስ አስብ።”

6ምን ይዤ ወደ እግዚአብሔር ፊት ልምጣና በልዑል አምላክ ፊት ልስገድ? የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የአንዱን ዓመት ጥጃ ይዤ በፊቱ ልምጣን?

7እግዚአብሔርስ በሺህ አውራ በጎች ወይስ በእልፍ የዘይት ፈሳሾች ደስ ይለዋልን? ወይስ የበኵር ልጄን ስለ በደሌ፥ የሆዴንም ፍሬ ስለ ነፍሴ ኃጢአት እሰጣለሁን?

8ሰው ሆይ፥ መልካሙን ነግሮሃል፤ እግዚአብሔርም ከአንተ ዘንድ የሚሻው ምንድር ነው? ፍርድን ታደርግ ዘንድ፥ ምሕረትንም ትወድድ ዘንድ፥ ከአምላክህም ጋር በትሕትና ትሄድ ዘንድ አይደለምን?

9የእግዚአብሔር ድምፅ ከተማይቱን ይጠራታል፤ ስምህን መፍራት ጥበብ ነው፤ የመቅሠፍትን በትር፥ እርሱንም ያዘጋጀ ማን እንደ ሆነ ስሙ።

10በውኑ በኃጢአተኛ ቤት የኃጢአት መዝገብ፥ የተጸየፈም ውሽተኛ መስፈሪያ ገና አለ ይሆን?

11በአባይ ሚዛንና በከረጢት ባለ በተንኰል መመዘኛ ንጹሕ እሆናለሁን?

12ባለ ጠጎችዋን ግፍ ሞልቶባቸዋል፤ በእርስዋም የሚኖሩ በሐሰት ተናግረዋል፥ ምላሳቸውም በአፋቸው ውስጥ ተንኰለኛ ነው።

13ስለዚህ እኔ ደግሞ በክፉ ቍስል መታሁህ፤ ስለ ኃጢአትህም አፈርስሁህ።

14ትበላለህ፥ ነገር ግን አትጠግብም፥ ችጋርህም በመካከልህ ይሆናል፤ ትወስዳለህ፥ ነገር ግን አታድንም፤ የምታድነውንም ለሰይፍ እሰጣለሁ።

15ትዘራለህ፥ ነገር ግን አታጭድም፤ ወይራውንም ትጨምቃለህ፥ ነገር ግን ዘይቱን አትቀባም፤ ወይኑንም ትጨምቃለህ፥ ነገር ግን የወይን ጠጁን አትጠጣም።

16አንተን ለጥፋት፥ በእርስዋም የሚኖሩትን ለማፍዋጫ እሰጥ ዘንድ የዘንበሪን ሥርዓትና የአክዓብን ቤት ሥራ ሁሉ ጠብቃችኋል፥ በምክራቸውም ሄዳችኋል፤ የሕዝቤንም ስድብ ትሸከማላችሁ።

ማብራሪያ

6:1-5 ሕዝቡ የእግዚአብሔርን አምልኮ ለምን እንደሰለቻቸውና ወደ ጣዖት አምልኮም ለምን እንዳደሉ እንዲገልጹ ይጠየቃሉ። ኃጢአት በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ለሚፈጠረው ክርክር መንስኤ ይሆናል። እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚከራከረው ራሳችንን እንድንመረምር ለማስተማር ነው። እነርሱም እግዚአብሔር ለእነርሱና ለአባቶቻቸው ያደረጋቸውን ብዙ ቸርነቶች ያስታውሱ፤ ከዚያም እነርሱ ለእርሱ ያሳዩትን የማይገባና ምስጋና የጎደለውን ምግባር ከእነዚያ ቸርነቶች ጋር ያወዳድሩ።

ሚክያስ 6:6-8

እነዚህ ጥቅሶች በለዓቅ የእስራኤልን አምላክ ሞገስ እንዴት ማግኘት እንደሚቻል ከበለዓም ጋር ያደረገው ምክክር ዋና ይዘት የያዙ ይመስላሉ። የጥፋተኝነትና የቁጣ ጥልቅ መንፈሳዊ ግንዛቤ ሰዎችን ሰላምንና ስርየትን በትጋት እንዲፈልጉ ያደርጋል፤ ያንጊዜም ለነሱ ተስፋ የሚሆን መሠረት ይፈጠራል። እግዚአብሔር በእኛ እንዲደሰትልን፣ የእኛ ትኩረት በክርስቶስ የማስታረቅ ሥራ (የኃጢአት ክፍያ) ተካፋይ መሆን ላይ ሊሆን ይገባል፤ እርሱን የምናስቀይምበት ኃጢአትም እንዲወገድ። ለእግዚአብሔር ፍትሕ የሚያስችለው/የሚያረካው ምንድን ነው? የራሳችን የምንለው የምንከራከርበት ምንም ነገር ስለሌለን በማን ስም ልንመጣ ይገባናል? በምን ጽድቅስ በፊቱ እንቀርባለን? የቀረቡት ሃሳቦች ቅንዓትን ቢያሳዩም እንኳ ድንቁርናን ያሳያሉ። እነርሱ በጣም የበለጸገውንና ውድ የሆነውን ያቀርባሉ። በኃጢአት ሙሉ በሙሉ የጸጸቱና ከእርሱም የሚመጣውን መከራና አደጋ በግልጽ የተገነዘቡ ሰዎች፣ ሰላምንና ስርየትን ለማግኘት ዓለምን ሁሉ (ካላቸው) ይሰጡ ነበር። ሆኖም በትክክል አያቀርቡም።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6