የማቴዎስ ወንጌል 2

AMHNIVአማርኛ23 ጥቅሶች3:51 አዳምጥ
አዳምጥ 3:51 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1በንጉሡ በሄሮድስ ዘመን፣ ኢየሱስ በቤተልሔም ይሁዳ ከተወለደ በኋላ ጠቢባን ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም መጥተው፣

2“የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? በምሥራቅ ኮከቡን አይተን ልንሰግድለት መጥተናልና” ሲሉ ጠየቁ።

3ንጉሡ ሄሮድስ ይህን በሰማ ጊዜ ታወከ፤ እንዲሁም መላዪቱ ኢየሩሳሌም አብራ ታወከች።

4እርሱም የካህናት አለቆችንና የአይሁድ ሃይማኖት መምህራንን በሙሉ ሰብስቦ፣ ክርስቶስ የት እንደሚወለድ ጠየቃቸው።

5እነርሱም፣ “በይሁዳ ቤተ ልሔም፤ ነቢዩ እንዲህ ብሎ ጽፎአልና አሉ፤

6“ ‘በይሁዳ ምድር የምትገኚው አንቺ ቤተ ልሔም፣ ከሌሎቹ የይሁዳ ገዦች በምንም አታንሺም፤ የሕዝቤ የእስራኤል ጠባቂ የሚሆን፣ ከአንቺ ይወጣልና።’ ”

7ከዚያም ሄሮድስ ጠቢባኑን በምስጢር አስጠርቶ በማነጋገር ኮከቡ የታየበትን ትክክለኛ ጊዜ ተረዳ።

8ጠቢባኑንም ወደ ቤተ ልሔም ልኮ፣ “ሂዱና ሕፃኑን ፈልጉ፤ እኔም ደግሞ ሄጄ እንድሰግድለት፣ እንዳገኛችሁት ወደ እኔ ተመልሳችሁ የት እንዳለ ንገሩኝ” አላቸው።

9ጠቢባኑ ንጉሡ ያለውን ከሰሙ በኋላ ጒዞአቸውን ቀጠሉ። ይህም በምሥራቅ ያዩት ኮከብ እየመራቸው ሕፃኑ እስካለበት ድረስ ወሰዳቸው።

10ኮከቡንም ሲያዩ ከመጠን በላይ ተደሰቱ።

11ወደ ቤትም በገቡ ጊዜ ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩ፤ ተንበርክከውም ሰገዱለት። ሣጥኖቻቸውን ከፍተው ወርቅ፣ ዕጣን፣ ከርቤም አቀረቡለት።

12እግዚአብሔርም ወደ ሄሮድስ እንዳይመለሱ በሕልም ባስጠነቀቃቸው መሠረት፣ መንገድ አሳብረው ወደ አገራቸው ተመለሱ።

13ጠቢባኑ ከሄዱ በኋላ የጌታ መልአክ ለዮሴፍ በሕልም ተገልጦ፣ “ተነሥ! የምትመለስበትን ጊዜ እስካስታውቅህ ድረስ ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ግብፅ በመሸሽ በዚያ ቈይ፤ ሄሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው ይሻልና” አለው።

14ስለዚህም ዮሴፍ ተነሣ፤ ሕፃኑንና እናቱን ይዞ በሌሊት ወደ ግብፅ ሄደ፤

15በዚያም ሄሮድስ እስከ ሞተበት ጊዜ ድረስ ኖረ። በዚህም፣ “ልጄን ከግብፅ ምድር ጠራሁት” በማለት እግዚአብሔር በነቢዩ አንደበት የተናገረው ቃል ተፈጸመ።

16ሄሮድስ ጠቢባኑ እንዳታለሉት በተረዳ ጊዜ በጣም ተናደደ። ከጠቢባኑ በተነገረው መሠረት ዕድሜያቸው ሁለት ዓመትና ከዚያም በታች የሆኑትን የቤተ ልሔምንና የአካባቢዋን መንደሮች ወንድ ልጆች ሁሉ ልኮ አስገደለ።

17በዚህም በነቢዩ በኤርምያስ እንዲህ ተብሎ የተነገረው ተፈጸመ፤

18“የልቅሶና የታላቅ ዋይታ ድምጽ፣ በራማ ተሰማ፤ ራሔል ስለ ልጆቿ አለቀሰች፤ መጽናናትም አልቻለችም፤ ልጆቿ ሁሉ አልቀዋልና።”

19ሄሮድስ ከሞተ በኋላ የጌታ መልአክ ለዮሴፍ በሕልም ተገልጦ፣

20“ተነሣ፤ ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ እስራኤል ምድር ተመለስ፤ ሕፃኑን ለመግደል የሚሹት ሞተዋልና” አለው።

21ዮሴፍም ተነሥቶ ሕፃኑንና እናቱን በመያዝ ወደ እስራኤል ምድር ተመለሰ፤

22ነገር ግን አርኬላዎስ በአባቱ በሄሮድስ ቦታ በይሁዳ መንገሡን በሰማ ጊዜ ወደዚያ መሄድ ፈራ። ጌታ በሕልም ስላስጠነቀቀው፣ ወደ ገሊላ አውራጃ ሄደ፤

23ናዝሬት ወደምትባል ከተማም ሄዶ መኖር ጀመረ። በዚህም በነቢያት፣ “ናዝራዊ ይባላል” ተብሎ የተነገረው ትንቢት ተፈጸመ።

ማብራሪያ

2:1-8 ከጸጋ መንገዶች እጅግ ርቀው የሚኖሩት ብዙውን ጊዜ እጅግ ብዙ ትጋትን ያሳያሉ፣ እናም ስለ ክርስቶስና ስለ ድነቱም እጅግ ብዙ ያውቃሉ። ነገር ግን ከሰው የመነጨ ጥበብ ወይም የሰዎች እውቀት ብቻ ሰውን ወደ እርሱ ሊመሩ አይችሉም። ስለ ክርስቶስ መማር ያለብን የእግዚአብሔርን ቃል በጨለማ ስፍራ እንደሚያበራ ብርሃን አድርጎ ትኩረት በመስጠት፣ እንዲሁም የመንፈስ ቅዱስን ትምህርት በመፈለግ ነው። ቀን ኮከብ በልባቸው የወጣላቸውና ስለ ክርስቶስም እውቀት ያገኙት፣ እርሱን ማምለክ ቀዳሚ ዓላማቸው ያደርጋሉ። ሄሮድስ እጅግ ሽማግሌ ቢሆንም፣ ለቤተሰቡም ፍቅር አሳይቶ የማያውቅ ቢሆንም፣ እንዲሁም አዲስ የተወለደ ሕፃን አድጎ ሰው እስከሚሆንበት ጊዜ ድረስ ራሱ የመኖር ዕድል የማይኖረው ቢሆንም፣ የተቀናቃኝ ፍርሃት ሊያስጨንቀው ጀመረ። የመሲሑን መንግሥት መንፈሳዊ ባሕርይ አልተረዳም ነበር። ከሞተ እምነት እንጠንቀቅ። አንድ ሰው ብዙ እውነቶችን ሊቀበል ይችላል፣ ሆኖም ግን ከሥልጣን ጥማቱ ወይም ከኃጢአታዊ ምኞቶቹ ጋር ስለሚጋጩ እነዚያን እውነቶች ሊጠላቸው ይችላል። እንዲህ ያለ እምነት እረፍት ያሳጣዋል፣ እውነትንና የእግዚአብሔርን ዓላማ ለመቃወምም የበለጠ ቁርጥ ውሳኔ እንዲያደርግ ያደርገዋል። በዚህም ስኬት እንደሚያገኝ በሞኝነት ሊያስብ ይችላል።

2:9-12 እነዚህ ጠቢባን ኮከቡን ባዩ ጊዜ ምን ያህል ደስታ እንደተሰማቸው የሚያውቁት እንደ እነዚያ ሰዎች ያለ ማንም የለም፤ እነርሱም ከረዥም እና ከሚያሳዝን የፈተናና የመተው ሌሊት፣ ባርነት በሚያመጣ መንፈስ ሥር ከቆዩ በኋላ፣ በመጨረሻም የእግዚአብሔር ልጆች መሆናቸውን ከገዛ መንፈሳቸው ጋር የሚመሰክርላቸውን የልጅነት መንፈስን የተቀበሉ ናቸው። እርሱ የተወለደበት ቤት ቤተ መንግሥቱ ሳይሆን አንድ ተራ ጎጆ እንደሆነ፣ እርሱን የምትንከባከበውም ምስኪን እናቱ ብቻ እንደነበረች ባዩ ጊዜ ምን ያህል ተስፋ እንደቆረጡ መገመት እንችላለን። ሆኖም እነዚህ ጠቢባን ግራ አልተጋቡም፤ የፈለጉትን ንጉሥ ስላገኙ ስጦታዎቻቸውን አቀረቡለት።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG ኢየሱስም በይሁዳ ቤተ ልሔም በንጉሡ በሄሮድስ ዘመን በተወለደ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሰብአ ሰገል፦ “የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? ኮከቡን በምሥራቅ አይተን ልንሰግድለት መጥተናልና፡” እያሉ… አማርኛ ENGNIV After Jesus was born in Bethlehem in Judea, during the time of King Herod, Magi from the east came to Jerusalem English BCV ኢየሱስ ብዘመን ንጉስ ሄሮድስ ኣብ ቤተ ልሔም ምድሪ ይሁዳ ምስ ተወለደ፥ እንሆ ኻብ ሃገር ምብራቕ ዝመፁ ሰብኣ ሰገል፥ “ኮኸቡ ብምብራቕ ርኢና ኽንሰግደሉ መፂእና ኢና እሞ፥ እቲ ዝተወለደ ን… ትግርኛ GAZBIB Bara mooticha Herodisitti, Yesus mandara Betlihem kutaa biyya Yihudaatti yommuu dhalate, kunoo namoonni ogeeyyiin urjii… Afaan Oromoo BCV GIZ ወተወሊዶ እግዚእ ኢየሱስ በቤተ ልሔም ዘይሁዳ በመዋዕለ ሄሮድስ ንጉሥ፡ ናሁ መጽኡ መሰግላን እምብሔረ ጽባሕ ወበጽሑ ውስተ ኢየሩሳሌም። giz GAZGAZ Bara mooticha Herodisitti, Yesus mandara Betlihem kutaa biyya Yihudaatti yommuu dhalate, kunoo namoonni ogeeyyiin urjii… Afaan Oromoo BCV aksum ኢየሱስ ብዘመን ንጉስ ሄሮድስ ኣብ ቤተ ልሔም ምድሪ ይሁዳ ምስ ተወለደ፥ እንሆ ኻብ ሃገር ምብራቕ ዝመፁ ሰብኣ ሰገል፥ “ኮኸቡ ብምብራቕ ርኢና ኽንሰግደሉ መፂእና ኢና እሞ፥ እቲ ዝተወለደ ን… ትግርኛ SWAHSUV Yesu alipozaliwa katika Bethlehemu ya Uyahudi zamani za mfalme Herode, tazama, mamajusi wa mashariki walifika Yerusalem… Kiswahili