የማቴዎስ ወንጌል 2

AMHEVGአማርኛ19 ጥቅሶች3:12 አዳምጥ
አዳምጥ 3:12 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ኢየሱስም በይሁዳ ቤተ ልሔም በንጉሡ በሄሮድስ ዘመን በተወለደ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሰብአ ሰገል፦ “የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? ኮከቡን በምሥራቅ አይተን ልንሰግድለት መጥተናልና፡” እያሉ ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።

3ንጉሡ ሄሮድስም ሰምቶ ደነገጠ፥ ኢየሩሳሌምም ሁሉ ከእርሱ ጋር፤

4የካህናትንም አለቆች የሕዝቡንም ጻፎች ሁሉ ሰብስቦ ክርስቶስ ወዴት እንዲወለድ ጠየቃቸው።

5እነርሱም፦ “ ‘አንቺ ቤተ ልሔም፥ የይሁዳ ምድር፥ ከይሁዳ ገዢዎች ከቶ አታንሽም፤ ሕዝቤን እስራኤልን የሚጠብቅ መስፍን ከአንቺ ይወጣልና፡’ ተብሎ በነቢይ እንዲህ ተጽፎአልና፡ በይሁዳ ቤተ ልሔም ነው፡” አሉት።

7ከዚህ በኋላ ሄሮድስ ሰብአ ሰገልን በስውር ጠርቶ ኮከቡ የታየበትን ዘመን ከእነርሱ በጥንቃቄ ተረዳ፥

8ወደ ቤተ ልሔምም እነርሱን ሰድዶ፦ “ሂዱ፥ ስለ ሕፃኑ በጥንቃቄ መርምሩ፤ ባገኛችሁትም ጊዜ እኔ ደግሞ መጥቼ እንድሰግድለት ንገሩኝ፡” አላቸው።

9እነርሱም ንጉሡን ሰምተው ሄዱ፤ እነሆም፥ በምሥራቅ ያዩት ኮከብ ሕፃኑ ባለበት ላይ መጥቶ እስኪቆም ድረስ ይመራቸው ነበር።

10ኮከቡንም ባዩ ጊዜ በታላቅ ደስታ እጅግ ደስ አላቸው።

11ወደ ቤትም ገብተው ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት፥ ወድቀውም ሰገዱለት፥ ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው እጅ መንሻ ወርቅና ዕጣን ከርቤም አቀረቡለት።

12ወደ ሄሮድስም እንዳይመለሱ በሕልም ተረድተው በሌላ መንገድ ወደ አገራቸው ሄዱ።

13እነርሱም ከሄዱ በኋላ እነሆ፥ የጌታ መልአክ በሕልም ለዮሴፍ ታይቶ፦ “ሄሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው ይፈልገዋልና ተነሣ፥ ሕፃኑንና እናቱንም ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ፥ እስክነግርህም ድረስ በዚያ ተቀመጥ፡” አለው።

14እርሱም ተነሥቶ ሕፃኑንና እናቱን በሌሊት ያዘና ከጌታ ዘንድ በነቢይ፦ “ልጄን ከግብፅ ጠራሁት፡” የተባለው እንዲፈጸም ወደ ግብፅ ሄደ፥ ሄሮድስም እስኪሞት ድረስ በዚያ ኖረ።

16ከዚህ በኋላ ሄሮድስ ሰብአ ሰገል እንደ ተሣለቁበት ባየ ጊዜ እጅግ ተቆጣና ልኮ ከሰብአ ሰገል እንደ ተረዳው ዘመን በቤተ ልሔምና በአውራጃዋ የነበሩትን፥ ሁለት ዓመት የሆናቸውን ከዚያም የሚያንሱትን ሕፃናት ሁሉ አስገደለ።

17ያን ጊዜ በነቢዩ በኤርምያስ፦ “ድምፅ በራማ ተሰማ፥ ልቅሶና ብዙ ዋይታ፤ ራሔል ስለ ልጆችዋ አለቀሰች፥ መጽናናትም አልወደደችም፥ የሉምና፡” የተባለው ተፈጸመ።

19ሄሮድስም ከሞተ በኋላ፥ እነሆ፥ የጌታ መልአክ በግብፅ ለዮሴፍ በሕልም ታይቶ፦

20“የሕፃኑን ነፍስ የፈለጉት ሞተዋልና ተነሣ፥ ሕፃኑን እናቱንም ይዘህ ወደ እስራኤል አገር ሂድ፡” አለ።

21እርሱም ተነሥቶ ሕፃኑንና እናቱን ያዘና ወደ እስራኤል አገር ገባ።

22በአባቱም በሄሮድስ ፈንታ አርኬላዎስ በይሁዳ እንደ ነገሠ በሰማ ጊዜ፥ ወደዚያ መሄድን ፈራ፤ በሕልምም ተረድቶ ወደ ገሊላ አገር ሄደ፤

23በነቢያት፦ “ናዝራዊ ይባላል፡” የተባለው ይፈጸም ዘንድ፥ ናዝሬት ወደምትባል ከተማ መጥቶ ኖረ።

ማብራሪያ

2:1-8 ከጸጋ መንገዶች እጅግ ርቀው የሚኖሩት ብዙውን ጊዜ እጅግ ብዙ ትጋትን ያሳያሉ፣ እናም ስለ ክርስቶስና ስለ ድነቱም እጅግ ብዙ ያውቃሉ። ነገር ግን ከሰው የመነጨ ጥበብ ወይም የሰዎች እውቀት ብቻ ሰውን ወደ እርሱ ሊመሩ አይችሉም። ስለ ክርስቶስ መማር ያለብን የእግዚአብሔርን ቃል በጨለማ ስፍራ እንደሚያበራ ብርሃን አድርጎ ትኩረት በመስጠት፣ እንዲሁም የመንፈስ ቅዱስን ትምህርት በመፈለግ ነው። ቀን ኮከብ በልባቸው የወጣላቸውና ስለ ክርስቶስም እውቀት ያገኙት፣ እርሱን ማምለክ ቀዳሚ ዓላማቸው ያደርጋሉ። ሄሮድስ እጅግ ሽማግሌ ቢሆንም፣ ለቤተሰቡም ፍቅር አሳይቶ የማያውቅ ቢሆንም፣ እንዲሁም አዲስ የተወለደ ሕፃን አድጎ ሰው እስከሚሆንበት ጊዜ ድረስ ራሱ የመኖር ዕድል የማይኖረው ቢሆንም፣ የተቀናቃኝ ፍርሃት ሊያስጨንቀው ጀመረ። የመሲሑን መንግሥት መንፈሳዊ ባሕርይ አልተረዳም ነበር። ከሞተ እምነት እንጠንቀቅ። አንድ ሰው ብዙ እውነቶችን ሊቀበል ይችላል፣ ሆኖም ግን ከሥልጣን ጥማቱ ወይም ከኃጢአታዊ ምኞቶቹ ጋር ስለሚጋጩ እነዚያን እውነቶች ሊጠላቸው ይችላል። እንዲህ ያለ እምነት እረፍት ያሳጣዋል፣ እውነትንና የእግዚአብሔርን ዓላማ ለመቃወምም የበለጠ ቁርጥ ውሳኔ እንዲያደርግ ያደርገዋል። በዚህም ስኬት እንደሚያገኝ በሞኝነት ሊያስብ ይችላል።

2:9-12 እነዚህ ጠቢባን ኮከቡን ባዩ ጊዜ ምን ያህል ደስታ እንደተሰማቸው የሚያውቁት እንደ እነዚያ ሰዎች ያለ ማንም የለም፤ እነርሱም ከረዥም እና ከሚያሳዝን የፈተናና የመተው ሌሊት፣ ባርነት በሚያመጣ መንፈስ ሥር ከቆዩ በኋላ፣ በመጨረሻም የእግዚአብሔር ልጆች መሆናቸውን ከገዛ መንፈሳቸው ጋር የሚመሰክርላቸውን የልጅነት መንፈስን የተቀበሉ ናቸው። እርሱ የተወለደበት ቤት ቤተ መንግሥቱ ሳይሆን አንድ ተራ ጎጆ እንደሆነ፣ እርሱን የምትንከባከበውም ምስኪን እናቱ ብቻ እንደነበረች ባዩ ጊዜ ምን ያህል ተስፋ እንደቆረጡ መገመት እንችላለን። ሆኖም እነዚህ ጠቢባን ግራ አልተጋቡም፤ የፈለጉትን ንጉሥ ስላገኙ ስጦታዎቻቸውን አቀረቡለት።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV After Jesus was born in Bethlehem in Judea, during the time of King Herod, Magi from the east came to Jerusalem English BCV ኢየሱስ ብዘመን ንጉስ ሄሮድስ ኣብ ቤተ ልሔም ምድሪ ይሁዳ ምስ ተወለደ፥ እንሆ ኻብ ሃገር ምብራቕ ዝመፁ ሰብኣ ሰገል፥ “ኮኸቡ ብምብራቕ ርኢና ኽንሰግደሉ መፂእና ኢና እሞ፥ እቲ ዝተወለደ ን… ትግርኛ GAZBIB Bara mooticha Herodisitti, Yesus mandara Betlihem kutaa biyya Yihudaatti yommuu dhalate, kunoo namoonni ogeeyyiin urjii… Afaan Oromoo BCV GIZ ወተወሊዶ እግዚእ ኢየሱስ በቤተ ልሔም ዘይሁዳ በመዋዕለ ሄሮድስ ንጉሥ፡ ናሁ መጽኡ መሰግላን እምብሔረ ጽባሕ ወበጽሑ ውስተ ኢየሩሳሌም። giz GAZGAZ Bara mooticha Herodisitti, Yesus mandara Betlihem kutaa biyya Yihudaatti yommuu dhalate, kunoo namoonni ogeeyyiin urjii… Afaan Oromoo BCV aksum ኢየሱስ ብዘመን ንጉስ ሄሮድስ ኣብ ቤተ ልሔም ምድሪ ይሁዳ ምስ ተወለደ፥ እንሆ ኻብ ሃገር ምብራቕ ዝመፁ ሰብኣ ሰገል፥ “ኮኸቡ ብምብራቕ ርኢና ኽንሰግደሉ መፂእና ኢና እሞ፥ እቲ ዝተወለደ ን… ትግርኛ AMHNIV በንጉሡ በሄሮድስ ዘመን፣ ኢየሱስ በቤተልሔም ይሁዳ ከተወለደ በኋላ ጠቢባን ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም መጥተው፣ አማርኛ SWAHSUV Yesu alipozaliwa katika Bethlehemu ya Uyahudi zamani za mfalme Herode, tazama, mamajusi wa mashariki walifika Yerusalem… Kiswahili