የማቴዎስ ወንጌል 15

AMHEVGአማርኛ39 ጥቅሶች4:44 አዳምጥ
አዳምጥ 4:44 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1በዚያን ጊዜ ጻፎችና ፈሪሳውያን ከኢየሩሳሌም ወደ ኢየሱስ ቀረቡና፦

2“ደቀ መዛሙርትህ ስለ ምን የሽማግሎችን ወግ ይተላለፋሉ? እንጀራ ሲበሉ እጃቸውን አይታጠቡምና፡” አሉት።

3እርሱም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ “እናንተስ ስለ ወጋችሁ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ስለ ምን ትተላለፋላችሁ?

4እግዚአብሔር፦ ‘አባትህንና እናትህን አክብር፤’ ደግሞ፦ ‘አባቱን ወይም እናቱን የሰደበ ፈጽሞ ይሙት፡’ ብሎአልና፤

5“እናንተ ግን፤ አባቱን ወይም እናቱን፦ ‘ከእኔ የምትጠቀምበት መባ ነው፡’ የሚል ሁሉ፥

6‘አባቱን ወይም እናቱን አያከብርም’ ትላላችሁ፤ ስለ ወጋችሁም የእግዚአብሔርን ቃል ሻራችሁ።

7“እናንተ ግብዞች፥ ኢሳይያስ ስለ እናንተ፦

8‘ይህ ሕዝብ በከንፈሩ ያከብረኛል፥ ልቡ ግን ከእኔ በጣም የራቀ ነው፤

9የሰውም ሥርዓት የሆነ ትምህርት እያስተማሩ በከንቱ ያመልኩኛል፣ ብሎ በእውነት ትንቢት ተናገረ።”

10ሕዝቡንም ጠርቶ፦ “ስሙ አስተውሉም፤

11ሰውን የሚያረክሰው ወደ አፍ የሚገባ አይደለም፥ ከአፍ የሚወጣው ግን ሰውን የሚያረክሰው ይህ ነው፡” አላቸው።

12በዚያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ቀርበው፦ “ፈሪሳውያን ይህን ቃል ሰምተው እንደ ተሰናከሉ አወቅህን?” አሉት።

13እርሱ ግን መልሶ፦ “የሰማዩ አባቴ ያልተከለው ተክል ሁሉ ይነቀላል።

14ተዉአቸው፤ ዕውሮችን የሚመሩ ዕውሮች ናቸው፤ ዕውርም ዕውርን ቢመራው ሁለቱም ወደ ጉድጓድ ይወድቃሉ፡” አለ።

15ጴጥሮስም መልሶ፦ “ምሳሌውን ተርጕምልን፡” አለው።

16ኢየሱስም እንዲህ አለ፦ “እናንተ ደግሞ እስካሁን የማታስተውሉ ናችሁን?

17ወደ አፍ የሚገባ ሁሉ ወደ ሆድ አልፎ ወደ እዳሪ እንዲጣል አትመለከቱምን?

18ከአፍ የሚወጣ ግን ከልብ ይወጣል፥ ሰውንም የሚያረክሰው ያ ነው።

19“ከልብ ክፉ አሳብ፥ መግደል፥ ምንዝርነት፥ ዝሙት፥ መስረቅ፥ በውሸት መመስከር፥ ስድብ ይወጣልና።

20ሰውን የሚያረክሰው ይህ ነው እንጂ፥ ባልታጠበ እጅ መብላትስ ሰውን አያረክሰውም።”

21ኢየሱስም ከዚያ ወጥቶ ወደ ጢሮስና ወደ ሲዶና አገር ሄደ።

22እነሆም፥ ከነናዊት ሴት ከዚያ አገር ወጥታ፦ “ጌታ ሆይ፥ የዳዊት ልጅ፥ ማረኝ፤ ልጄን ጋኔን ክፉኛ ይዞአታል፡” ብላ ጮኸች።

23እርሱ ግን አንዳች አልመለሰላትም። ደቀ መዛሙርቱም ቀርበው፦ “በኋላችን ትጮኻለችና አሰናብታት፡” እያሉ ለመኑት።

24እርሱም መልሶ፦ “ከእስራኤል ቤት ለጠፉት በጎች በቀር አልተላክሁም፡” አለ።

25እርስዋ ግን መጥታ፦ “ጌታ ሆይ፥ እርዳኝ፡” እያለች ሰገደችለት።

26እርሱ ግን መልሶ፦ “የልጆችን እንጀራ ይዞ ለቡችሎች መጣል አይገባም” አለ።

27እርስዋም፦ “አዎን ጌታ ሆይ፤ ቡችሎችም እኮ ከጌቶቻቸው ማዕድ የወደቀውን ፍርፋሪ ይበላሉ፡” አለች።

28በዚያን ጊዜ ኢየሱስ መልሶ፦ “አንቺ ሴት፥ እምነትሽ ታላቅ ነው፤ እንደወደድሽ ይሁንልሽ” አላት። ልጅዋም ከዚያች ሰዓት ጀምሮ ዳነች።

29ኢየሱስም ከዚያ አልፎ ወደ ገሊላ ባሕር አጠገብ መጣ፥ ወደ ተራራም ወጥቶ በዚያ ተቀመጠ።

30ብዙ ሕዝብም አንካሶችን፥ ዕውሮችንም፥ ዲዳዎችንም፥ ጉንድሾችንም፥ ሌሎችንም ብዙ ይዘው ወደ እርሱ ቀረቡ፥ በኢየሱስም እግር አጠገብ ጣሉአቸው፤ ፈወሳቸውም፤

31ስለዚህም ሕዝቡ ዲዳዎች ሲናገሩ፥ ጉንድሾችም ሲድኑ፥ አንካሶችም ሲሄዱ፥ ዕውሮችም ሲያዩ አይተው ተደነቁ፤ የእስራኤልንም አምላክ አከበሩ።

32ኢየሱስም ደቀ መዛሙርቱን ጠርቶ፦ “ሕዝቡ ከእኔ ጋር እስካሁን ሦስት ቀን ውለዋልና የሚበሉት ስለ ሌላቸው አዝንላቸዋለሁ፤ በመንገድም እንዳይዝሉ ጦማቸውን ላሰናብታቸው አልወድም፡” አላቸው።

33ደቀ መዛሙርቱም፦ “ይህን ያህል ሕዝብ የሚያጠግብ ይህን ያህል እንጀራ በምድረ በዳ ከወዴት እናገኛለን?” አሉት።

34ኢየሱስም፦ “ስንት እንጀራ አላችሁ?” አላቸው። እነርሱም፦ “ሰባት፥ ጥቂትም ትንሽ ዓሣ” አሉት።

35ሕዝቡም በምድር ላይ እንዲቀመጡ አዘዘ፤

36ሰባቱንም እንጀራ ዓሣውንም ይዞ አመሰገነ ቈርሶም ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠ፥ ደቀ መዛሙርቱም ለሕዝቡ።

37ሁሉም በሉና ጠገቡ፥ የተረፈውንም ቁርስራሽ ሰባት ቅርጫት ሙሉ አነሡ።

38የበሉትም ከሴቶችና ከልጆች በቀር አራት ሺህ ወንዶች ነበሩ።

39ሕዝቡንም ካሰናበተ በኋላ ወደ ታንኳይቱ ገብቶ ወደ መጌዶል አገር መጣ።

ማብራሪያ

15:1-9 ወደ እግዚአብሔር ሕግጋት የሚጨመሩ ነገሮች ጥበቡን ይተቻሉ፤ የሚያስፈልገውን ነገር ትቶ ሰው ሊያሟላው እንደሚችል አድርገው ያሳያሉ። በሆነ መንገድ ወይም በሌላ፣ እነዚህ ጭማሪዎች ሁልጊዜ ሰዎችን እግዚአብሔርን እንዳይታዘዙ ይመራሉ። ለተጻፈው የእግዚአብሔር ቃል ምን ያህል አመስጋኞች መሆን ይገባናል! የመጽሐፍ ቅዱስ ሃይማኖት በማንኛውም የሰው ልጅ ጭማሪ—በትምህርትም ሆነ በተግባር—ሊሻሻል ይችላል ብለን በፍጹም እንዳናስብ። የተባረከው ጌታችን ወጎቻቸውን የራሳቸው ፈጠራ እንደሆኑ ተናግሯል፤ ይህ ግልጽ የሆነበትን አንድ ምሳሌም ጠቁሟል፤ እርሱም አምስተኛውን ትእዛዝ መተላለፋቸው ነበር። የወላጅ ፍላጎት እርዳታ በጠየቀ ጊዜ፣ ሊለቁት የሚችሉትን ሁሉ ለቤተ መቅደሱ እንደለዩ ተከራከሩ—ምንም እንኳን እነሱ ራሳቸው ከእርሱ ጋር ባይለያዩም (ሳይለዩት ቢይዙትም)፤ ስለዚህም ወላጆቻቸው ከእነርሱ ምንም መጠበቅ እንደሌለባቸው ተናገሩ። ይህ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ሙሉ በሙሉ ከንቱ ማድረግ ነበር። የግብዞች ፍርድ በአጭር ቃል ተቀምጧል፦ "በከንቱ ያመልኩኛል።" ይህ እግዚአብሔርንም አያስደስትም፣ ለእነርሱም አይጠቅምም። በከንቱ ይመካሉ፤ ከንቱነትም ዋጋቸው ይሆናል።

ማቴዎስ 15:10-20 ክርስቶስ ሊፈሩት የሚገባው ርኩሰት በአፋቸው እንደ ምግብ ከሚገባው ሳይሆን፣ ከአፋቸው ከሚወጣው እንደሆነ ያሳያል፤ ይህም የልባቸውን ክፋት የሚያመለክት ነው። በመንፈስ ቅዱስ የሚሰጡት እንደገና የመወለድ ጸጋዎች ካልሆኑ በቀር በነፍስ ውስጥ የሚጸና ምንም ነገር የለም፤ ወደ ቤተ ክርስቲያንም ሊገባ የሚገባው ከላይ የመጣው ብቻ ነው። ስለዚህ፣ እውነት በግልጽና በጊዜው ሲገለጥ የሚሰናከል ሰው ቢኖር፣ እኛ በእርሱ ልንረበሽ አይገባም። ደቀ መዛሙርቱም በዚህ ጉዳይ ላይ በተሻለ ሁኔታ እንዲያስተምራቸው ጠየቁ። ደካማ አእምሮ በክርስቶስ ቃል ላይ ቢጠራጠር፣ ቅን ልብና ፈቃደኛ አእምሮ ግን ትምህርትን ይሻሉ። ልብ እጅግ ክፉ ነው (ኤር 17:9)፤ በቃልም ሆነ በግብር የሚፈጸም ኃጢአት ሁሉ በመጀመሪያ በልብ ያልነበረ የለምና። እነዚህ ሁሉ ከሰው ይወጣሉ፣ በልብ ውስጥ የሰፈረና የሚሰራ የክፋት ፍሬዎችም ናቸው። ክርስቶስ ሲያስተምር፣ ለሰዎች የራሳቸውን ልብ ተንኮለኛነትና ክፋት ያሳያል፤ ራሳቸውን እንዲያዋርዱ ያስተምራቸዋል፤ ለኃጢአትና ለርኩሰት በተከፈተው ምንጭ እንዲነጹም ፍለጋ እንዲያደርጉ ያስተምራቸዋል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6