ትንቢተ ሚልክያ 3

AMHNIVአማርኛ18 ጥቅሶች3:59 አዳምጥ
አዳምጥ 3:59 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1“እነሆ፤ በፊቴ መንገድ እንዲያዘጋጅ መልእክተኛዬን እልካለሁ፤ የምትፈልጉት ጌታ በድንገት ወደ ቤተ መቅደሱ ይመጣል፤ ደስ የምትሰኙበትም የቃል ኪዳኑ መልእክተኛ ይመጣል” ይላል እግዚአብሔር ጸባኦት።

2እርሱ የሚመጣበትን ቀን ማን ሊቋቋመው ይችላል? በሚገለጥበትስ ጊዜ በፊቱ መቆም የሚችል ማን ነው? እርሱ እንደ አንጥረኛ እሳት ወይም እንደ ልብስ አጣቢ ሳሙና ነውና።

3ብርን እንደሚያነጥርና እንደሚያነጻ ሰው ይቀመጣል፤ ሌዋውያንንም አንጽቶ እንደ ወርቅና እንደ ብር ያጠራቸዋል፤ ከዚያም እግዚአብሔር ቊርባንን በጽድቅ የሚያቀርቡ ሰዎች ይኖሩታል፤

4በዚያ ጊዜ የይሁዳና የኢየሩሳሌም ቊርባን እንዳለፉት ቀናትና እንደ ቀድሞው ዘመን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ይሆናል።

5“ስለዚህ እኔ ለፍርድ ወደ እናንተ እመጣለሁ፤ በመተተኞች፣ በአመንዝራዎች፣ በሐሰት በሚምሉ፣ የሠራተኞችን ደመወዝ በሚከለክሉ፣ መበለቶችንና ድኻ አደጉን በሚጨቍኑ፣ መጻተኞችን ፍትሕ በሚነፍጉ፣ እኔንም በማይፈሩት ላይ እመሰክርባቸው ዘንድ እፈጥናለሁ” ይላል እግዚአብሔር ጸባኦት።

6“እኔ እግዚአብሔር አልለወጥም፤ ስለዚህ እናንተ የያዕቆብ ልጆች ሆይ፤ አልጠፋችሁም።

7ከአባቶቻችሁ ዘመን ጀምሮ ከትእዛዛቴ ፈቀቅ ብላችኋል፤ አልጠበቃችኋቸውምም፤ ወደ እኔ ተመለሱ፤ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ” ይላል እግዚአብሔር ጸባኦት። “እናንተ ግን፣ የምንመለሰው እንዴት ነው ትላላችሁ?”

8“ሰው እግዚአብሔርን ይሰርቃልን?” እናንተ ግን ትሰርቁኛላችሁ። “እናንተ ግን፣ ‘እንዴት እንሰርቅሃለን?’ ትላላችሁ። “ዐሥራትና መባ ትሰርቁኛላችሁ፤

9እናንተም፣ መላው ሕዝባችሁም ስለምትሰርቁኝ የተረገማችሁ ናችሁ።

10በቤቴ መብል እንዲኖር፣ እኔንም በዚህ እንድትፈትኑኝ ዐሥራቱን ሁሉ ወደ ጐተራ አስገቡ፤” ይላል እግዚአብሔር ጸባኦት፤ “የሰማይን መስኮት የማልከፍትላችሁ፣ የተትረፈረፈ በረከትንም ማስቀመጫ እስክታጡ ድረስ የማላፈስላችሁ ከሆነ ተመልከቱ።

11ስለ እናንተ ተባዩን እገሥጻለሁ፤ አዝመራችሁን አይበላም፤ ዕርሻ ላይ ያለ የወይን ተክላችሁም ፍሬ አልባ አይሆንም” ይላል እግዚአብሔር ጸባኦት።

12“ከዚያም በኋላ የተድላ ምድር ስለምትሆኑ ሕዝቦች ሁሉ የተባረከ ሕዝብ ብለው ይጠሯችኋል” ይላል እግዚአብሔር ጸባኦት።

13“በእኔ ላይ የድፍረት ቃል ተናግራችኋል” ይላል እግዚአብሔር። “እናንተ ግን፣ ‘በአንተ ላይ የተናገርነው ምንድን ነው?’ ትላላችሁ።

14“እንዲህም ብላችኋል፤ ‘እግዚአብሔርን ማገልገል ከንቱ ነው፤ እርሱ የሚፈልገውን ሁሉ በማድረግና በእግዚአብሔር ጸባኦት ፊት ሐዘንተኞች ሆነን በመመላለስ ምን ተጠቀምን?

15አሁን ግን ትዕቢተኞችን ቡሩካን እንላቸዋለን፤ ክፉ አድራጊዎች ይበለጽጋሉ፤ እግዚአብሔርን የሚፈታተኑትም ያመልጣሉ።’ ”

16በዚያን ጊዜ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች እርስ በርሳቸው ተነጋገሩ፤ እግዚአብሔር አዳመጠ፤ ሰማቸውም፤ እግዚአብሔርን ለሚፈሩና ስሙን ለሚያከብሩ በእርሱ ፊት የመታሰቢያ መጽሐፍ ተጻፈ።

17“እኔ በምሠራበት ቀን እነርሱ የገዛ ገንዘቤ ይሆናሉ” ይላል እግዚአብሔር ጸባኦት፤ “አባት የሚያገለግለውን ልጁን እንደሚታደግ ሁሉ እኔም እታደጋቸዋለሁ።

18በዚያን ጊዜም እንደ ገና በጻድቁና በኀጢአተኛው መካከል፣ እግዚአብሔርን በሚያገለግለውና በማያገለግለው መካከል ያለውን ልዩነት ታያላችሁ።

ማብራሪያ

፫፡፩-፮ የዚህ ምዕራፍ የመጀመሪያ ቃላት በዚያ ዘመን ለነበሩት ዘባቾች መልስ የሚሆኑ ይመስላሉ። እዚህም የመጥምቁ ዮሐንስ መገለጥ ትንቢት ተሰጥቷል። እርሱ የክርስቶስ መንገድ ጠራጊ ነው። ሰዎችን ወደ ንስሐ በመጥራት መንገዱን ከፊቱ ያዘጋጃል። መሲሑ ለረጅም ጊዜ 'የሚመጣው እርሱ' ተብሎ ሲጠራ ኖሯል፤ አሁን ግን በጥቂት ጊዜ ውስጥ ይመጣል። እርሱ የቃል ኪዳኑ መልእክተኛ ነው። ኢየሱስን የሚሹት ብዙ ጊዜ ባልጠበቁት ጊዜም ጭምር በእርሱ ደስታ ያገኛሉ። ጌታ ኢየሱስ በቃሉ አገልግሎትና በመንፈሱ ውግዘት የኃጢአተኛውን ልብ መቅደሱ እንዲሆን ያዘጋጃል፤ እርሱም የሰላምና የመጽናናት መልእክተኛ ሆኖ ወደዚያ ይገባል። ምንም ግብዝ ወይም ቅርጻዊ ትምህርቱን ሊቋቋም ወይም በፍርድ ወንበሩ ፊት ሊቆም አይችልም። ክርስቶስ ሰዎችን ለመለየት፤ ክቡርንና ንቁውን ለመለየት መጣ። እርሱ እንደ አንጥረኛ ይቀመጣል። ክርስቶስ በወንጌሉ ቤተ ክርስቲያኑን ያነጻል እንዲሁም ያድሳል፤ ከእርሱ ጋር በሚሰራው በመንፈሱም ነፍሳትን እንደገና ይወልዳል እንዲሁም ያነጻል። በእነርሱ ውስጥ የሚገኘውን ዝገት ያስወግዳል። ችሎታዎቻቸውን ከንቱና የማይጠቅሙ የሚያደርጉትን ብልሹነቶቻቸውን ይለያል። ምእመኑ አዳኙ ወርቁን የሚያነጻበትን የመከራና የፈተና የእሳት ፈተና መፍራት አያስፈልገውም። ለጥቅሙ ከሚያስፈልገው በላይ ኃይለኛ ወይም ረጅም እንዳይሆን ይጠነቀቃል፤ ይህም ፈተና ከክፉዎች ፈተና ፈጽሞ በተለየ መንገድ ያበቃል። ክርስቶስ ስለ እነርሱ ምልጃ በማድረግ ተቀባይነት እንዲያገኙ ያደርጋል። የእግዚአብሔር ፍርሃት በሌለበት ምንም መልካም ነገር አይጠበቅም። ክፋት ኃጢአተኞችን ያሳድዳል። እግዚአብሔር የማይለወጥ ነው። በክፉ ሥራዎች ላይ የተፈረደው ፍርድ በፍጥነት ባይፈጸምም፣ ይፈጸማል፤ ጌታ ለኃጢአት እንደሁልጊዜው ሁሉ ጠላት ነው። ይህን ሁላችንም በራሳችን ላይ ተግባራዊ ማድረግ እንችላለን። የማይለወጥ አምላክ ስለምናገለግል፣ እንዲሁም ምሕረቱ አያልቅምና አንጠፋም።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG እነሆ፥ መልእክተኛዬን እልካለሁ፥ መንገድንም በፊቴ ያስተካክላል፤ እናንተም የምትፈልጉት ጌታ በድንገት ወደ መቅደሱ ይመጣል፤ የምትወዱትም የቃል ኪዳን መልእክተኛ፥ እነሆ፥ ይመጣል፥ ይላል የሠ… አማርኛ ENGNIV “See, I will send my messenger, who will prepare the way before me. Then suddenly the Lord you are seeking will come to… English BCV “እንሆ፥ መንገዲ ዝፀርግ ልኡኸይ ቀቅድመይ እልእኽ ኣለኹ። እቲ እትደልይዎ ጐይታ ኸዓ ናብ መቕደሱ ድንገት ክመፅእ እዩ፤ እቲ እትሕጐሱሉ መልእኽተኛ ቃል ኪዳን፥ እንሆ፥ ይመፅእ ኣሎ” ይብል … ትግርኛ GAZBIB Waaqayyo gooftaan maccaa,“Kunoo, ani ergamaa koo isa karaa anaaf qopheessu of dura nan erga; dingatas gooftichi inni is… Afaan Oromoo BCV GIZ ናሁ አነ እፌኑ መልእክየ ዘይጸይሕ ወይርኢ ፍኖትየ ቅድመ ገጽከ፡ ወይመጽእ ውስተ ጽርሑ ግብተ እግዚአብሔር ዘአንትሙ ተኀሥሡ መልአከ ሥርዓትየ ዘአንትሙ ትፈቅዱ፤ ናሁ ይመጽእ፡ ይቤ እግዚአብሔ… giz GAZGAZ Waaqayyo gooftaan maccaa,“Kunoo, ani ergamaa koo isa karaa anaaf qopheessu of dura nan erga; dingatas gooftichi inni is… Afaan Oromoo BCV aksum “እንሆ፥ መንገዲ ዝፀርግ ልኡኸይ ቀቅድመይ እልእኽ ኣለኹ። እቲ እትደልይዎ ጐይታ ኸዓ ናብ መቕደሱ ድንገት ክመፅእ እዩ፤ እቲ እትሕጐሱሉ መልእኽተኛ ቃል ኪዳን፥ እንሆ፥ ይመፅእ ኣሎ” ይብል … ትግርኛ SWAHSUV Angalieni, namtuma mjumbe wangu, naye ataitengeneza njia mbele yangu; naye Bwana mnayemtafuta atalijilia hekalu lake gh… Kiswahili