ትንቢተ ሚልክያ 3

AMHEVGአማርኛ18 ጥቅሶች3:25 አዳምጥ
አዳምጥ 3:25 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1እነሆ፥ መልእክተኛዬን እልካለሁ፥ መንገድንም በፊቴ ያስተካክላል፤ እናንተም የምትፈልጉት ጌታ በድንገት ወደ መቅደሱ ይመጣል፤ የምትወዱትም የቃል ኪዳን መልእክተኛ፥ እነሆ፥ ይመጣል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።

2ነገር ግን እርሱ እንደ አንጥረኛ እሳትና እንደ አጣቢ ሳሙና ነውና የሚመጣበትን ቀን መታገሥ የሚችል ማን ነው? እርሱስ በተገለጠ ጊዜ የሚቆም ማን ነው?

3እርሱም ብርን እንደሚያነጥርና እንደሚያጠራ ሰው ይቀመጣል፥ የሌዊንም ልጆች ያጠራል፥ እንደ ወርቅና እንደ ብርም ያነጥራቸዋል፤ እነርሱም ለእግዚአብሔር በጽድቅ ቍርባንን የሚያቀርቡ ይሆናሉ።

4እግዚአብሔርም እንደ ዱሮው ዘመንና እንደ ቀደሙት ዓመታት በይሁዳና በኢየሩሳሌም ቍርባን ደስ ይለዋል።

5ለፍርድ ወደ እናንተ እቀርባለሁ፤ በመተተኞችና በአመንዝሮች፥ በሐሰትም በሚምሉ፥ የምንደኛውን ደመወዝ በሚከለክሉ፥ መበለቲቱንና ድሀ አደጉን በሚያስጨንቁ፥ የመጻተኛውንም ፍርድ በሚያጣምሙ፥ እኔንም በማይፈሩ ላይ ፈጣን ምስክር እሆንባቸዋለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።

6እኔ እግዚአብሔር አልለወጥም፤ እናንተ የያዕቆብ ልጆች ሆይ፥ ስለዚህ የጠፋችሁ አይደላችሁም።

7ከአባቶቻችሁ ዘመን ጀምር ከሥርዓቴ ፈቀቅ ብላችኋል፥ እርስዋንም አልጠበቃችሁም። ወደ እኔ ተመለሱ፥ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።¶ እናንተ ግን፦ “የምንመለሰው በምንድር ነው?” ብላችኋል።

8ሰው እግዚአብሔርን ይሰርቃልን? እናንተ ግን እኔን ሰርቃችኋል።¶ እናንተም፦ “የሰረቅንህ በምንድር ነው?” ብላችኋል።¶ በአሥራትና በበኵራት ነው።

9እናንተ፥ ይህ ሕዝብ ሁሉ፥ እኔን ሰርቃችኋልና በእርግማን ርጉሞች ናችሁ።

10በቤቴ ውስጥ መብል እንዲሆን አሥራቱን ሁሉ ወደ ጎተራ አግቡ፤ የሰማይንም መስኮት ባልከፍትላችሁ፥ በረከትንም አትረፍርፌ ባላፈስስላችሁ በዚህ ፈትኑኝ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።

11ስለ እናንተ ነቀዙን እገሥጻለሁ፥ የምድራችሁንም ፍሬ አያጠፋም፤ በእርሻችሁም ያለው ወይን ፍሬውን አያረግፍም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።

12የተድላ ምድር ትሆናላችሁና፥ አሕዛብ ሁሉ፡ ብፁዓን፡ ብለው ይጠሩአችኋል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።

13“ቃላችሁ በእኔ ላይ ድፍረት ሆኖአል፥” ይላል እግዚአብሔር።¶ እናንተ ግን፦ “በአንተ ላይ ደፍረን የተናገርነው በምንድር ነው?” ብላችኋል።

14እናንተም፦ “እግዚአብሔርን ማገልገል ከንቱ ነው፤ ትእዛዙንስ በመጠበቅ፥ በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ፊት ኀዘንተኞች ሆነን በመሄድ ምን ይረባናል?

15አሁንም የሚታበዩትን ሰዎች ብፁዓን ብለን እንጠራቸዋለን፤ ክፉንም የሚሠሩ ጸንተዋል እግዚአብሔርንም ይፈታተናሉ፥ ያመልጣሉም፡” ብላችኋል።

16የዚያን ጊዜ እግዚአብሔርን የሚፈሩ እርስ በእርሳቸው ተነጋገሩ፤¶ እግዚአብሔርም አደመጠ፥ ሰማም፥¶ እግዚአብሔርንም ለሚፈሩ ስሙንም ለሚያስቡ የመታሰቢያ መጽሐፍ በፊቱ ተጻፈ።

17እኔ በምሠራበት ቀን እነርሱ የእኔ ገንዘብ ይሆናሉ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ ሰውም የሚያገለግለውን ልጁን እንደሚምር፥ እንዲሁ እምራቸዋለሁ።

18ተመልሳችሁም በጻድቁና በኃጢአተኛው መካከል፥ ለእግዚአብሔር በሚገዛውና በማይገዛው መካከል ትለያላችሁ።

ማብራሪያ

፫፡፩-፮ የዚህ ምዕራፍ የመጀመሪያ ቃላት በዚያ ዘመን ለነበሩት ዘባቾች መልስ የሚሆኑ ይመስላሉ። እዚህም የመጥምቁ ዮሐንስ መገለጥ ትንቢት ተሰጥቷል። እርሱ የክርስቶስ መንገድ ጠራጊ ነው። ሰዎችን ወደ ንስሐ በመጥራት መንገዱን ከፊቱ ያዘጋጃል። መሲሑ ለረጅም ጊዜ 'የሚመጣው እርሱ' ተብሎ ሲጠራ ኖሯል፤ አሁን ግን በጥቂት ጊዜ ውስጥ ይመጣል። እርሱ የቃል ኪዳኑ መልእክተኛ ነው። ኢየሱስን የሚሹት ብዙ ጊዜ ባልጠበቁት ጊዜም ጭምር በእርሱ ደስታ ያገኛሉ። ጌታ ኢየሱስ በቃሉ አገልግሎትና በመንፈሱ ውግዘት የኃጢአተኛውን ልብ መቅደሱ እንዲሆን ያዘጋጃል፤ እርሱም የሰላምና የመጽናናት መልእክተኛ ሆኖ ወደዚያ ይገባል። ምንም ግብዝ ወይም ቅርጻዊ ትምህርቱን ሊቋቋም ወይም በፍርድ ወንበሩ ፊት ሊቆም አይችልም። ክርስቶስ ሰዎችን ለመለየት፤ ክቡርንና ንቁውን ለመለየት መጣ። እርሱ እንደ አንጥረኛ ይቀመጣል። ክርስቶስ በወንጌሉ ቤተ ክርስቲያኑን ያነጻል እንዲሁም ያድሳል፤ ከእርሱ ጋር በሚሰራው በመንፈሱም ነፍሳትን እንደገና ይወልዳል እንዲሁም ያነጻል። በእነርሱ ውስጥ የሚገኘውን ዝገት ያስወግዳል። ችሎታዎቻቸውን ከንቱና የማይጠቅሙ የሚያደርጉትን ብልሹነቶቻቸውን ይለያል። ምእመኑ አዳኙ ወርቁን የሚያነጻበትን የመከራና የፈተና የእሳት ፈተና መፍራት አያስፈልገውም። ለጥቅሙ ከሚያስፈልገው በላይ ኃይለኛ ወይም ረጅም እንዳይሆን ይጠነቀቃል፤ ይህም ፈተና ከክፉዎች ፈተና ፈጽሞ በተለየ መንገድ ያበቃል። ክርስቶስ ስለ እነርሱ ምልጃ በማድረግ ተቀባይነት እንዲያገኙ ያደርጋል። የእግዚአብሔር ፍርሃት በሌለበት ምንም መልካም ነገር አይጠበቅም። ክፋት ኃጢአተኞችን ያሳድዳል። እግዚአብሔር የማይለወጥ ነው። በክፉ ሥራዎች ላይ የተፈረደው ፍርድ በፍጥነት ባይፈጸምም፣ ይፈጸማል፤ ጌታ ለኃጢአት እንደሁልጊዜው ሁሉ ጠላት ነው። ይህን ሁላችንም በራሳችን ላይ ተግባራዊ ማድረግ እንችላለን። የማይለወጥ አምላክ ስለምናገለግል፣ እንዲሁም ምሕረቱ አያልቅምና አንጠፋም።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV “See, I will send my messenger, who will prepare the way before me. Then suddenly the Lord you are seeking will come to… English BCV “እንሆ፥ መንገዲ ዝፀርግ ልኡኸይ ቀቅድመይ እልእኽ ኣለኹ። እቲ እትደልይዎ ጐይታ ኸዓ ናብ መቕደሱ ድንገት ክመፅእ እዩ፤ እቲ እትሕጐሱሉ መልእኽተኛ ቃል ኪዳን፥ እንሆ፥ ይመፅእ ኣሎ” ይብል … ትግርኛ GAZBIB Waaqayyo gooftaan maccaa,“Kunoo, ani ergamaa koo isa karaa anaaf qopheessu of dura nan erga; dingatas gooftichi inni is… Afaan Oromoo BCV GIZ ናሁ አነ እፌኑ መልእክየ ዘይጸይሕ ወይርኢ ፍኖትየ ቅድመ ገጽከ፡ ወይመጽእ ውስተ ጽርሑ ግብተ እግዚአብሔር ዘአንትሙ ተኀሥሡ መልአከ ሥርዓትየ ዘአንትሙ ትፈቅዱ፤ ናሁ ይመጽእ፡ ይቤ እግዚአብሔ… giz GAZGAZ Waaqayyo gooftaan maccaa,“Kunoo, ani ergamaa koo isa karaa anaaf qopheessu of dura nan erga; dingatas gooftichi inni is… Afaan Oromoo BCV aksum “እንሆ፥ መንገዲ ዝፀርግ ልኡኸይ ቀቅድመይ እልእኽ ኣለኹ። እቲ እትደልይዎ ጐይታ ኸዓ ናብ መቕደሱ ድንገት ክመፅእ እዩ፤ እቲ እትሕጐሱሉ መልእኽተኛ ቃል ኪዳን፥ እንሆ፥ ይመፅእ ኣሎ” ይብል … ትግርኛ AMHNIV “እነሆ፤ በፊቴ መንገድ እንዲያዘጋጅ መልእክተኛዬን እልካለሁ፤ የምትፈልጉት ጌታ በድንገት ወደ ቤተ መቅደሱ ይመጣል፤ ደስ የምትሰኙበትም የቃል ኪዳኑ መልእክተኛ ይመጣል” ይላል እግዚአብሔር ጸ… አማርኛ SWAHSUV Angalieni, namtuma mjumbe wangu, naye ataitengeneza njia mbele yangu; naye Bwana mnayemtafuta atalijilia hekalu lake gh… Kiswahili