የሉቃስ ወንጌል 12

AMHNIVአማርኛ59 ጥቅሶች9:23 አዳምጥ
አዳምጥ 9:23 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1በዚያን ጊዜ፣ በብዙ ሺህ የሚቈጠር ሕዝብ እርስ በርስ እስኪረጋገጥ ድረስ ተሰብስቦ ሳለ፣ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ ይል ጀመር፤ “ከፈሪሳውያን እርሾ ተጠንቀቁ፤ ይህም ግብዝነት ነው።

2የማይገለጥ የተሸፈነ፣ የማይታወቅ የተሰወረ ምንም የለም።

3ስለዚህ በጨለማ ያወራችሁት ሁሉ በብርሃን ይሰማል፤ በእልፍኝም ውስጥ በጆሮ ያንሾካሾካችሁት በሰገነት በይፋ ይነገራል።

4“ወዳጆቼ ሆይ፤ እላችኋለሁ ሥጋን የሚገድሉትን፣ ከዚያ ወዲያ ግን ምንም ማድረግ የማይችሉትን አትፍሩ።

5ነገር ግን መፍራት የሚገባችሁን አሳያችኋለሁ፤ ከገደለ በኋላ ወደ ገሃነም ለመጣል ሥልጣን ያለውን እርሱን ፍሩት፤ አዎን፤ እርሱን ፍሩት እላችኋለሁ።

6አምስት ድንቢጦች በዐሥር ሳንቲም ይሸጡ የለምን? ይሁን እንጂ ከእነርሱ አንዷ እንኳ በእግዚአብሔር ዘንድ አትዘነጋም።

7የእናንተ የራሳችሁ ጠጕር ሁሉ እንኳ የተቈጠረ ነው፤ እንግዲህ አትፍሩ፤ ከብዙ ድንቢጦች የበለጠ ዋጋ አላችሁ።

8“እላችኋለሁ፤ በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ የሰው ልጅ ደግሞ በእግዚአብሔር መላእክት ፊት ይመሰክርለታል።

9በሰው ፊት የሚክደኝም በእግዚአብሔር መላእክት ፊት ይካዳል።

10በሰው ልጅ ላይ የማቃለል ቃል የሚሰነዝር ሁሉ ይሰረይለታል፤ መንፈስ ቅዱስን የሚሳደብ ግን አይሰረይለትም።

11“ሰዎች ይዘው ወደ ምኵራብ፣ ወደ ገዥዎችና ወደ ባለ ሥልጣናት ባቀረቧችሁ ጊዜ፣ እንዴት ወይም ምን እንደምትመልሱ አትጨነቁ፤

12በዚያ ሰዓት መንፈስ ቅዱስ መናገር የሚገባችሁን ያስተምራችኋልና።”

13ከሕዝቡም መካከል አንድ ሰው፣ “መምህር ሆይ፤ ወንድሜ ውርስ እንዲያካፍለኝ ንገረው” አለው።

14ኢየሱስም፣ “አንተ ሰው፤ በእናንተ ላይ ፈራጅ ወይም ዳኛ ያደረገኝ ማነው?” አለው።

15ደግሞም፣ “የሰው ሕይወቱ በሀብቱ ብዛት የተመሠረተ ስላልሆነ፣ ተጠንቀቁ፤ ከስግብግብነትም ሁሉ ራሳችሁንም ጠብቁ” አላቸው።

16ቀጥሎም እንዲህ ሲል ምሳሌ ነገራቸው፤ “ዕርሻው እጅግ ፍሬያማ የሆነችለት አንድ ሀብታም ነበረ፤

17ይህም ሰው፣ ምርቴን የማከማችበት ስፍራ ስለሌለኝ ምን ላድርግ? ብሎ በልቡ አሰበ።

18“እንዲህም አለ፤ ‘እንደዚህ አደርጋለሁ፤ ያሉኝን ጐተራዎች አፈርስና ሌሎች ሰፋ ያሉ ጐተራዎች እሠራለሁ፤ በዚያም ምርቴንና ንብረቴንም ሁሉ አከማቻለሁ፤

19ነፍሴንም፣ “ነፍሴ ሆይ፤ ለብዙ ዘመን የሚበቃሽ ሀብት አከማችቼልሻለሁ፤ እንግዲህ ዕረፊ፤ ብዪ፤ ጠጪ፤ ደስም ይበልሽ” እላታለሁ።’

20“እግዚአብሔር ግን፣ ‘አንተ ሞኝ፤ ነፍስህን በዚህች ሌሊት ከአንተ ሊውስዱ ይፈልጓታል፤ እንግዲህ፣ ለራስህ ያከማቸኸው ለማን ይሆናል?’ አለው።

21“ስለዚህ ለራሱ ሀብት የሚያከማች፣ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ዘንድ ሀብታም ያልሆነ ሰው መጨረሻው ይኸው ነው።”

22ከዚያም ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አለ፤ “ስለዚህ እላችኋለሁ፣ ስለ ሕይወታችሁ ምን እንደምትበሉ፣ ወይም ስለ ሰውነታችሁ ምን እንደምትለብሱ አትጨነቁ፤

23ሕይወት ከምግብ፣ ሰውነትም ከልብስ ይበልጣልና።

24ቁራዎችን ተመልከቱ፤ አይዘሩም፤ አያጭዱም፤ ማከማቻ ወይም ጐተራ የላቸውም፤ እግዚአብሔር ግን ይመግባቸዋል። እናንተማ ከወፎች እጅግ ትበልጡ የለምን?

25ለመሆኑ፣ ከእናንተ ተጨንቆ በዕድሜው ላይ አንድ ሰዓት መጨመር የሚችል ማነው?

26እንግዲህ ቀላሉን ነገር እንኳ ማድረግ የማትችሉ ከሆነ፣ ስለ ሌላው ነገር ለምን ትጨነቃላችሁ?

27“እስቲ አበቦች እንዴት እንደሚያድጉ ተመልከቱ፤ አይለፉም፤ አይፈትሉም፤ ነገር ግን እላችኋለሁ፤ ሰሎሞን እንኳ በዚያ ሁሉ ክብሩ ከእነርሱ እንደ አንዷ አልለበሰም።

28እንግዲህ እግዚአብሔር ዛሬ ታይቶ ነገ ወደ እሳት የሚጣለውን የሜዳ ሣር እንዲህ የሚያለብስ ከሆነ፣ እናንተ እምነት የጐደላችሁ፣ እናንተንማ እንዴት አብልጦ አያለብሳችሁም?

29ስለዚህ ምን እንደምትበሉና ምን እንደምትጠጡ በመሻት ልባችሁ አይጨነቅ፤

30ይህንማ በዓለም ያለ ሕዝብ ሁሉ ይፈልጋል፤ አባታችሁ እኮ ይህ ሁሉ እንደሚያስፈልጋችሁ ያውቃል።

31ይልቁንስ የእግዚአብሔርን መንግሥት ፈልጉ፤ ይህም ሁሉ በተጨማሪ ይሰጣችኋል።

32“እናንተ አነስተኛ መንጋ የሆናችሁ መንግሥትን ሊሰጣችሁ የአባታችሁ መልካም ፈቃድ ነውና አትፍሩ፤

33ያላችሁን ሽጡና ለድኾች ስጡ፤ ሌባ በማይሰርቅበት፣ ብል በማይበላበት፣ በማያረጅ ከረጢት የማያልቅ ንብረት በሰማይ አከማቹ፤

34ልባችሁ፣ ንብረታችሁ ባለበት ቦታ ይሆናልና።

35“በአጭር ታጥቃችሁ ተዘጋጁ፤ መብራታችሁም የበራ ይሁን፤

36ጌታቸው ከሰርግ ግብዣ እስኪመለስ እንደሚጠባበቁና መጥቶም በር ሲያንኳኳ ወዲያው ለመክፈት ዝግጁ የሆኑ ሰዎችም ምሰሉ።

37ጌታቸው በሚመጣበት ጊዜ ነቅተው የሚያገኛቸው አገልጋዮች ብፁዓን ናቸው፤ እውነት እላችኋለሁ፤ ጌታቸውም በአጭር ይታጠቃል፤ በማእድ ያስቀምጣቸዋል፤ ቀርቦም ያስተናግዳቸዋል።

38ከሌሊቱ በሁለተኛውም ሆነ በሦስተኛው ክፍል መጥቶ እንደዚያው ነቅተው ቢያገኛቸው፣ እነዚያ አገልጋዮች ብፁዓን ናቸው።

39ይህን ግን ዕወቁ፤ ሌባ በምን ሰዓት እንደሚመጣ የቤቱ ባለቤት ቢያውቅ ኖሮ፣ ቤቱ ሲቈፈር ዝም ብሎ ባላየ ነበር።

40እናንተም ተዘጋጅታችሁ ጠብቁ፤ የሰው ልጅ ባላሰባችሁት ሰዓት ይመጣልና።”

41ጴጥሮስም፣ “ጌታ ሆይ፤ ይህን ምሳሌ የምትናገረው ለእኛ ብቻ ነው ወይስ ለሁሉም ጭምር ነው?” አለው።

42ጌታም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “እንግዲህ፣ ምግባቸውን በተገቢው ጊዜ እንዲሰጣቸው ጌታው በቤተ ሰዎቹ ላይ የሚሾመው ታማኝና ብልህ መጋቢ ማነው?

43ጌታው ሲመለስ እንዲህ ሲያደርግ የሚያገኘው አገልጋይ እርሱ ብፁዕ ነው።

44እውነት እላችኋለሁ፤ ባለው ንብረት ሁሉ ላይ ይሾመዋል።

45ዳሩ ግን ያ አገልጋይ፣ ጌታዬ ቶሎ አይመጣም፤ ይዘገያል፤ ብሎ ቢያስብና ወንድና ሴት አገልጋዮችን ቢደበድብ፣ ደግሞም እንዳሻው መብላት፣ መጠጣትና መስከር ቢጀምር፣

46የዚያ አገልጋይ ጌታ ባላሰበው ቀንና ባልጠረጠረው ሰዓት ይመጣበታል፤ ስለዚህ ይቈራርጠዋል፤ ዕድል ፈንታውንም ከማያምኑ ጋር ያደርጋል።

47“የጌታውን ፍላጎት እያወቀ የማይዘጋጅና ፈቃዱን የማያደርግ አገልጋይ እርሱ ክፉኛ ይገረፋል፤

48ነገር ግን ይህን ሳያውቅ ቀርቶ መገረፍ የሚገባውን ያህል ያደረገ አገልጋይ በጥቂቱ ይገረፋል። ብዙ ከተሰጠው ሁሉ ብዙ ይፈለግበታል፤ ብዙ ዐደራም ከተቀበለም ብዙ ይጠበቅበታል።

49“እኔ የመጣሁት በምድር ላይ እሳት ለመለኰስ ነው፤ አሁኑኑ ቢቀጣጠል ምንኛ ደስ ባለኝ!

50ነገር ግን የምጠመቀው ጥምቀት አለኝ፤ እስኪፈጸምም ድረስ እንዴት ተጨንቄአለሁ?

51በምድር ላይ ሰላምን ለማምጣት የመጣሁ ይመስላችኋል? አይደለም፤ እላችኋለሁ፤ እኔ የመጣሁት ለመለያየት ነው።

52ከአሁን ጀምሮ እርስ በርስ የተለያዩ በአንድ ቤተ ሰብ ውስጥ አምስት ሰዎች ይኖራሉ፤ ሁለቱ በሦስቱ ላይ፣ ሦስቱም በሁለቱ ላይ ተነሥተው ይለያያሉ፤

53አባት በወንድ ልጁ ላይ፣ ወንድ ልጅም በአባቱ ላይ፣ እናት በሴት ልጇ ላይ፣ ሴት ልጅም በእናቷ ላይ፣ አማት በምራቷ ላይ፣ ምራትም በአማቷ ላይ ተነሥተው ይለያያሉ።”

54ደግሞም ለሕዝቡ እንዲህ አለ፤ “ደመና በምዕራብ በኩል ሲወጣ ስታዩ ወዲያው፣ ዝናብ ሊመጣ ነው ትላላችሁ፤ እንደዚያም ይሆናል፤

55የደቡብ ነፋስም ከደቡብ በኩል ሲነፍስ፣ ቀኑ ሞቃት ይሆናል ትላላችሁ፤ እንደዚያም ይሆናል።

56እናንት ግብዞች፤ የምድሩንና የሰማዩን መልክ መመርመር ታውቁበታላችሁ፤ ታዲያ ይህን የአሁኑን ዘመን መመርመር እንዴት ተሳናችሁ?

57“ታዲያ ራሳችሁ ትክክለኛ የሆነውን ነገር ለምን አትፈርዱም?

58ከባላጋራህ ጋር ወደ ዳኛ ፊት ለመቅረብ ስትሄድ፣ ገና በመንገድ ላይ ሳለህ ለመታረቅ ጥረት አድርግ፤ አለበለዚያ ጐትቶ ወደ ዳኛው ይወስድሃል፤ ዳኛውም ለመኰንኑ አሳልፎ ይሰጥሃል፤ መኰንኑም ወደ ወህኒ ይጥልሃል፤

59እልሃለሁ፤ የመጨረሻዋን ሳንቲም እስክትከፍል ድረስ ከዚያ አትወጣም።

ማብራሪያ

12:1-12 የእግዚአብሔርን ሁሉን አቀፍ አቅርቦት ትምህርት እና ስፋቱን በጽኑ ማመን በአደጋ ውስጥ ስንሆን ያረጋጋናል፣ እንዲሁም ግዴታችንን በመወጣት መንገድ እግዚአብሔርን እንድንታመን ያበረታታናል። አቅርቦቱ እጅግ አነስተኛ የሆኑ ፍጥረታትን፣ የድንቢጦችንም ጭምር፣ ያስተውላል፤ ስለዚህም የክርስቶስ ደቀ መዛሙርትን ጥቃቅን ጉዳዮችም ያውቃል። አሁን ክርስቶስን የሚመሰክሩ በታላቁ ቀን፣ በእግዚአብሔር መላእክት ፊት፣ በእርሱ ዘንድ የእርሱ እንደሆኑ ይታወቃሉ። ክርስቶስን ከመካድና የእርሱን እውነቶችና መንገዶች ከመተው እንድንቆጠብ፣ ክርስቶስን የሚክዱ ሰዎች፣ በዚህ የራሳቸውን ሕይወት ቢያድኑም፣ ወይም በእርሱ መንግሥት ቢያገኙም እንኳ፣ በመጨረሻ ትልቅ ከሳሪዎች እንደሚሆኑ እዚህ ላይ ተረጋግጦልናል። ክርስቶስ አያውቃቸውምና፣ የራሱም ናቸው አይልምና፣ ሞገስም አያሳያቸውምና። ነገር ግን የሚንቀጠቀጥ፣ ንስሐ የገባ፣ ከመንገዱ ያፈነገጠ አማኝ ይቅርታ ስለማግኘቱ ሊጠራጠር አይገባም። ይህ ግን ከመንፈስ ቅዱስ ላይ ስድብ ከሆነው፣ ፈጽሞ ይቅርታ ከማይገኝለትና ፈጽሞ ንስሐ ከማይገባበት፣ በጽኑ ከተወሰነው ጥላቻ በእጅጉ የተለየ ነው።

12:13-21

የክርስቶስ መንግሥት መንፈሳዊ ነው እንጂ የዚህ ዓለም አይደለም። ክርስትና ከፖለቲካ ጋር አይገባም፤ ሁሉንም በጽድቅ እንዲያደርጉ ያስገድዳል፣ ነገር ግን ዓለማዊ ሥልጣን በጸጋ ላይ የተመሠረተ አይደለም። ሃይማኖትን በመጠቀም ዓለማዊ ጥቅም እንድናገኝ አያበረታታም። የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ሽልማቶች የተለየ ባሕርይ አላቸው። ስግብግብነት ያለማቋረጥ ልንጠነቀቅበት የሚገባ ኃጢአት ነው፤ ምክንያቱም ደስታና ምቾት በዚህ ዓለም ሀብት ላይ የተመካ አይደለምና። የዚህ ዓለም ነገሮች የነፍስን ፍላጎት አያረኩም።

እነሆ ምሳሌ! ይህ ምሳሌ ሥጋውያን ዓለማውያን በሕይወት እያሉ ያላቸውን ሞኝነት፣ ሲሞቱም የሚደርስባቸውን መከራ ያሳያል። የተሳለው ባሕርይ በትክክል ጥንቁቅ መስሎ የሚታይ፣ ዓለማዊ ሰው ነው፤ እርሱም ለእግዚአብሔር አስተዳደር ምስጋና የለውም፣ የሰው ልጆች ጉዳዮች እርግጠኝነት የጎደላቸው መሆናቸውን፣ የነፍሱን ዋጋ ወይም የዘላለምን አስፈላጊነት በትክክል አያስብም። ምን ያህል ሰዎች፣ የክርስቲያን ነን ከሚሉት መካከልም እንኳ፣ እንደነዚህ ያሉ ባሕርያትን ለመኮረጅ እንደ ሞዴል፣ ግንኙነት ለመመሥረትም እንደ ተገቢ ሰው ያመለክታሉ! ሐሳቦች የተደበቁ ናቸው፣ ሐሳቦችም ነፃ ናቸው ብለን ካሰብን ተሳስተናል። በእርሻው ላይ ብዙ ምርት ሲያይ፣ ለእግዚአብሔር ከማመስገን ወይም ብዙ በጎ ነገር ማድረግ ስለሚችል ከመደሰት ይልቅ፣ ራሱን አጨነቀ።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG በዚያን ጊዜ የሕዝብ አእላፍ እርስ በርሳቸው እስኪረጋገጡ ድረስ ተሰብስበው ሳሉ፥ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ ይል ጀመር፦ “አስቀድማችሁ ከፈሪሳውያን እርሾ ተጠበቁ፥ እርሱም ግብዝነት ነው። አማርኛ ENGNIV Meanwhile, when a crowd of many thousands had gathered, so that they were trampling on one another, Jesus began to spea… English BCV ኣእላፋት ህዝቢ፥ ንስንሳቶም ክሳዕ ዝፀቓቐጡ ናብኡ ምስ ተኣከቡ፥ ኢየሱስ ንደቀ መዛሙርቱ ኸምዙይ ክብሎም ጀመረ፦ “ካብ ማይ ብሒቝ ፈሪሳውያን፥ ንሱውን ካብ ግብዝና፥ ርእስኹም ሓልዉ። ትግርኛ GAZBIB Namoonni hamma wal irra ejjetanitti kumaatama baay'ee ta'anii, yeroo walitti qabamanitti, Yesus duraan dursee bartoota … Afaan Oromoo BCV GIZ ወተጋብኡ ኀቤሁ አእላፍ ሰብእ እስከ ይትካየዱ በበይናቲሆሙ ወአኀዘ ይበሎሙ ለአርዳኢሁ፦ “ቅድመ ተዐቀቡ እምነብሑኦሙ ለፈሪሳውያን ዘውእቱ አድልዎ። giz GAZGAZ Namoonni hamma wal irra ejjetanitti kumaatama baay'ee ta'anii, yeroo walitti qabamanitti, Yesus duraan dursee bartoota … Afaan Oromoo BCV aksum ኣእላፋት ህዝቢ፥ ንስንሳቶም ክሳዕ ዝፀቓቐጡ ናብኡ ምስ ተኣከቡ፥ ኢየሱስ ንደቀ መዛሙርቱ ኸምዙይ ክብሎም ጀመረ፦ “ካብ ማይ ብሒቝ ፈሪሳውያን፥ ንሱውን ካብ ግብዝና፥ ርእስኹም ሓልዉ። ትግርኛ SWAHSUV Wakati huo, makutano walipokutanika elfu elfu, hata wakakanyagana, alianza kuwaambia wanafunzi wake kwanza, Jilindeni n… Kiswahili