ሰቆቃው ኤርምያስ 4

AMHNIVአማርኛ22 ጥቅሶች4:31 አዳምጥ
አዳምጥ 4:31 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ወርቁ እንዴት ደበሰ! ንጹሑስ ወርቅ እንዴት ተለወጠ! የከበሩ ድንጋዮች፣ በየመንገዱ ዳር ተበታትነዋል።

2እንደ ወርቅ ይቈጠሩ የነበሩ፣ የከበሩ የጽዮን ወንዶች ልጆች፣ የሸክላ ሠሪ እጅ እንደ ሠራው፣ እንዴት አሁን እንደ ሸክላ ዕቃ ሆኑ!

3ቀበሮዎች እንኳን ግልገሎቻቸውን ለማጥባት፣ ጡታቸውን ይሰጣሉ፤ ሕዝቤ ግን በምድረ በዳ እንዳሉ ሰጎኖች፣ ጨካኞች ሆኑ።

4ከውሃ ጥም የተነሣ፣ የሕፃናት ምላስ ከላንቃቸው ጋር ተጣበቀ፤ ልጆቹ ምግብ ለመኑ፤ ነገር ግን ማንም አልሰጣቸውም።

5ምርጥ ምግብ ይበሉ የነበሩ፣ ተቸግረው በየመንገዱ ላይ ተንከራተቱ፤ ሐምራዊ ግምጃ ለብሰው ያደጉ፣ አሁን በዐመድ ክምር ላይ ተኙ።

6በሕዝቤ ላይ የደረሰው ቅጣት፣ የማንም እጅ ሳይረዳት፣ በድንገት ከተገለበጠችው፣ ሰዶም ላይ ከደረሰው ቅጣት ይልቅ ታላቅ ነው።

7መሳፍንቶቻቸው ከበረዶ ይልቅ ብሩህ፣ ከወተትም ይልቅ ነጭ ነበሩ፤ ሰውነታቸው ከቀይ ዕንቍ የቀላ፣ መልካቸውም እንደ ሰንፔር ነበር።

8አሁን ግን ከጥላሸት ይልቅ ጠቍረዋል፤ በመንገድም የሚያውቃቸው የለም፤ ቆዳቸው ከዐጥንታቸው ጋር ተጣብቆአል፤ እንደ ዕንጨትም ደርቀዋል።

9በራብ ከሚሞቱት ይልቅ፣ በሰይፍ የተገደሉት ይሻላሉ፤ ምግብ በሜዳ ላይ ካለማግኘታቸው የተነሣ፣ በራብ ደርቀው ያልቃሉ።

10ሕዝቤ ባለቀበት ጊዜ፣ ምግብ እንዲሆኑአቸው፣ ርኅሩኆቹ ሴቶች በገዛ እጆቻቸው፣ ልጆቻቸውን ቀቀሉ።

11እግዚአብሔር ለመቅሠፍቱ መውጫ በር ከፈተ፤ ጽኑ ቍጣውን አፈሰሰ፤ መሠረትዋን እንዲበላ፣ በጽዮን እሳት ለኰሰ።

12ጠላቶችም ሆኑ ወራሪዎች፣ የኢየሩሳሌምን በሮች ጥሰው ይገባሉ ብለው፣ የምድር ነገሥታት፣ ወይም ከዓለም ሕዝብ አንዳቸውም አላመኑም።

13ይህ ግን ከነቢያት ኀጢአት፣ ከካህናቷም መተላለፍ የተነሣ ሆኖአል፤ በውስጧ፣ የጻድቃንን ደም አፍስሰዋልና።

14እንደ ታወሩ ሰዎች፣ በየመንገዱ ላይ ይደናበራሉ፤ ማንም ሰው ደፍሮ ልብሳቸውን መንካት እስከማይችል ድረስ፣ በደም እጅግ ረክሰዋል።

15ሰዎች “ሂዱ! እናንት ርኵሳን!” ብለው ይጮኹባቸዋል፤ “ወግዱ! ወግዱ! አትንኩ!” ይሏቸዋል፤ ሸሽተው በሚቅበዘበዙበትም ጊዜ፣ በአሕዛብ መካከል ያሉ ሰዎች፣ “ከእንግዲህ በዚህ መቀመጥ አይገባቸውም!” ይላሉ።

16እግዚአብሔር ራሱ በትኖአቸዋል፤ ከእንግዲህ ወዲያ አይጠብቃቸውም፤ ካህናቱ አልተከበሩም፤ ሽማግሌዎቹም ከበሬታ አላገኙም።

17ከሁሉም በላይ በከንቱ ርዳታን ስንጠባበቅ፣ ዐይኖቻችን ደከሙ፤ ከግንብ ማማችን ላይ ሆነን፣ ሊያድን ከማይችል ሕዝብ ርዳታ ጠበቅን።

18ሰዎች እግር እግራችንን ተከታተሉን፤ ስለዚህ በመንገዳችን መሄድ አልቻልንም፤ መጨረሻችን ቀርቦአል፤ ቀኖቻችንም ተቈጥረዋል፤ ፍጻሜያችን መጥቶአልና።

19ከሰማይ ንስሮች ይልቅ፣ ጠላቶቻችን ፈጣኖች ናቸው፤ በተራሮች ላይ አሳደዱን፤ በምድረ በዳም ሸመቁብን።

20በእግዚአብሔር የተቀባው፣ የሕይወታችን እስትንፋስ፣ በወጥመዳቸው ተያዘ፤ በጥላው ሥር፣ በአሕዛብ መካከል እንኖራለን ብለን አስበን ነበር።

21አንቺ በዖፅ ምድር የምትኖሪ፣ የኤዶምያስ ሴት ልጅ ሆይ፤ ደስ ይበልሽ፤ ሐሴትም አድርጊ ነገር ግን ለአንቺም ደግሞ ጽዋው ይደርስሻል፤ ትሰክሪያለሽ፤ ዕርቃንሽንም ትጋለጫለሽ።

22የጽዮን ልጅ ሆይ፤ ቅጣትሽ ያበቃል፤ እርሱም የስደትሽን ዘመን አያራዝምም፤ ነገር ግን አንቺ የኤዶምያስ ልጅ ሆይ፤ ኀጢአትሽን ይቀጣል፤ ክፋትሽንም ይፋ ያወጣል።

ማብራሪያ

4:1-12 እንዴት ያለ ለውጥ ነው እዚህ ያለው! ኃጢአት የላቀውን ኃይልና እጅግ ምርጥ የሆኑ ስጦታዎችን ውበት ያደበዝዛል፤ ነገር ግን በክርስቶስ የሚሰጠን፣ በእሳት የተፈተነ ወርቅ ከእኛ ፈጽሞ አይወሰድም፤ ውጫዊ መልኩ ቢደበዝዝም፣ እውነተኛ ዋጋው ግን ፈጽሞ ሊለወጥ አይችልም። የኢየሩሳሌም የመከበብና የመጥፋት አስፈሪነት እንደገና ተገልጿል። በጥንቷ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የኃጢአትን አሳዛኝ ውጤቶች በመመልከት፣ ተመሳሳይ ምክንያቶች አሁን ያለውን ቤተ ክርስቲያንን ወደ ምን እንደሚያወርዷት በቁም ነገር እናስብ። ነገር ግን ጌታ ሆይ፣ በዓመፅ ከአንተ ብንርቅም፣ ወደ እኛ ተመለስ፣ ልባችንንም ወደ አንተ መልስ፣ ስምህንም እንድንፈራ።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6