ትንቢተ ኢዮኤል 2

AMHNIVአማርኛ32 ጥቅሶች7:55 አዳምጥ
አዳምጥ 7:55 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1በጽዮን መለከትን ንፉ፤ በቅዱሱ ተራራዬም የማስጠንቀቂያውን ድምፅ አሰሙ፤ በምድሪቱ የሚኖሩ ሁሉ ይንቀጥቀጡ፤ የእግዚአብሔር ቀን ቀርቦአልና፤ እርሱም በደጅ ነው።

2ይህም የጨለማና የጭጋግ ቀን፣ የደመናና የድቅድቅ ጨለማ ቀን ነው። የንጋት ብርሃን በተራሮች ላይ እንደሚወጣ፣ ኀያልና ብዙ ሰራዊት ይመጣል፤ ከጥንት እንዲህ ዐይነት ከቶ አልነበረም፤ በሚመጡትም ዘመናት እንዲህ ዐይነት ከቶ አይሆንም።

3በፊታቸው፣ እሳት ይባላል፤ በኋላቸውም ነበልባል ይለበልባል፤ በፊታቸው ምድሪቱ እንደ ዔድን ገነት ናት፤ በኋላቸውም የሚቀረው ባዶ ምድረ በዳ ነው፤ ምንም አያመልጣቸውም።

4መልካቸው እንደ ፈረስ መልክ ነው፤ እንደ ጦር ፈረስም ይጋልባሉ።

5ገለባ እንደሚበላ እንደሚንጣጣ እሳት፣ ለጦርነት እንደ ተዘጋጀ ኀያል ሰራዊት፣ የሠረገሎችን ድምፅ የሚመስል ድምፅ እያሰሙ፣ በተራሮች ጫፍ ላይ ይዘላሉ።

6በእነርሱ ፊት ሕዝቦች ይርዳሉ፤ የሁሉም ፊት ይገረጣል።

7እንደ ተዋጊዎች ድንገት አደጋ ይጥላሉ፤ እንደ ወታደሮችም ቅጥርን ይዘላሉ፤ ከመንገዳቸውም ሳይወጡ፣ አቅጣጫ ይዘው ይጓዛሉ።

8እርስ በርሳቸው አይገፋፉም፤ እያንዳንዱ መስመሩን ጠብቆ ይሄዳል፤ መስመራቸውን ሳይለቁ፣ መከላከያውን ሰብረው ያልፋሉ።

9ከተማዪቱን ይወራሉ፤ በቅጥሩም ላይ ይዘላሉ፤ በቤቶች ላይ ዘለው ይወጣሉ፤ እንደ ሌባም በመስኮት ይገባሉ።

10ምድር በፊታቸው ትንቀጠቀጣለች፤ ሰማይም ይናወጣል፤ ፀሓይና ጨረቃ ይጨልማሉ፤ ከዋክብትም ከእንግዲህ ወዲያ አያበሩም።

11በሰራዊቱ ፊት፣ እግዚአብሔር ያንጐደጒዳል፤ የሰራዊቱ ብዛት ስፍር ቊጥር የለውም፤ ትእዛዙንም የሚያደርግ እርሱ ኀያል ነው፤ የእግዚአብሔር ቀን ታላቅ፣ እጅግም የሚያስፈራ ነው፤ ማንስ ሊቋቋመው ይችላል?

12“አሁንም ቢሆን፣ በጾም፣ በልቅሶና በሐዘን፣ በፍጹም ልባችሁ ወደ እኔ ተመለሱ” ይላል እግዚአብሔር።

13ልባችሁን እንጂ፣ ልብሳችሁን አትቅደዱ፤ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ተመለሱ፤ እርሱ መሓሪና ርኅሩኅ፣ ቊጣው የዘገየና ፍቅሩ የበዛ፣ ክፉ ነገር ከማምጣትም የሚታገሥ ነውና።

14በምሕረቱ ተመልሶ፣ ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር የሚሆነውን፣ የእህል ቊርባንና የመጠጥ ቊርባን እንዲተርፋችሁ፣ በረከቱን ይሰጣችሁ እንደሆነ ማን ያውቃል?

15በጽዮን መለከትን ንፉ፤ ቅዱስ ጾምን ዐውጁ፤ የተቀደሰን ጉባኤ ጥሩ።

16ሕዝቡን ሰብስቡ፤ ጉባኤውን ቀድሱ፤ ሽማግሌዎችን በአንድነት አቅርቡ፤ ሕፃናትን ሰብስቡ፤ ጡት የሚጠቡትንም አታስቀሩ፤ ሙሽራው እልፍኙን ይተው፣ ሙሽሪትም የጫጒላ ቤቷን ትተው።

17በእግዚአብሔር ፊት የሚያገለግሉ ካህናት፣ በመሠዊያውና በቤተ መቅደሱ አደባባይ መካከል ሆነው ያልቅሱ፤ እንዲህም ይበሉ፤ “እግዚአብሔር ሆይ፤ ሕዝብህን አድን፤ ርስትህን በአሕዛብ መካከል መተረቻ፣ መሣቂያና መሣለቂያም አታድርግ፤ ለምንስ በሕዝቦች መካከል፣ ‘አምላካቸው ወዴት ነው?’ ይበሉን።”

18እነሆ፤ እግዚአብሔር ስለ ምድሩ ይቀናል፤ ስለ ሕዝቡም ይራራል።

19እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል ይመልስላቸዋል፤ “እህል፣ አዲስ የወይን ጠጅና ዘይት፣ እስክትጠግቡ ድረስ እሰጣችኋለሁ፤ የሕዝቦች መዘባበቻ አላደርጋችሁም።

20“የሰሜንን ሰራዊት ከእናንተ አርቃለሁ፤ ፊቱን ወደ ምሥራቁ ባሕር፣ ጀርባውንም ወደ ምዕራቡ ባሕር በማድረግ፣ ወደ ደረቀውና ወደ ባድማው ምድር እገፋዋለሁ፤ ግማቱ ይወጣል፤ ክርፋቱም ይነሣል።” በእርግጥ እርሱ ታላቅ ነገር አድርጎአል።

21ምድር ሆይ፤ አትፍሪ፤ ደስ ይበልሽ፤ ሐሤትም አድርጊ፤ በእርግጥ እግዚአብሔር ታላቅ ነገር አድርጎአል።

22የዱር እንስሳት ሆይ፤ አትፍሩ፤ መሰማሪያ መስኮቹ ለምልመዋልና፤ ዛፎቹ ፍሬያቸውን አፍርተዋል፤ የበለሱ ዛፍና የወይኑ ተክልም እጅግ አፍርተዋል።

23የጽዮን ሰዎች ሆይ፤ ደስ ይበላችሁ፤ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር፣ ሐሤት አድርጉ፤ የበልግን ዝናብ፣ በጽድቅ ሰጥቶአችኋልና፤ እንደ ቀድሞውም፣ የበልግንና የጸደይን ዝናብ በብዛት ልኮላችኋል።

24ዐውድማዎቹ በእህል ይሞላሉ፤ መጥመቂያ ጒድጓዶችም፣ በአዲስ የወይን ጠጅና በዘይት ተሞልተው ያፈሳሉ።

25“በመካከላችሁ የሰደድሁት ታላቁ ሰራዊት፣ ትልልቁ አንበጣና ትንንሹ አንበጣ፣ ሌሎች አንበጦችና የአንበጣው መንጋ የበላውን፣ እነዚህ ሁሉ የበሏቸውን ዓመታት ዋጋ እመልስላችኋለሁ።

26እስክትጠግቡ የምትበሉት ብዙ ምግብ ይኖራችኋል፤ ድንቅ ነገሮችን ለእናንተ የሠራውን፣ የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ስም ታመሰግናላችሁ፤ ሕዝቤም ከእንግዲህ ወዲያ አያፍርም።

27ከዚያም እኔ በእስራኤል መካከል እንዳለሁ፣ እኔ አምላካችሁ እግዚአብሔር እንደሆንሁ፣ እንደ እኔም ያለ፣ ሌላ እንደሌለ ታውቃላችሁ፤ ሕዝቤም ከእንግዲህ ወዲያ አያፍርም።

28“ከዚህም በኋላ፣ መንፈሴን በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ አፈሳለሁ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁ ትንቢት ይናገራሉ፤ ሽማግሌዎቻችሁ ሕልም ያልማሉ፤ ጒልማሶቻችሁም ራእይ ያያሉ።

29በእነዚያ ቀናት በወንዶችና በሴቶች ባሪያዎች ላይ እንኳ፣ መንፈሴን አፈሳለሁ።

30ድንቆችን በሰማያት፣ እንዲሁም በምድር፣ ደምና እሳት፣ የጢስም ዐምድ አሳያለሁ።

31ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ከመምጣቱ በፊት፣ ፀሓይ ትጨልማለች፤ ጨረቃም ወደ ደም ትለወጣለች።

32የእግዚአብሔርን ስም የሚጠራ ሁሉ፣ እርሱ ይድናል፤ እግዚአብሔርም እንዳለው፣ በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም፣ መድኀኒት ይገኛል፤ ከትሩፋኑም መካከል እግዚአብሔር የጠራቸው በዚያ ይገኛሉ።

ማብራሪያ

፪፥፩-፲፬ ካህናቱ የመለኮታዊ ፍርዶች መቃረብን አስመልክቶ ሕዝቡን ማስጠንቀቅ ነበረባቸው። የኃጢአት አስከፊ መዘዞችን ማስጠንቀቅ እና በሰዎች ዐመፀኝነትና ክፋት ላይ ከሰማይ የሚመጣውን ቁጣ መግለጥ የአገልጋዮች ሥራ ነው። የሚከተለው አስደናቂ መግለጫ የአንበጣዎችን ውድመት ተከትሎ የሚመጣውን የሚያሳይ ሲሆን፣ ከለዳውያን ምድሪቱን በማጥፋት የሚያስከትሉትንም ውጤት ሊገልጽ ይችላል። ለበደለኛ አሕዛብ ጊዜያዊ ፍርዶች ማስጠንቀቂያ ከተሰጠ፣ ኃጢአተኞችማ ከሚመጣው ቁጣ መዳንን እንዲሹ እንዴት አብልጠው ሊያስጠነቅቁ ይገባል! ስለዚህ በምድር ላይ ያለን ዋና ተግባራችን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ድርሻችንን ማስጠበቅ ሲሆን፣ አሁን ጣዖት ከሚያደርጓቸው ሁሉ በቅርቡ የሚነጠቁትን ነገሮች ከመውደድም መራቅን መፈለግ አለብን። የኀዘንና የኀፍረት የውጪ መግለጫዎች፣ ጾም፣ ለቅሶና ማልቀስ ሊኖሩ ይገባል፤ ለመከራ የሚፈሱ እንባዎች ለመከራው መንስኤ በሆነው ኃጢአት በሚፈሱ እንባዎች መለወጥ አለባቸው።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG የእግዚአብሔር ቀን መጥቶአልና፥ እርሱም ቀርቦአልና በጽዮን መለከትን ንፉ፥ በቅዱሱም ተራራዬ ላይ እሪ በሉ፤ በምድርም የሚኖሩ ሁሉ ይንቀጥቀጡ፤ የእግዚአብሔር ቀን መጥቶአልና፤ አማርኛ ENGNIV Blow the trumpet in Zion; sound the alarm on my holy hill. Let all who live in the land tremble, for the day of the Lor… English BCV መዓልቲ እግዚኣብሄር ትመፅእ ኣላ፤ ቀሪባ ኸዓ እያ እሞ፥ ኣብ ፅዮን መለኸት ንፍሑ፤ ኣብቲ ቅዱስ እምባይ ድማ ኣእውዩ፤ መዓልቲ እግዚኣብሄር መፂኣ እያሞ፥ ኣብ ምድሪ ዝነብሩ ዘለዉ ዅላቶም የ… ትግርኛ GAZBIB Xiyoon gaara koo isa qulqulluu irratti fiinoo afuufaa, sagalee nama dammaqsu dhageessisaa! Guyyaan Waaqayyoo waan dhufu… Afaan Oromoo BCV GIZ ንፍሑ ቀርነ በጽዮን ወስብኩ በደብረ መቅደስየ ወይደነግፁ ኵሎሙ እለ ይነብሩ ውስተ ምድር እስመ አልጸቀት ዕለተ እግዚአብሔር ወበጽሐት። giz GAZGAZ Xiyoon gaara koo isa qulqulluu irratti fiinoo afuufaa, sagalee nama dammaqsu dhageessisaa! Guyyaan Waaqayyoo waan dhufu… Afaan Oromoo BCV aksum መዓልቲ እግዚኣብሄር ትመፅእ ኣላ፤ ቀሪባ ኸዓ እያ እሞ፥ ኣብ ፅዮን መለኸት ንፍሑ፤ ኣብቲ ቅዱስ እምባይ ድማ ኣእውዩ፤ መዓልቲ እግዚኣብሄር መፂኣ እያሞ፥ ኣብ ምድሪ ዝነብሩ ዘለዉ ዅላቶም የ… ትግርኛ SWAHSUV Pigeni tarumbeta katika Sayuni, Pigeni na kelele katika mlima wangu mtakatifu; Wenyeji wote wa nchi na watetemeke; Kwa … Kiswahili