ትንቢተ ኢዮኤል 2

AMHEVGአማርኛ32 ጥቅሶች5:53 አዳምጥ
አዳምጥ 5:53 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1የእግዚአብሔር ቀን መጥቶአልና፥ እርሱም ቀርቦአልና በጽዮን መለከትን ንፉ፥ በቅዱሱም ተራራዬ ላይ እሪ በሉ፤ በምድርም የሚኖሩ ሁሉ ይንቀጥቀጡ፤ የእግዚአብሔር ቀን መጥቶአልና፤

2የጨለማና የጭጋግ ቀን፥ የደመናና የድቅድቅ ጨለማ ቀን ነው፤ ታላቅና ብርቱ ሕዝብ በተራሮች ላይ እንደ ወገግታ ተዘርግቶአል፤ ከዘላለምም ጀምሮ እንደ እነርሱ ያለ አልነበረም፥ ከእነርሱም በኋላ እስከ ብዙ ትውልድ ድረስ እንደ እነርሱ ያለ ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም።

3እሳት በፊታቸው ትባላለች፥ በኋላቸውም ነበልባል ታቃጥላለች፤ ምድሪቱ በፊታቸው እንደ ዔድን ገነት፥ በኋላቸውም የምድረ በዳ በረሃ ናት፤ ከእነርሱም የሚያመልጥ የለም።

4መልካቸው እንደ ፈረስ መልክ ነው፥ እንደ ፈረሶችም ይሮጣሉ።

5በተራራ ላይ እንዳሉ ሰረገሎች ድምፅ፥ ገለባውንም እንደሚበላ እንደ እሳት ነበልባል ድምፅ፥ ለሰልፍም እንደ ተዘጋጀ እንደ ብርቱ ሕዝብ ያኰበኵባሉ።

6ከፊታቸው አሕዛብ ይንቀጠቀጣሉ፤ የሰውም ፊት ሁሉ ይጠቍራል።

7እንደ ኃያላን ይሮጣሉ፥ እንደ ሰልፈኞችም በቅጥሩ ላይ ይወጣሉ፤ እያንዳንዱም በመንገዱ ላይ ይራመዳል፥ ከእርምጃቸውም አያፈገፍጉም።

8አንዱ ካንዱ ጋር አይጋፉም፥ እያንዳንዱም መንገዱን ይጠበጥባል፤ በሰልፍ መካከል ያልፋሉ፥ እነርሱም አይቈስሉም።

9በከተማም ያኰበኵባሉ፥ በቅጥሩም ላይ ይሮጣሉ፤ ወደ ቤቶችም ይወጣሉ፥ እንደ ሌባም በመስኮቶች ይገባሉ።

10ምድሪቱም ከፊታቸው ትናወጣለች፥ ሰማያትም ይንቀጠቀጣሉ፤ ፀሐይና ጨረቃም ይጨልማሉ፥ ከዋክብትም ብርሃናቸውን ይሰውራሉ።

11እግዚአብሔርም በሠራዊቱ ፊት ድምፁን ይሰጣል፤ ሰፈሩ እጅግ ብዙ ነውና፥ ቃሉንም የሚያደርግ እርሱ ኃያል ነውና፤ የእግዚአብሔርም ቀን ታላቅና እጅግ የሚያስፈራ ነውና ማንስ ይችለዋል?

12አሁንስ፥ ይላል እግዚአብሔር፦ በፍጹም ልባችሁ፥ በጾምም፥ በልቅሶና በዋይታ ወደ እኔ ተመለሱ።

13ልባችሁን እንጂ ልብሳችሁን አትቅደዱ፤ አምላካችሁም እግዚአብሔር ቸርና መሐሪ፥ ቍጣው የዘገየ፥ ምሕረቱም የበዛ፥ ለክፋትም የተጸጸተ ነውና ወደ እርሱ ተመለሱ።

14የሚመለስና የሚጸጸት እንደ ሆነ፥ ለአምላካችሁም ለእግዚአብሔር የእህልና የመጠጥ ቍርባን የሚሆነውን በረከት የሚያተርፍ እንደ ሆነ ማን ያውቃል?

15በጽዮን መለከትን ንፉ፥ ጾምንም ቀድሱ፥ ጉባኤውንም አውጁ፥

16ሕዝቡንም አከማቹ፥ ማኅበሩንም ቀድሱ፥ ሽማግሌዎቹንም ሰብስቡ፥ ሕፃናቱንና ጡት የሚጠቡትን አከማቹ፤ ሙሽራው ከእልፍኙ፥ ሙሽራይቱም ከጫጉላዋ ይውጡ።

17የእግዚአብሔርም አገልጋዬች ካህናት ከወለሉና ከመሠዊያው መካከል እያለቀሱ፦ “አቤቱ፥ ለሕዝብህ ራራ፥ አሕዛብም እንዳይነቅፉአቸው ርስትህን ለማላገጫ አሳልፈህ አትስጥ፤ ከአሕዛብ መካከል፦ ‘አምላካቸው ወዴት ነው?’ ስለ ምን ይላሉ?” ይበሉ።

18እግዚአብሔርም ስለ ምድሩ ቀና፥ ለሕዝቡም ራራለት።

19እግዚአብሔርም መልሶ ሕዝቡን፦ “እነሆ፥ እህልንና ወይንን ዘይትንም እሰድድላችኋለሁ፥ እናንተም በእርሱ ትጠግባላችሁ፤ ከእንግዲህም ወዲያ በአሕዛብ መካከል መሰደቢያ አላደርጋችሁም።

20የሰሜንንም ሠራዊት ከእናንተ ዘንድ አርቃለሁ፥ ወደ በረሃና ወደ ምድረበዳ፥ ፊቱን ወደ ምሥራቁ ባሕር ጀርባውንም ወደ ምዕራቡ ባሕር አድርጌ አሳድደዋለሁ፤ እርሱም ትዕቢትን አድርጎአልና ግማቱ ይወጣል፥ ክርፋቱም ይነሣል፡” አለ።

21ምድር ሆይ፥ እግዚአብሔር ታላቅ ነገር አድርጎአልና አትፍሪ፥ ደስም ይበልሽ፥ እልልም በዪ።

22እናንተ የምድር እንስሶች ሆይ፥ የምድር በዳው ማሰማርያ ለምልሞአልና፥ ዛፉም ፍሬውን አፍርቶአልና፥ በለሱና ወይኑም ኃይላቸውን ሰጥተዋልና አትፍሩ።

23እናንተ የጽዮን ልጆች፥ አምላካችሁ እግዚአብሔር የፊተኛውን ዝናብ በጽድቅ ሰጥቶአችኋልና፥ እንደ ቀድሞውም የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ አዝንቦላችኋልና በእርሱ ደስ ይበላችሁ፥ ለእርሱም እልል በሉ።

24አውድማዎችም እህልን ይሞላሉ፥ መጥመቂያዎችም የወይን ጠጅንና ዘይትን አትረፍርፈው ያፈስሳሉ።

25የሰደድሁባችሁ ታላቁ ሠራዊቴ አንበጣና ደጎብያ ኩብኩባና ተምች የበላቸውን ዓመታት እመልስላችኋለሁ።

26ብዙ መብል ትበላላችሁ፥ ትጠግቡማላችሁ፤ ከእናንተም ጋር ተአምራትን የሠራውን የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ስም ታመሰግናላችሁ፤ ሕዝቤም ለዘላለም አያፍርም።

27እኔም በእስራኤል መካከል እንዳለሁ፥ እኔም አምላካችሁ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ፥ ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ ታውቃላችሁ፤ ሕዝቤም ለዘላለም አያፍርም።

28ከዚህም በኋላ እንዲህ ይሆናል፤ መንፈሴን በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ አፈስሳለሁ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁም ትንቢት ይናገራሉ፥ ሽማግሌዎቻችሁም ሕልምን ያልማሉ፥ ጐበዞቻችሁም ራእይ ያያሉ፤

29ደግሞም በዚያ ወራት በወንዶችና በሴቶች ባሪያዎች ላይ መንፈሴን አፈስሳለሁ፤

30በላይ በሰማይ ድንቆችን አሳያለሁ፥ በታች በምድርም ደምና እሳት የጢስም ጭጋግ።

31ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ሳይመጣ ፀሐይ ወደ ጨለማ፥ ጨረቃም ወደ ደም ይለወጣል።

32እንዲህም ይሆናል፤ የእግዚአብሔርን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል፤ እግዚአብሔርም እንደ ተናገረ፥ በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም መድኃኒት ይገኛል። ደግሞም እግዚአብሔር የጠራቸው፥ የምስራች የሚሰበክላቸው ይገኛሉ።

ማብራሪያ

፪፥፩-፲፬ ካህናቱ የመለኮታዊ ፍርዶች መቃረብን አስመልክቶ ሕዝቡን ማስጠንቀቅ ነበረባቸው። የኃጢአት አስከፊ መዘዞችን ማስጠንቀቅ እና በሰዎች ዐመፀኝነትና ክፋት ላይ ከሰማይ የሚመጣውን ቁጣ መግለጥ የአገልጋዮች ሥራ ነው። የሚከተለው አስደናቂ መግለጫ የአንበጣዎችን ውድመት ተከትሎ የሚመጣውን የሚያሳይ ሲሆን፣ ከለዳውያን ምድሪቱን በማጥፋት የሚያስከትሉትንም ውጤት ሊገልጽ ይችላል። ለበደለኛ አሕዛብ ጊዜያዊ ፍርዶች ማስጠንቀቂያ ከተሰጠ፣ ኃጢአተኞችማ ከሚመጣው ቁጣ መዳንን እንዲሹ እንዴት አብልጠው ሊያስጠነቅቁ ይገባል! ስለዚህ በምድር ላይ ያለን ዋና ተግባራችን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ድርሻችንን ማስጠበቅ ሲሆን፣ አሁን ጣዖት ከሚያደርጓቸው ሁሉ በቅርቡ የሚነጠቁትን ነገሮች ከመውደድም መራቅን መፈለግ አለብን። የኀዘንና የኀፍረት የውጪ መግለጫዎች፣ ጾም፣ ለቅሶና ማልቀስ ሊኖሩ ይገባል፤ ለመከራ የሚፈሱ እንባዎች ለመከራው መንስኤ በሆነው ኃጢአት በሚፈሱ እንባዎች መለወጥ አለባቸው።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV Blow the trumpet in Zion; sound the alarm on my holy hill. Let all who live in the land tremble, for the day of the Lor… English BCV መዓልቲ እግዚኣብሄር ትመፅእ ኣላ፤ ቀሪባ ኸዓ እያ እሞ፥ ኣብ ፅዮን መለኸት ንፍሑ፤ ኣብቲ ቅዱስ እምባይ ድማ ኣእውዩ፤ መዓልቲ እግዚኣብሄር መፂኣ እያሞ፥ ኣብ ምድሪ ዝነብሩ ዘለዉ ዅላቶም የ… ትግርኛ GAZBIB Xiyoon gaara koo isa qulqulluu irratti fiinoo afuufaa, sagalee nama dammaqsu dhageessisaa! Guyyaan Waaqayyoo waan dhufu… Afaan Oromoo BCV GIZ ንፍሑ ቀርነ በጽዮን ወስብኩ በደብረ መቅደስየ ወይደነግፁ ኵሎሙ እለ ይነብሩ ውስተ ምድር እስመ አልጸቀት ዕለተ እግዚአብሔር ወበጽሐት። giz GAZGAZ Xiyoon gaara koo isa qulqulluu irratti fiinoo afuufaa, sagalee nama dammaqsu dhageessisaa! Guyyaan Waaqayyoo waan dhufu… Afaan Oromoo BCV aksum መዓልቲ እግዚኣብሄር ትመፅእ ኣላ፤ ቀሪባ ኸዓ እያ እሞ፥ ኣብ ፅዮን መለኸት ንፍሑ፤ ኣብቲ ቅዱስ እምባይ ድማ ኣእውዩ፤ መዓልቲ እግዚኣብሄር መፂኣ እያሞ፥ ኣብ ምድሪ ዝነብሩ ዘለዉ ዅላቶም የ… ትግርኛ AMHNIV በጽዮን መለከትን ንፉ፤ በቅዱሱ ተራራዬም የማስጠንቀቂያውን ድምፅ አሰሙ፤ በምድሪቱ የሚኖሩ ሁሉ ይንቀጥቀጡ፤ የእግዚአብሔር ቀን ቀርቦአልና፤ እርሱም በደጅ ነው። አማርኛ SWAHSUV Pigeni tarumbeta katika Sayuni, Pigeni na kelele katika mlima wangu mtakatifu; Wenyeji wote wa nchi na watetemeke; Kwa … Kiswahili