የዮሐንስ ወንጌል 9

AMHNIVአማርኛ41 ጥቅሶች5:54 አዳምጥ
አዳምጥ 5:54 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1በመንገድ ሲያልፍም ከተወለደ ጀምሮ ዐይነ ስውር የሆነ ሰው አየ።

2ደቀ መዛሙርቱም፣ “ረቢ፤ ይህ ሰው ዐይነ ስውር ሆኖ እንዲወለድ ኀጢአት የሠራ ማን ነው? እርሱ ራሱ ወይስ ወላጆቹ?” ብለው ጠየቁት።

3ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “እርሱ ወይም ወላጆቹ ኀጢአት አልሠሩም፤ ይህ የሆነው ግን የእግዚአብሔር ሥራ በእርሱ ሕይወት እንዲገለጥ ነው።

4ቀን ሳለ፣ የላከኝን ሥራ መሥራት አለብን፤ ማንም ሊሠራ የማይችልበት ሌሊት ይመጣል፤

5በዓለም ሳለሁ የዓለም ብርሃን እኔ ነኝ።”

6ይህን ካለ በኋላ፣ በምድር ላይ እንትፍ ብሎ በምራቁ ጭቃ አበጀ፤ የሰውየውንም ዐይን ቀባና፣

7“ሄደህ በሰሊሆም መጠመቂያ ታጠብ” አለው፤ ሰሊሆም ማለት ‘የተላከ’ ማለት ነው። ሰውየውም ሄዶ ታጠበ፤ እያየም ተመልሶ መጣ።

8ጎረቤቶቹና ከዚህ ቀደም ብሎ ሲለምን ያዩት ሰዎች፣ “ይህ ሰው ተቀምጦ ሲለምን የነበረው አይደለምን?” አሉ።

9አንዳንዶቹም፣ “በርግጥ እርሱ ነው” አሉ። ሌሎችም፣ “ይመስለዋል እንጂ እርሱ አይደለም” አሉ። እርሱ ግን፣ “እኔው ነኝ” አለ።

10እነርሱም፣ “ታዲያ ዐይኖችህ እንዴት ተከፈቱ?” ሲሉ ጠየቁት።

11እርሱም፣ “ኢየሱስ የሚሉት ሰው ጭቃ አድርጎ ዐይኔን ቀባኝ፤ ወደ ሰሊሆም ሄጄ እንድታጠብም ነገረኝ፤ ሄጄ ታጠብሁ፤ ማየትም ቻልሁ” ሲል መለሰ።

12እነርሱም፣ “ታዲያ፣ ያ ሰው የት አለ?” አሉት። እርሱም፣ “እኔ አላውቅም” አለ።

13እነርሱም ዐይነ ስውር የነበረውን ሰው ወደ ፈሪሳውያን ወሰዱት።

14ኢየሱስ ጭቃ የሠራበት፣ የሰውየውንም ዐይን የከፈተበት ቀን ሰንበት ነበር።

15ስለዚህ ፈሪሳውያንም እንዴት ማየት እንደ ቻለ ጠየቁት። ሰውየውም፣ “እርሱ ዐይኔን ጭቃ ቀባኝ፤ እኔም ታጠብሁ፤ ይኸው አያለሁ” አላቸው።

16ከፈሪሳውያንም አንዳንዶቹ፣ “ይህ ሰው ሰንበትን ስለማያከብር፣ ከእግዚአብሔር አይደለም” አሉ። ሌሎች ግን፣ “ኀጢአተኛ፣ እንዲህ ያሉትን ታምራዊ ምልክቶች እንዴት ሊያደርግ ይችላል?” አሉ። በመካከላቸውም አለመስማማት ተፈጠረ።

17ስለዚህ፣ ዐይነ ስውር ወደ ነበረው ሰው ተመልሰው፣ “ዐይንህን ስለ ከፈተው ሰው፣ እንግዲህ አንተ ምን ትላለህ?” አሉት። ሰውየውም፣ “እርሱ ነቢይ ነው” አለ።

18አይሁድ ወደ ወላጆቹ ልከው እስኪያስጠሯቸው ድረስ፣ ሰውየው ዐይነ ስውር እንደ ነበረና እንዳየ አላመኑም ነበር።

19እነርሱም፣ “ዐይነ ስውር ሆኖ ተወልዶአል የምትሉት ልጃችሁ ይህ ነውን? ታዲያ አሁን እንዴት ሊያይ ቻለ?” አሏቸው።

20ወላጆቹም እንዲህ ሲሉ መለሱ፤ “ልጃችን መሆኑንና ዐይነ ስውር ሆኖ መወለዱን እናውቃለን፤

21አሁን ግን እንዴት ማየት እንደቻለና ዐይኖቹን ማን እንደ ከፈተለት እኛ አናውቅም። ሙሉ ሰው ስለ ሆነ፣ ስለ ራሱ መናገር ይችላልና እርሱን ጠይቁት።”

22ኢየሱስን፣ ክርስቶስ ነው ብሎ የመሰከረ ሁሉ ከምኲራብ እንዲባረር አይሁድ አስቀድመው ወስነው ስለ ነበር፣ ወላጆቹ ይህን ያሉት አይሁድን ፈርተው ነው።

23ስለዚህ ወላጆቹ፣ “ሙሉ ሰው ስለ ሆነ እርሱን ጠይቁት” አሉ።

24ዐይነ ስውር የነበረውንም ሰው ዳግመኛ ጠርተው፣ “አንተ ሰው፤ እግዚአብሔርን አክብር፤ ይህ ሰው ኀጢአተኛ መሆኑን እኛ እናውቃለን” አሉት።

25እርሱም፣ “ኀጢአተኛ መሆኑን እኔ አላውቅም፤ ነገር ግን ዐይነ ስውር እንደ ነበርሁ፤ አሁን ግን እንደማይ ይህን አንድ ነገር ዐውቃለሁ” አለ።

26እነርሱም፣ “ምን አደረገልህ? እንዴትስ ዐይንህን ከፈተ?” ብለው ጠየቁት።

27እርሱም፣ “አስቀድሜ ነገርኋችሁ፤ አላዳመጣችሁኝም፤ ለምን እንደ ገና መስማት ፈለጋችሁ? እናንተም ደግሞ ደቀ መዛሙርቱ ልትሆኑ ትሻላችሁ?” አለ።

28ከዚህ በኋላ በእርሱ ላይ የስድብ ናዳ በማውረድ እንዲህ አሉት፤ “የዚህ ሰው ደቀ መዝሙር አንተ ነህ፤ እኛስ የሙሴ ደቀ መዛሙርት ነን!

29እግዚአብሔር ሙሴን እንደ ተናገረው እናውቃለን፤ ይህ ሰው ግን ከየት እንደ መጣ እንኳ አናውቅም።”

30ሰውየውም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ “እናንተ ከየት እንደ መጣ አለማወቃችሁ የሚያስደንቅ ነው፤ ይሁን እንጂ እርሱ ዐይኖቼን ከፈተልኝ።

31እግዚአብሔር የሚሰማው፣ የሚፈራውንና ፈቃዱን የሚያደርገውን እንጂ፣ ኀጢአተኞችን እንደማይሰማ እናውቃለን፤

32ዐይነ ስውር ሆኖ የተወለደን ሰው ዐይን የከፈተ አለ ሲባል፣ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ማንም ሰምቶ አያውቅም።

33ይህ ሰው ከእግዚአብሔር ባይሆን ኖሮ ይህን ማድረግ ባልቻለ ነበር።”

34እነርሱም፣ “ሁለንተናህ በኀጢአት ተነክሮ የተወለድህ፣ አንተ እኛን ለማስተማር እንዴት ትደፍራለህ?” ሲሉ መለሱለት፤ አባረሩትም።

35ኢየሱስም ሰውየውን እንዳባረሩት ሰማ፤ ባገኘውም ጊዜ፣ “በሰው ልጅ ታምናለህን?” አለው።

36ሰውየውም፣ “ጌታዬ፤ አምንበት ዘንድ እርሱ ማን ነው?” ሲል ጠየቀው።

37ኢየሱስም፣ “አይተኸዋል፤ አሁንም ከአንተ ጋር የሚነጋገረው እርሱ ነው” አለው።

38ሰውየውም፣ “ጌታ ሆይ፤ አምናለሁ” አለ፤ ሰገደለትም።

39ኢየሱስም፣ “ዕውሮች እንዲያዩ፣ የሚያዩም እንዲታወሩ፣ ለፍርድ ወደዚህ ዓለም መጥቻለሁ” አለ።

40ከእርሱ ጋር ከነበሩት ፈሪሳውያን አንዳንዶቹ ይህን ሰምተው፣ “ምን ማለትህ ነው? ታዲያ እኛም ዕውሮች መሆናችን ነው?” አሉት።

41ኢየሱስም፣ “ዕውሮችስ ብትሆኑ ኀጢአት ባልሆነባችሁ ነበር፤ አሁን ግን እናያለን ስለምትሉ፣ ኀጢአታችሁ እንዳለ ይኖራል” አላቸው።

ማብራሪያ

9:1-7 ክርስቶስ በበሽታ ወይም በአደጋ የታወሩትን ብዙዎችን ፈውሷል፤ እዚህ ግን ከትውልድ ጀምሮ እውር የነበረውን ፈውሷል። በዚህም እጅግ ተስፋ በሌላቸው ሁኔታዎች ውስጥ የመርዳት ኃይሉን፣ እና በተፈጥሮ እውር ለሆኑት የዓይኖችን ብርሃን የሚሰጠውን በኃጢአተኞች ነፍሳት ላይ ያለውን የጸጋውን ሥራ ገልጿል። ይህ ምስኪን ሰው ክርስቶስን ማየት ባይችልም፣ ክርስቶስ ግን እርሱን አይቶታል። እኛም ስለ ክርስቶስ ምንም የምናውቅ ወይም የምንረዳ ከሆነ፣ ይህ የሆነው እርሱ አስቀድሞ ስላወቀን ነው። ክርስቶስ ያልተለመዱ መከራዎችን አስመልክቶ፣ እነዚህ ሁልጊዜ ለኃጢአት የተለዩ ቅጣቶች ተደርገው ሊታዩ እንደማይገባ ገልጿል፤ አንዳንድ ጊዜም ለእግዚአብሔር ክብር እና ሥራዎቹን ለመግለጥ ይሆናሉ።

ሕይወታችን ቀናችን ነው፤ በዚህም የቀኑን ሥራ መሥራት ይገባናል። ሥራ የበዛብን መሆን አለብን፣ የቀን ሰዓትንም ማባከን የለብንም፤ ቀናችን ሲያልቅ የማረፍ ጊዜ ይሆናልና፣ እሱም አንድ ቀን ብቻ ነው። የሞት መቃረብ መልካምን ለመሥራትም ሆነ ለማግኘት ያሉንን ዕድሎች ሁሉ እንድንጠቀምበት ሊያፋጥነን ይገባል። የምናገኘውን መልካም ሥራ በፍጥነት ማድረግ ይገባናል። እናም ምንም የሚያስከራክር ነገር እስከሌለ ድረስ መልካም ሥራን የማይሠራ ሰው፣ ብዙ መልካም ሥራዎችን ለዘላለም ሳይሠራ ይተዋል፣ Ec 11:4።

ክርስቶስ ሰዎች የሚያይን ሰው ሊያሳውር ይችላል ብለው ከሚገምቱት በተቃራኒ፣ እውር የነበረውን ሰው እንዲያይ በማድረግ ኃይሉን ገልጿል። የሰው አእምሮ የጌታን ዘዴዎች ሊፈርድ አይችልም፤ እርሱ ሰዎች የሚንቋቸውን መንገዶችና መጠቀሚያዎችን ይጠቀማል። በክርስቶስ ሊፈወሱ የሚፈልጉ በእርሱ ሊመሩ ይገባቸዋል። ከኩሬው ተመልሶ ሲመጣ ይደነቅ ነበር እንዲሁም በእርሱም ይደነቁ ነበር፤ የሚያይ ሆኖ ተመልሷል። ይህ ክርስቶስ በወሰናቸው ሥርዓቶች ላይ በመገኘት የሚገኙትን ጥቅሞች ይወክላል፤ ነፍሳት ደካሞች ሆነው ይሄዳሉ፣ ተጠናክረውም ይመለሳሉ፤ እየተጠራጠሩ ይሄዳሉ፣ እርካታ አግኝተውም ይመለሳሉ፤ እያዘኑ ይሄዳሉ፣ ደስ እያላቸውም ይመለሳሉ፤ እውሮች ሆነው ይሄዳሉ፣ የሚያዩ ሆነውም ይመለሳሉ።

፱፥፰-፲፪ ዓይኖቻቸው የተከፈቱና ልቦቻቸው በጸጋ የነጹ ሰዎች፣ አንድ ሰው ሆነው ሳለ በባሕሪያቸው ግን እጅግ የተለዩ ሲሆኑ፣ ለቤዛው ክብር የመታሰቢያ ሐውልቶች ሆነው ይኖራሉ፤ እንዲሁም ተመሳሳይ ውድ ድነትን ለሚፈልጉ ሁሉ ጸጋውን ይመክራሉ። የእግዚአብሔርን ሥራ መንገድና ስልት ማስተዋል መልካም ነው፤ እንዲህ ሲሆንም ሥራዎቹ ይበልጥ ድንቅ ሆነው ይታያሉ። ይህን በመንፈሳዊ መንገድ ተግብሩ። በነፍስ ላይ በሚሠራው የጸጋ ሥራ ለውጡን እናያለን፣ ነገር ግን ያንን የሚያደርገውን እጅ አናይም። የመንፈስ መንገድ እንደ ነፋስ ነው፤ ድምፁን ትሰማለህ፣ ነገር ግን ከየት እንደሚመጣ ወይም ወዴት እንደሚሄድ ልትነግር አትችልም።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6