የዮሐንስ ወንጌል 1

AMHNIVአማርኛ51 ጥቅሶች7:39 አዳምጥ
አዳምጥ 7:39 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1በመጀመሪያ ቃል ነበረ፤ ቃልም ከእግዚአብሔር ጋር ነበረ፤ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።

2እርሱም በመጀመሪያ ከእግዚአብሔር ጋር ነበረ።

3ሁሉ ነገር በእርሱ ተፈጥሮአል፤ ከተፈጠረው ሁሉ ያለ እርሱ የተፈጠረ ምንም የለም።

4ሕይወት በእርሱ ነበረች፤ ይህች ሕይወት የሰው ብርሃን ነበረች።

5ብርሃንም በጨለማ ያበራል፤ ጨለማውም አላሸነፈውም።

6ከእግዚአብሔር የተላከ ዮሐንስ የተባለ አንድ ሰው ነበረ።

7ሰዎች ሁሉ በእርሱ በኩል እንዲያምኑ፣ ስለ ብርሃን ምስክር ሆኖ ለመቆም መጣ፤

8ስለ ብርሃን ሊመሰክር መጣ እንጂ እርሱ ራሱ ብርሃን አልነበረም።

9ለሰው ሁሉ ብርሃን ሰጪ የሆነው እውነተኛው ብርሃን ወደ ዓለም እየመጣ ነበር።

10እርሱ በዓለም ውስጥ ነበረ፤ ዓለም የተፈጠረው በእርሱ ቢሆንም እንኳ፣ ዓለም አላወቀውም።

11ወደ ራሱ ወገኖች መጣ፤ የገዛ ወገኖቹ ግን አልተቀበሉትም፤

12ለተቀበሉትና በስሙ ላመኑት ሁሉ ግን የእግዚአብሔር ልጆች የመሆን መብት ሰጣቸው።

13እነዚህም ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ፣ ከደም ወይም ከሥጋ ፈቃድ ወይም ከወንድ ፈቃድ አልተወለዱም።

14ቃልም ሥጋ ሆነ፤ በመካከላችንም አደረ፤ እኛም ጸጋንና እውነትን ተሞልቶ ከአባቱ ዘንድ የመጣውን የአንድያ ልጅን ክብር አየን።

15ዮሐንስም፣ “ ‘ከእኔ በኋላ የሚመጣው ከእኔ በፊት ስለ ነበረ ከእኔ ይልቃል’ ብዬ የመሰከርሁለት እርሱ ነው” በማለት ጮኾ ስለ እርሱ መሰከረ።

16ከእርሱ ሙላት ሁላችንም በጸጋ ላይ ጸጋ ተቀብለናል፤

17ሕግ በሙሴ በኩል ተሰጥቶ ነበር፤ ጸጋና እውነት ግን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል መጣ።

18ከቶውንም እግዚአብሔርን ያየ ማንም የለም፤ ነገር ግን በአብ እቅፍ ያለው አንድያ ልጁ የሆነው አምላክ እርሱ ገለጠው።

19አይሁድ፣ ማንነቱን እንዲጠይቁት ካህናትንና ሌዋውያንን ከኢየሩሳሌም ወደ እርሱ ሲልኩ፣ ዮሐንስ የሰጠው ምስክርነት ይህ ነበር።

20ከመመስከርም ወደ ኋላ አላለም፤ “እኔ ክርስቶስ አይደለሁም” ብሎ በግልጽ መሰከረ።

21እነርሱም፣ “ታዲያ አንተ ማን ነህ? ኤልያስ ነህ?” ብለው ጠየቁት። እርሱም፣ “አይደለሁም” አለ። እነርሱም፣ “ታዲያ ነቢዩ ነህ?” አሉት። እርሱም፣ “አይደለሁም” ሲል መለሰ።

22በመጨረሻም፣ “እንግዲያስ ማን ነህ? ለላኩን ሰዎች መልስ እንድንሰጥ ስለ ራስህ ምን ትላለህ?” አሉት።

23ዮሐንስም በነቢዩ በኢሳይያስ እንደ ተነገረው፣ “ ‘ለጌታ መንገድ አቅኑለት’ እያለ በምድረ በዳ የሚጮኽ ድምፅ እኔ ነኝ” ሲል መለሰ።

24ከተላኩትም ፈሪሳውያን አንዳንዶቹ፣

25“ታዲያ፣ ክርስቶስ ወይም ኤልያስ ወይም ነቢዩ ካልሆንህ፤ ለምን ታጠምቃለህ?” ብለው ጠየቁት።

26ዮሐንስም እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፤ “እኔ በውሃ አጠምቃለሁ፤ እናንተ የማታውቁት ግን በመካከላችሁ ቆሟል፤

27ከእኔ በኋላ የሚመጣው፣ የጫማውን ማሰሪያ ለመፍታት እንኳ የማልበቃ እርሱ ነው።”

28ይህ ሁሉ የሆነው ዮሐንስ ሲያጠምቅ በነበረበት ከዮርዳኖስ ማዶ በቢታንያ ነበር።

29ዮሐንስ በማግሥቱ፣ ኢየሱስ ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ እንዲህ አለ፤ “እነሆ! የዓለምን ኀጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ፤

30‘ከእኔ በኋላ የሚመጣው ከእኔ በፊት ስለ ነበር ከእኔ ይልቃል’ ያልሁት እርሱ ነው፤

31እኔ ራሴ አላወቅሁትም ነበር፤ በውሃ እያጠመቅሁ የመጣሁትም እርሱ በእስራኤል ዘንድ እንዲገለጥ ነው።”

32ከዚያም ዮሐንስ እንዲህ ሲል ምስክርነቱን ሰጠ፤ “መንፈስ እንደ ርግብ ከሰማይ ወርዶ በእርሱ ላይ ሲያርፍ አየሁ፤

33በውሃ እንዳጠምቅ የላከኝም፣ ‘በመንፈስ ቅዱስ የሚያጠምቀው፣ መንፈስ ሲወርድና በርሱ ላይ ሲያርፍ የምታየው እርሱ ነው’ ብሎ እስከ ነገረኝ ድረስ እኔም አላወቅሁትም ነበር፤

34አይቻለሁ፣ እርሱ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ እመሰክራለሁ።”

35በማግሥቱ፣ ዮሐንስ ከሁለቱ ደቀ መዛሙርቱ ጋር እንደ ገና እዚያው ቦታ ነበር፤

36ኢየሱስንም በዚያ ሲያልፍ አይቶ፣ “እነሆ! የእግዚአብሔር በግ” አለ።

37ሁለቱ ደቀ መዛሙርትም ይህን ሲናገር ሰምተው ኢየሱስን ተከተሉት።

38ኢየሱስም ዘወር ብሎ ሲከተሉት አየና፣ “ምን ትፈልጋላችሁ?” ብሎ ጠየቃቸው። እነርሱም፣ “ረቢ፣ የት ትኖራለህ?” አሉት፤ ‘ረቢ’ ማለት መምህር ማለት ነው።

39እርሱም፣ “ኑና እዩ” አላቸው። ስለዚህ ሄደው የት እንደሚኖር አዩ፤ በዚያም ዕለት አብረውት ዋሉ፤ ከቀኑም ዐሥር ሰዓት ያህል ነበር።

40ዮሐንስ የተናገረውን ሰምተው፣ ኢየሱስን ከተከተሉት ከሁለቱ አንዱ የስምዖን ጴጥሮስ ወንድም እንድርያስ ነበር።

41እንድርያስ በመጀመሪያ ያደረገው ወንድሙን ስምዖንን ፈልጎ፣ “መሲሑን አገኘነው” ብሎ መንገር ነው፤ ‘መሲሕ’ ማለት ክርስቶስ ማለት ነው።

42ወደ ኢየሱስም አመጣው። ኢየሱስም ተመለከተውና፣ “አንተ የዮና ልጅ ስምዖን ነህ፤ ኬፋ ተብለህ ትጠራለህ” አለው፤ ‘ኬፋ’ ማለት ጴጥሮስ ማለት ነው።

43በማግሥቱ፣ ኢየሱስ ወደ ገሊላ ለመሄድ ፈለገ፤ ፊልጶስንም አግኝቶ፣ “ተከተለኝ” አለው።

44ፊልጶስም እንደ እንድርያስና እንደ ጴጥሮስ ሁሉ የቤተ ሳይዳ ከተማ ሰው ነበረ።

45ፊልጶስ ናትናኤልን አግኝቶ፣ “ሙሴ በሕግ መጻሕፍት፣ ነቢያትም ስለ እርሱ የጻፉለትን የዮሴፍን ልጅ የናዝሬቱ ኢየሱስን አግኝተነዋል” አለው።

46ናትናኤልም፣ “ከናዝሬት በጎ ነገር ሊወጣ ይችላልን?” አለ። ፊልጶስም፣ “መጥተህ እይ” አለው።

47ኢየሱስም፣ ናትናኤል ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ፣ “እነሆ፤ ተንኮል የሌለበት እውነተኛ እስራኤላዊ” አለ።

48ናትናኤልም “እንዴት አወቅኸኝ?” ሲል ጠየቀው። ኢየሱስም፣ “ከበለስ ዛፍ ሥር ሳለህ፣ ገና ፊሊጶስ ሳይጠራህ አየሁህ” ሲል መለሰለት።

49ናትናኤልም መልሶ፣ “ረቢ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ፤ አንተ የእስራኤል ንጉሥ ነህ” አለ።

50ኢየሱስም፣ “ያመንኸው ከበለስ ዛፍ ሥር አየሁህ ስላልሁህ ነውን? ገና ከዚህ የሚበልጥ ነገር ታያለህ” አለው፤

51ጨምሮም፣ “እውነት እላችኋለሁ፣ ሰማይ ተከፍቶ፣ የእግዚአብሔርም መላእክት በሰው ልጅ ላይ ሲወጡና ሲወርዱ ታያላችሁ” አለው።

ማብራሪያ

ዮሐንስ 1:1-5

የእግዚአብሔር ልጅ ቃል ተብሎ የተጠራበት ቀላሉ ምክንያት፣ ቃሎቻችን አሳባችንን ለሌሎች እንደሚያስረዱ ሁሉ፣ የእግዚአብሔር ልጅም የአባቱን ሀሳብ ለዓለም ሊገልጥ ተልኮ ነበርና ይመስላል። ወንጌላዊው ስለ ክርስቶስ የሚናገረው እርሱ እግዚአብሔር መሆኑን ያረጋግጣል። ከመጀመሪያው የነበረ መሆኑን፣ ከአብ ጋርም አብሮ የነበረ መሆኑን ያረጋግጣል። ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ። ሁሉ በእርሱ ሆነ እንጂ እንደ መሣሪያ አልነበረም። ከፍ ካለው መልአክ አንስቶ እስከ ትንሹ ትል ድረስ፣ ከሆነው ሁሉ ያለ እርሱ ምንም የሆነ የለም። ይህ ለቤዛነታችንና ለመዳናችን ሥራ ምን ያህል ብቁ እንደነበረ ያሳያል። የማስተዋል ብርሃን፣ እንዲሁም የስሜት ሕይወት ከእርሱ የመነጨ ነው፣ በእርሱም ላይ የተመካ ነው። ይህ የዘላለም ቃል፣ ይህ እውነተኛ ብርሃን ያበራል፣ ጨለማ ግን አላስተዋለውም። ይህን ብርሃን እንድናይ ዓይኖቻችን እንዲከፈቱ፣ በውስጡም እንድንመላለስ፣ በዚህም በኢየሱስ ክርስቶስ ባለው እምነት ለመዳን ጥበበኞች እንድንሆን ሳናቋርጥ እንጸልይ።

፩:፮-፲፬ መጥምቁ ዮሐንስ ስለ ኢየሱስ ለመመስከር መጣ። የሰዎች አእምሮ የጨለመ መሆኑን ከሁሉ ይበልጥ የሚያሳየው፣ ብርሃኑ ከታየ በኋላም እንኳ ለእርሱ ትኩረት ለመሳብ ምስክር ማስፈለጉ ነው። ክርስቶስ እውነተኛው ብርሃን ነበር፤ እንደዚያ ተብሎ ሊጠራ የሚገባው ታላቁ ብርሃን እርሱ ነው። በመንፈሱና በጸጋው ለመዳን የሚያበሩትን ሁሉ ያበራል፤ በእርሱ ያልበሩት ግን በጨለማ ይጠፋሉ። ክርስቶስ የእኛን ሰብዓዊ ተፈጥሮ ለብሶ በመካከላችን ሲኖር በዓለም ውስጥ ነበር። የልዑሉ ልጅ እዚህ በታችኛው ዓለም ነበር። በዓለም ውስጥ ነበር፣ ነገር ግን የዓለም አልነበረም። የጠፋውን ዓለም ሊያድን መጣ፣ ምክንያቱም የራሱ የእጁ ሥራ የሆነ ዓለም ነበርና። ሆኖም ዓለም አላወቀውም። በዳኛነት ሲመጣ ግን ዓለም ያውቀዋል። ብዙዎች የክርስቶስ እንደሆኑ ይናገራሉ፣ ነገር ግን ኃጢአታቸውን ለመተው ስለማይፈልጉና በእነርሱ ላይ እንዲነግሥ ስላልተመኙ እርሱን አይቀበሉትም። የእግዚአብሔር ልጆች ሁሉ እንደገና ተወልደዋል። ይህ እንደገና መወለድ በመለኮታዊው ቃል እንደ መንገድ፣ ፩ጴጥ ፩:፳፫፣ እና በእግዚአብሔር መንፈስ እንደ ፈጻሚ ነው። በመለኮታዊ ህልውናው ክርስቶስ ሁልጊዜ በዓለም ውስጥ ነበር። የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ ግን፣ በሌላ መንገድ፣ እግዚአብሔር በሥጋ ተገልጦ ነበር። ነገር ግን በዚህ የሥጋ መጋረጃ ውስጥ ዘልቀው የወጡትን የመለኮታዊ ክብሩን ጨረሮች ልብ በሉ። ሰዎች ድክመታቸውን ከእነርሱ ጋር በጣም ለሚቀራረቡት ያሳያሉ፣ ከክርስቶስ ጋር ግን እንዲህ አልነበረም፤ ከእርሱ ጋር የጠበቀ ቅርርብ የነበራቸው ክብሩን ይበልጥ ያዩ ነበር። ምንም እንኳ በውጫዊ ሁኔታዎች የአገልጋይ መልክ የነበረው ቢሆንም፣ በጸጋዎቹ ረገድ ግን መልኩ እንደ እግዚአብሔር ልጅ ነበር። መለኮታዊ ክብሩ በቃሉ ቅድስናና በተአምራቱ ታየ። እርሱ በጸጋ የተሞላ፣ ለአባቱ ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት ያለው ነበር፣ ስለዚህም ለእኛ ሊማልድ ብቁ ነው፤ እንዲሁም በእውነት የተሞላ፣ ሊገልጣቸው የሚገቡትን ነገሮች ሙሉ በሙሉ የሚያውቅ ነበር።

1:15-18 በጊዜ ቅደም ተከተልና ሥራውን ስለመጀመሩ፣ ክርስቶስ ከዮሐንስ በኋላ መጣ፤ ነገር ግን በሌሎች ሁሉ ረገድ እርሱ ከዮሐንስ በፊት ነበር። ይህ አገላለጽ ኢየሱስ በምድር ላይ እንደ ሰው ከመገለጡ በፊት ሕልውና እንደነበረው በግልጽ ያሳያል። የመለኮት ሙላት ሁሉ በእርሱ ዘንድ ይኖራል፤ ከእርሱ ብቻ የወደቁ ኃጢአተኞች በጥበብ፣ በብርታት፣ በቅድስና፣ በአገልግሎትና በደስታ የሚያደርጋቸውን ነገር ሁሉ በእምነት ያገኛሉ፤ ወደፊትም ይቀበላሉ። በክርስቶስ የምናገኛቸው ነገሮች ሁሉ በአንድ ቃል በጸጋ ተጠቃልለዋል። እንዲህ ያለ ታላቅ፣ ባለጸጋና ዋጋ የሌለውን ስጦታ የሆነውን ጸጋ እንኳን ተቀብለናል። ይህም የእግዚአብሔር መልካም ፈቃድ ለእኛና በእኛ ውስጥ የእግዚአብሔር መልካም ሥራ ነው። የእግዚአብሔር ሕግ ቅዱስ፣ ጻድቅና መልካም ነው፤ እኛም በትክክል ልንጠቀምበት ይገባል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6