የዮሐንስ ወንጌል 16

AMHEVGአማርኛ32 ጥቅሶች4:14 አዳምጥ
አዳምጥ 4:14 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1“እንዳትሰናከሉ ይህን ተናግሬአችኋለሁ።

2ከምኵራባቸው ያወጡአችኋል፤ ከዚህ በላይ ደግሞ የሚገድላችሁ ሁሉ እግዚአብሔርን እንደሚያገለግል የሚመስልበት ጊዜ ይመጣል።

3ይህንም የሚያደርጉባችሁ አብንና እኔን ስላላወቁ ነው።

4ነገር ግን ጊዜው ሲደርስ እኔ እንደ ነገርኋችሁ ታስቡ ዘንድ ይህን ተናግሬአችኋለሁ። ከእንናንተም ጋር ስለ ነበርሁ በመጀመሪያ ይህን አልነገርኋችሁም።”

5“አሁን ግን ወደ ላከኝ እሄዳለሁ ከእናንተም፦ ‘ወዴት ትሄዳለህ?’ ብሎ የሚጠይቀኝ የለም።

6ነገር ግን ይህን ስለ ተናገርኋችሁ ኀዘን በልባችሁ ሞልቶአል።

7እኔ ግን እውነት እነግራችኋለሁ፤ እኔ እንድሄድ ይሻላችኋል። እኔ ባልሄድ አጽናኙ ወደ እናንተ አይመጣምና፤ እኔ ብሄድ ግን እርሱን እልክላችኋለሁ።

8እርሱም መጥቶ ስለ ኃጢአት ስለ ጽድቅም ስለ ፍርድም ዓለምን ይወቅሳል፤

9ስለ ኃጢአት፥ በእኔ ስለማያምኑ ነው፤ ስለ ጽድቅም፥ ወደ አብ ስለምሄድ ከዚህም በኋላ ስለማታዩኝ ነው፤

11ስለ ፍርድም፥ የዚህ ዓለም ገዥ ስለ ተፈረደበት ነው።

12የምነግራችሁ ገና ብዙ አለኝ፥ ነገር ግን አሁን ልትሸከሙት አትችሉም።

13ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ ከራሱ አይነግርምና፤ የሚመጣውንም ይነግራችኋል።

14እርሱ ያከብረኛል፥ ለእኔ ካለኝ ወስዶ ይነግራችኋልና።

15ለአብ ያለው ሁሉ የእኔ ነው፤ ስለዚህ፦ ‘ለእኔ ካለኝ ወስዶ ይነግራችኋል’ አልሁ።”

16“ጥቂት ጊዜ አለ፥ አታዩኝምም፤ ደግሞም ጥቂት ጊዜ አለ፥ ታዩኛላችሁም፥ እኔ ወደ አብ እሄዳለሁና።”

17ከደቀ መዛሙርቱም አንዳንዶቹ እርስ በርሳቸው፦ “ ‘ጥቂት ጊዜ አለ፥ አታዩኝምም፤’ ደግሞም ‘ጥቂት ጊዜ አለ፥ ታዩኛላችሁም፤’ ደግሞ፦ ‘ወደ አብ እሄዳለሁና’ የሚለን ይህ ምንድር ነው?” ተባባሉ።

18“እንግዲህ፦ ‘ጥቂት’ የሚለው ይህ ምንድር ነው? የሚናገረውን አናውቅም” አሉ።

19ኢየሱስም ሊጠይቁት እንደ ወደዱ አውቆ፡ እንዲህ አላቸው፦ “ጥቂት ጊዜ አለ፥ አታዩኝምም፤ ደግሞም ጥቂት ጊዜ አለ፥ ታዩኛላችሁ፡ ስላልሁ፥ ስለዚህ እርስ በርሳችሁ ትመራመራላችሁን?

20እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ እናንተ ታለቅሳለችሁ ሙሾም ታወጣላችሁ፥ ዓለም ግን ደስ ይለዋል፤ እናንተም ታዝናላችሁ፥ ነገር ግን ኀዘናችሁ ወደ ደስታ ይለወጣል።

21ሴት በምትወልድበት ጊዜ ወራትዋ ስለ ደረሰ ታዝናለች፤ ነገር ግን ሕፃን ከወለደች በኋላ፥ ሰው በዓለም ተወልዶአልና ስለ ደስታዋ መከራዋን ኋላ አታስበውም።

22እንግዲህ እናንተ ደግሞ አሁን ታዝናላችሁ፤ ነገር ግን እንደ ገና አያችኋለሁ ልባችሁም ደስ ይለዋል፥ ደስታችሁንም የሚወስድባችሁ የለም።

23በዚያን ቀንም ከእኔ አንዳች አትለምኑም። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ ይሰጣችኋል።

24እስከ አሁን በስሜ ምንም አልለመናችሁም፤ ደስታችሁ ፍጹም እንዲሆን ለምኑ ትቀበሉማላችሁ።”

25“ይህን በምሳሌ ነግሬአችኋለሁ፤ ነገር ግን ስለ አብ ለእናንተ በግልጥ የምናገርበት እንጂ ከዚያ ወዲያ በምሳሌ የማልናገርበት ሰዓት ይመጣል።

26በዚያን ቀን በስሜ ትለምናላችሁ፤ እኔም ስለ እናንተ አብን እንድለምን የምላችሁ አይደለሁም፤

27እናንተ ስለ ወደዳችሁኝ ከእግዚአብሔርም ዘንድ እኔ እንደ ወጣሁ ስላመናችሁ አብ እርሱ ራሱ ይወዳችኋልና።

28ከአብ ወጥቼ ወደ ዓለም መጥቻለሁ፤ ደግሞ ዓለምን እተወዋለሁ ወደ አብም እሄዳለሁ።”

29ደቀ መዛሙርቱ፦ “እነሆ፥ አሁን በግልጥ ትናገራለህ በምሳሌም ምንም አትነግርም።

30ሁሉን እንድታውቅ ማንምም ሊጠይቅህ እንዳትፈልግ አሁን እናውቃለን፤ ስለዚህ ከእግዚአብሔር እንደ ወጣህ እናምናለን፡” አሉት።

31ኢየሱስም እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፦ “አሁን ታምናላችሁን?

32እነሆ፥ እያንዳንዳችሁ ወደ ቤት የምትበታተኑበት እኔንም ለብቻዬ የምትተዉበት ሰዓት ይመጣል፥ አሁንም ደርሶአል፤ ነገር ግን አብ ከእኔ ጋር ስለ ሆነ ብቻዬን አይደለሁም።

33በእኔ ሳላችሁ ሰላም እንዲሆንላችሁ ይህን ተናግሬአችኋለሁ። በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ።”

ማብራሪያ

16:1-6 ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱን ስለሚመጣው መከራ አስቀድሞ በማስጠንቀቅ፣ ፍርሃቱ ድንገተኛ እንዳይሆንባቸው አቀደ። በእውነት የእግዚአብሔር አገልግሎት ጠላቶች የሆኑ ሰዎች ለእርሱ ቅንዓት እንዳላቸው ማስመሰል ይቻላቸዋል። ይህ ግን የአሳዳጆችን ኃጢአት አያቀልም፤ በክፋት ሥራዎች ላይ የእግዚአብሔርን ስም በመጥራት ክፋት በፍጹም አይለወጥም። ኢየሱስ በመከራው ውስጥ እንደሆነ ሁሉ፣ ተከታዮቹም በመከራቸው ውስጥ የቅዱሳት መጻሕፍትን ፍጻሜ ሊመለከቱ ይገባል። አስቀድሞ ያልነገራቸው እርሱ ከእነርሱ ጋር ሆኖ ሊያስተምራቸው፣ ሊመራቸውና ሊያጽናናቸው ስለነበረ ነው፤ ያኔ የመንፈስ ቅዱስን መገኘት ተስፋ አያስፈልጋቸውም ነበር። መከራዎች ከየት እንደሚመጡ መጠየቅ ያስደነግጠናል፤ ወዴት እንደሚሄዱ መጠየቅ ግን ያረካናል፤ ምክንያቱም ለበጎ እንደሆነ እናውቃለንና። የኀዘንተኞች ክርስቲያኖች የጋራ ስህተትና ሞኝነት የደመናውን ጨለማ ጎን ብቻ ማየት፣ እንዲሁም የደስታንና የሐሤትን ድምፅ ጆሮ ዳባ ልበስ ማለት ነው። የደቀ መዛሙርትን ልብ በኀዘን የሞላው ለዚህ ጊዜያዊ ሕይወት የነበራቸው ከመጠን ያለፈ ፍቅር ነበር። በእግዚአብሔር ያለንን ደስታ ከዓለም ፍቅርና ከእርሱ በሚመጣው የዓለም ኀዘን የበለጠ የሚከለክለው የለም።

16:7-15 የክርስቶስ መሄድ የአጽናኝ መንፈስ ለመምጣት አስፈላጊ ነበር። መንፈስ ቅዱስን መላክ የክርስቶስ ሞት ፍሬ ነበር፤ ይህም እርሱ መሄዱ ነበር። ሥጋዊ መገኘቱ በአንድ ጊዜ በአንድ ስፍራ ብቻ ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን መንፈሱ በየቦታው፣ በሁሉ ስፍራ፣ በሁሉ ጊዜ፣ በስሙ ሁለት ወይም ሦስት በተሰበሰቡበት ሁሉ አለ።

እዚህ የመንፈስ ቅዱስን ተግባር እንመልከት፤ በመጀመሪያ መገሰጽ ወይም ማሳመን ነው። የማሳመን ሥራ የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ነው፤ እርሱ ሙሉ በሙሉ ሊያደርገው ይችላል፣ ከእርሱ በቀር ማንም የለም። መንፈስ ቅዱስ የሚከተለው መንገድ በመጀመሪያ ማሳመን ከዚያም ማጽናናት ነው። መንፈስ ቅዱስ ዓለምን ስለ ኃጢአት ያሳምናል፤ ዝም ብሎ ስለእርሱ አይነግራቸውም። መንፈስ ቅዱስ ዓለምን የኃጢአት መኖርን፤ የኃጢአትን ጥፋተኝነትን፤ የኃጢአትን ሞኝነትን፤ የኃጢአትን ርኩሰት (በእርሱም ለእግዚአብሔር የተጠላን መሆናችንን)፤ የኃጢአትን ምንጭ (የረከሰ ተፈጥሮአችንን)፤ በመጨረሻም የኃጢአትን ፍሬ፣ ማለትም መጨረሻው ሞት መሆኑን ያሳምናል።

መንፈስ ቅዱስ ዓለም ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ጥፋተኛ መሆኑን ያረጋግጣል። ዓለምን ስለ ጽድቅ ያሳምናል፤ የናዝሬቱ ኢየሱስ ጻድቁ ክርስቶስ መሆኑን። ደግሞም ስለ ክርስቶስ ጽድቅ፣ ለእኛ ለጽድቅና ለመዳን የተሰጠንን። እንዴት እንደሚያገኙትና በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ ሆነው እንዴት ተቀባይነት እንደሚያገኙ ያሳያቸዋል። የክርስቶስ ዕርገት ቤዛው ተቀባይነት ማግኘቱንና ጽድቅ መጠናቀቁን ያረጋግጣል፤ ይህም አማኞች የሚጸድቁበት ነው። ስለ ፍርድ ደግሞ፣ የዚህ ዓለም ገዢ የተፈረደበት ስለሆነ። ሁሉንም ክፋት ያመጣው እርሱ ኃይሉ ሲሰበር፣ ሁሉ መልካም ይሆናል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6