ትንቢተ ኤርምያስ 9

AMHNIVአማርኛ26 ጥቅሶች5:49 አዳምጥ
አዳምጥ 5:49 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ስለ ታረዱት ወገኖቼ፣ ቀንና ሌሊት አለቅስ ዘንድ፣ ምነው፣ ራሴ የውሃ ምንጭ በሆነ! ምነው ዐይኖቼ የእንባ መጒረፊያ በሆኑልኝ!

2ሕዝቤን ትቼ፣ ርቄ እንድሄድ፣ በምድረ በዳ የእንግዶች ማደሪያ ማን በሰጠኝ! ሁሉም አመንዝሮች፣ የአታላዮች መንጋ ሆነዋላ!

3“ሐሰትን ለመናገር፣ ምላሳቸውን እንደ ቀስት ገተሩ፤ በእውነት ሳይሆን፣ በሐሰት በምድሪቱ ገነኑ፤ ከክፋት ወደ ክፋት ሄዱ፤ እኔንም አላወቁኝም፤” ይላል እግዚአብሔር።

4“እያንዳንዱ ወንድም አታላይ፣ ባልንጀራም ሁሉ ሐሜተኛ ስለ ሆነ፣ ወንድም ከወንድሙ፣ ይጠንቀቅ፣ ባልንጀራም በጓደኛው አይታመን።

5ባልንጀራ ባልንጀራውን ያታልላል፤ እውነትን የሚናገር የለም፤ ሐሰትን ይናገር ዘንድ ምላሳቸውን አሠልጥነዋል፤ ኀጢአትንም በማድረግ ራሳቸውን አድክመዋል።

6መኖሪያህ በሽንገላ መካከል ነው፤ ከሽንገላቸውም የተነሣ ሊያውቁኝ አልፈቀዱም፤” ይላል እግዚአብሔር።

7ስለዚህ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እነሆ፤ እንደ ብረት አነጥራቸዋለሁ፤ እፈትናቸዋለሁም፤ ስለ ሕዝቤ ኀጢአት፣ ከዚህ የተለየ ምን ማድረግ እችላለሁ?

8ምላሳቸው የሚገድል ቀስት ነው፤ በሽንገላ ይናገራል፤ ሁሉም ከባልንጀራው ጋር በፍቅር ይናገራል፤ በልቡ ግን ያደባበታል።

9ታዲያ ስለ እነዚህ ነገሮች ልቀጣቸው አይገባኝምን?” ይላል እግዚአብሔር፤ “እንደዚህ ዐይነቱንስ ሕዝብ፣ አልበቀልምን?

10ስለ ተራሮች አለቅሳለሁ፤ ዋይ ዋይ እላለሁ፤ በምድረ በዳ ስላሉትም መሰማሪያዎች አዝናለሁ፤ ሰው የማያልፍባቸው ባድማ ሆነዋል፤ የከብቶች ጩኸት አይሰማም፤ የሰማይ ወፎች ሸሽተዋል፤ የዱር አራዊትም ጠፍተዋል።

11“ኢየሩሳሌምን የፍርስራሽ ክምር፣ የቀበሮም ጐሬ አደርጋታለሁ፤ የይሁዳንም ከተሞች፣ ሰው የማይኖርባቸው ባድማ አደርጋቸዋለሁ።”

12ይህን መረዳት የሚችል ጥበበኛ ሰው ማን ነው? እግዚአብሔር ገልጾለት ይህንስ ማስረዳት የሚችል ማን ነው? ምድሪቱስ ሰው እንደማያልፍበት በረሓ ለምን ጠፋች? ለምን ወና ሆነች?

13እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፤ “ይህ የሆነው የሰጠኋቸውን ሕጌን ትተው ስላልታዘዙኝና ሥርዐቴን ስላልተከተሉ ነው።

14በዚህ ፈንታ፣ በልባቸው እልኸኝነት በመሄድ አባቶቻቸው ያስተማሯቸውን በአሊምን ተከተሉ።”

15ስለዚህ የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ እንዲህ ይላል፤ “እነሆ፤ ይህን ሕዝብ መራራ ምግብ አበላዋለሁ፤ የተመረዘንም ውሃ አጠጣዋለሁ።

16እነርሱንም ሆነ አባቶቻቸውን በማያውቋቸው ሕዝቦች መካከል እበትናቸዋለሁ፤ እስካጠፋቸውም ድረስ በሰይፍ አሳድዳቸዋለሁ።”

17የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እንግዲህ፤ አልቃሽ ሴቶች ጥሩ፤ ሥልጡን ሙሾ አውራጆች አስመጡ፤

18እነርሱ ፈጥነው ይምጡ፤ ዐይኖቻችን እንባ እስኪያጐርፉ፣ ሽፋሽፍቶቻችንም ውሃ እስኪያመነጩ፣ ስለ እኛ ሙሾ ያውርዱልን።

19እነሆ የዋይታ ድምፅ ከጽዮን ተሰምቶአል፤ እንዲህም ይላል፤ ‘ምንኛ ወደቅን! ውርደታችንስ እንዴት ታላቅ ነው! ቤቶቻችን ፈራርሰዋልና፤ አገራችንን ጥለን እንሂድ።’ ”

20እናንት ሴቶች ሆይ፤ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ ጆሮቻችሁን ከአንደበቱ ለሚወጡት ቃላት ክፈቱ፤ ሴቶች ልጆቻችሁን ዋይታ፣ አንዳችሁም ሌላውን ሙሾ አስተምሩ።

21ሞት በመስኮቶቻችን ገብቶአል፤ ወደ ምሽጎቻችንም ዘልቆአል፤ ሕፃናትን ከየመንገዱ፣ ወጣቶችን ከየአደባባዩ ጠራርጎ ወስዶአል።

22እንዲህ በሉ፤ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ ‘የሰዎች ሬሳ፣ በሜዳ እንደተጣለ ጕድፍ፣ ማንም እንደማይሰበስበው፣ ከዐጫጅ ኋላ እንደተተወ ቃርሚያ ይወድቃል።’ ”

23እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ጥበበኛ በጥበቡ አይታበይ፤ ኀያልም በኀይሉ አይመካ፤ ሀብታምም በሀብቱ አይኵራራ፤

24የሚመካ ግን፣ እኔ እግዚአብሔር እንደሆንሁ በማወቁና፣ በምድር ላይ ምሕረትን፣ ፍትሕንና ጽድቅን የማደርግ መሆኔን በመረዳቱ፣ በዚህ ይመካ፤ እኔ በእነዚህ ነገሮች፣ እደሰታለሁና፤” ይላል እግዚአብሔር።

25እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ሥጋቸውን ብቻ የተገረዙትን ሁሉ የምቀጣበት ጊዜ ይመጣል፤

26እነርሱም ግብፅ፣ ይሁዳ፣ ኤዶም፣ አሞን፣ ሞዓብና ጠጒራቸው ዙሪያውን የሚከረከም የበረሓ ነዋሪዎች ሁሉ ናቸው፤ እነዚህ ሕዝቦች ሁሉ በርግጥ የተገረዙ አይደሉምና፤ የእስራኤልም ቤት ሁሉ ልባቸው አልተገረዘም።

ማብራሪያ

9:1-11 ኤርምያስ እጅግ አለቀሰ፤ ይሁን እንጂ ሕዝቡ የእግዚአብሔርን እጅ በአግባቡ እንዲገነዘቡ ለማድረግ ይበልጥ ማልቀስ ቢችል እመኝ ነበር። ነገር ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በኩል ከእግዚአብሔር ጋር ህብረት የሌለበትና የመንፈስ ቅዱስ ተጽዕኖ የሌለበት በረሃው እንኳን የፈተናና የክፋት ስፍራ መሆን አለበት፤ እነዚህ በረከቶች ሲኖሩን ግን በተጨናነቁ ከተሞች ውስጥም በቅድስና መኖር እንችላለን። ሕዝቡ ምላሳቸውን ለውሸት አስለምደው ነበር። በጣም ውሸታሞች ስለነበሩ ወንድም እንኳ ቢሆን ሊታመን አልቻለም። ሲነግዱና ሲደራደሩ ውሸት መሆኑን እያወቁ እንኳን ለራሳቸው ጥቅም የሚሆነውን ማንኛውንም ነገር ይናገሩ ነበር። ነገር ግን እግዚአብሔር ኃጢአታቸውን መዝግቦ ነበር። የእግዚአብሔር እውቀት በሌለበት ምን መልካም ነገር ሊጠበቅ ይችላል? እርሱም በእርሷ ውስጥ በሚኖሩት ክፋት የተነሳ ለም መሬትን ወደ በረሃነት ለመለወጥ ብዙ መንገዶች አሉት።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG ተወግተው ስለ ሞቱ ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ሰዎች ሌሊትና ቀን አለቅስ ዘንድ ራሴ ውኃ፥ ዓይኔም የእንባ ምንጭ በሆነልኝ! አማርኛ ENGNIV Oh, that my head were a spring of water and my eyes a fountain of tears! I would weep day and night for the slain of my… English BCV ነቶም ተወጊኦም ዝሞቱ ደቂ ጓል ህዝበይ፥ ለይትን መዓልትን ክበክስ፥ ርእሰይ ዒላ ማይ፥ ኣዒንተይ ድማ፥ ፈልፋሊ ንብዓት ኮይኑ እንተ ዝኸውን መን ምሃበኒ! ትግርኛ GAZBIB Halkanii fi guyyaa utuun wal irraa hin kutin, saba koo warra qalamanii dhumaniif akkan boo'utti, maaloo mataan koo iddo… Afaan Oromoo BCV GIZ መኑ ይሁበኒ ማየ ለርእስየ ወፈልፈለ አንብዕ ለአዕይንትየ እብክዮሙ ለሕዝብየ መዓልተ ወሌሊተ ለቅቱላነ ወለተ ሕዝብየ። giz GAZGAZ Halkanii fi guyyaa utuun wal irraa hin kutin, saba koo warra qalamanii dhumaniif akkan boo'utti, maaloo mataan koo iddo… Afaan Oromoo BCV aksum ነቶም ተወጊኦም ዝሞቱ ደቂ ጓል ህዝበይ፥ ለይትን መዓልትን ክበክስ፥ ርእሰይ ዒላ ማይ፥ ኣዒንተይ ድማ፥ ፈልፋሊ ንብዓት ኮይኑ እንተ ዝኸውን መን ምሃበኒ! ትግርኛ SWAHSUV Laiti kichwa changu kingekuwa maji, na macho yangu kuwa chemchemi ya machozi, ili nipate kulia mchana na usiku kwa ajil… Kiswahili