ትንቢተ ኤርምያስ 9

AMHEVGአማርኛ25 ጥቅሶች4:47 አዳምጥ
አዳምጥ 4:47 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ተወግተው ስለ ሞቱ ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ሰዎች ሌሊትና ቀን አለቅስ ዘንድ ራሴ ውኃ፥ ዓይኔም የእንባ ምንጭ በሆነልኝ!

2ሁሉም አመንዝሮች፥ የአታላዮች ጉባኤ ናቸውና ሕዝቤን እተዋቸው ዘንድ ከእነርሱም እለይ ዘንድ በምድረ በዳ የመንገደኞች ማደሪያን ማን በሰጠኝ?

3ምላሳቸውን ስለ ሐሰት እንደ ቀስት ገተሩ፤ በምድር በረቱ ነገር ግን ለእውነት አይደለም፤ ከክፋት ወደ ክፋት ይሄዳሉና እኔንም አላወቁምና፥ ይላል እግዚአብሔር።

4ወንድምም ሁሉ ያሰናክላልና፥ ባልንጀራም ሁሉ ያማልና እናንተ ሁሉ ከባልንጀሮቻችሁ ተጠንቀቁ፥ በወንድሞቻችሁም አትታመኑ።

5ሰውም ሁሉ ባልንጀራውን ያታልላል በእውነትም አይናገርም፤ ሐሰትን መናገርንም ምላሳቸው ተምሮአል፥ ክፉንም ለማድረግ ይደክማሉ።

6ማደሪያህ በሽንገላ መካከል ነው፥ ከሽንገላም የተነሣ እኔን ያውቁኝ ዘንድ እንቢ ብለዋል፥ ይላል እግዚአብሔር።

7ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ አቀልጣቸዋለሁ እፈትናቸውማለሁ፤ ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ክፋት ከዚህ ሌላ የማደርገው ምንድር ነው?

8ምላሳቸው የተሳለ ፍላጻ ነው፤ ሽንገላን ይናገራሉ ሰው ከባልንጀራው ጋር በሰላም ይናገራል፥ በልቡ ግን ያደባበታል።

9በውኑ ስለዚህ ነገር አልቀሥፍምን? ይላል እግዚአብሔር፤ ነፍሴስ እንደዚህ ባለ ሕዝብ ላይ አትበቀልምን?

10ለተራሮች ልቅሶን ለምድረ በዳ ማሰማርያዎችም ዋይታን አነሣለሁ፥ ሰው እንዳያልፍባቸው በእሳት ተቃጥለዋልና። ሰዎችም የከብቱን ድምፅ አይሰሙም፤ ከሰማይ ወፎች ጀምሮ እስከ እንስሳ ድረስ ሸሽተው ሄደዋል።

11ኢየሩሳሌምንም የፍርስራሽ ክምር የቀበሮም ማደሪያ አደርጋታለሁ፥ የይሁዳንም ከተሞች ሰው የማይቀመጥባት ባድማ አደርጋቸዋለሁ።

12ይህን የሚያስተውል ጠቢብ ሰው ማን ነው? ያወራስ ዘንድ የእግዚአብሔር አፍ ለማን ተናገረ? ሰው እንዳያልፍባት ምድርስ ስለምን ጠፋች፥ እንደ ምድረ በዳስ ስለ ምን ተቃጠለች?

13እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፦ የሰጠኋቸውን ሕጌን ትተዋልና፥ ቃሌንም አልሰሙምና፥

14ነገር ግን የልባቸውን ምኞትና አባቶቻቸው ያስተማሩአቸውን በኣሊምን ተከትለዋልና፥

15ስለዚህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ይህን ሕዝብ እሬትን አበላዋለሁ የሐሞትንም ውኃ አጠጣዋለሁ።

16እነርሱና አባቶቻቸውም ባላወቁአቸው አሕዛብ መካከል እበትናቸዋለሁ፥ እስካጠፋቸውም ድረስ በስተ ኋላቸው ሰይፍን እሰድድባቸዋለሁ።

17እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እንዲመጡ አልቃሾች ሴቶችን ጥሩ፤ እንዲመጡም ወደ ብልሃተኞች ሴቶች ላኩ፤

18ዓይኖቻችንም እንባ እንዲያፈስሱ የዓይናችንም ሽፋሽፍቶች ውኃን እንዲያፈልቁ ፈጥነው ለእኛ ልቅሶውን ይያዙ።

19በጽዮን፦ እንዴት ተበዘበዝን! ምድርንም ትተናልና፥ ቤቶቻችንንም አፍርሰዋልና እንዴት አፈርን! የሚል የልቅሶ ድምፅ ተሰምቶአል።

20እናንተ ሴቶች ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፥ ጆሮአችሁም የአፉን ቃል ትቀበል፥ ለሴቶች ልጆቻችሁም ልቅሶውን፥ እያንዳንዳችሁም ለባልንጀሮቻችሁ ዋይታውን አስተምሩ።

21ሕፃናቱን ከመንገድ ጕልማሶቹንም ከአደባባይ ያጠፉ ዘንድ ሞት ወደ መስኮታችን ደርሶአል ወደ አዳራሻችንም ውስጥ ገብቶአል።

22የሰውም ሬሳ እንደ ጕድፍ በእርሻ ላይ፥ ማንምም እንደማይሰበስበው ከአጫጆች በኋላ እንደሚቀር ቃርሚያ ይወድቃል።

23እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጠቢብ በጥበቡ አይመካ፥ ኃያልም በኃይሉ አይመካ፥ ባለ ጠጋም በብልጥግናው አይመካ፤

24ነገር ግን የሚመካው፦ ምሕረትንና ፍርድን ጽድቅንም በምድር ላይ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን በማወቁና በማስተዋሉ በዚህ ይመካ፤ ደስ የሚያሰኙኝ እነዚህ ናቸውና፥ ይላል እግዚአብሔር።

25አሕዛብ ሁሉ ያልተገረዙ ናቸውና፥ የእስራኤልም ቤት ሁሉ ልባቸው ያልተገረዘ ነውና የተገረዙትን ሁሉ፥ ግብፅንና ይሁዳን ኤዶምያስንም የአሞንንም ልጆች ሞዓብንም በምድረ በዳም የተቀመጡትን ጠጕራቸውን በዙሪያ የተላጩትን ሁሉ፥ ባለመገረዛቸው እነርሱን የምቀጣበት ዘመን እነሆ ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር።

ማብራሪያ

9:1-11 ኤርምያስ እጅግ አለቀሰ፤ ይሁን እንጂ ሕዝቡ የእግዚአብሔርን እጅ በአግባቡ እንዲገነዘቡ ለማድረግ ይበልጥ ማልቀስ ቢችል እመኝ ነበር። ነገር ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በኩል ከእግዚአብሔር ጋር ህብረት የሌለበትና የመንፈስ ቅዱስ ተጽዕኖ የሌለበት በረሃው እንኳን የፈተናና የክፋት ስፍራ መሆን አለበት፤ እነዚህ በረከቶች ሲኖሩን ግን በተጨናነቁ ከተሞች ውስጥም በቅድስና መኖር እንችላለን። ሕዝቡ ምላሳቸውን ለውሸት አስለምደው ነበር። በጣም ውሸታሞች ስለነበሩ ወንድም እንኳ ቢሆን ሊታመን አልቻለም። ሲነግዱና ሲደራደሩ ውሸት መሆኑን እያወቁ እንኳን ለራሳቸው ጥቅም የሚሆነውን ማንኛውንም ነገር ይናገሩ ነበር። ነገር ግን እግዚአብሔር ኃጢአታቸውን መዝግቦ ነበር። የእግዚአብሔር እውቀት በሌለበት ምን መልካም ነገር ሊጠበቅ ይችላል? እርሱም በእርሷ ውስጥ በሚኖሩት ክፋት የተነሳ ለም መሬትን ወደ በረሃነት ለመለወጥ ብዙ መንገዶች አሉት።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV Oh, that my head were a spring of water and my eyes a fountain of tears! I would weep day and night for the slain of my… English BCV ነቶም ተወጊኦም ዝሞቱ ደቂ ጓል ህዝበይ፥ ለይትን መዓልትን ክበክስ፥ ርእሰይ ዒላ ማይ፥ ኣዒንተይ ድማ፥ ፈልፋሊ ንብዓት ኮይኑ እንተ ዝኸውን መን ምሃበኒ! ትግርኛ GAZBIB Halkanii fi guyyaa utuun wal irraa hin kutin, saba koo warra qalamanii dhumaniif akkan boo'utti, maaloo mataan koo iddo… Afaan Oromoo BCV GIZ መኑ ይሁበኒ ማየ ለርእስየ ወፈልፈለ አንብዕ ለአዕይንትየ እብክዮሙ ለሕዝብየ መዓልተ ወሌሊተ ለቅቱላነ ወለተ ሕዝብየ። giz GAZGAZ Halkanii fi guyyaa utuun wal irraa hin kutin, saba koo warra qalamanii dhumaniif akkan boo'utti, maaloo mataan koo iddo… Afaan Oromoo BCV aksum ነቶም ተወጊኦም ዝሞቱ ደቂ ጓል ህዝበይ፥ ለይትን መዓልትን ክበክስ፥ ርእሰይ ዒላ ማይ፥ ኣዒንተይ ድማ፥ ፈልፋሊ ንብዓት ኮይኑ እንተ ዝኸውን መን ምሃበኒ! ትግርኛ AMHNIV ስለ ታረዱት ወገኖቼ፣ ቀንና ሌሊት አለቅስ ዘንድ፣ ምነው፣ ራሴ የውሃ ምንጭ በሆነ! ምነው ዐይኖቼ የእንባ መጒረፊያ በሆኑልኝ! አማርኛ SWAHSUV Laiti kichwa changu kingekuwa maji, na macho yangu kuwa chemchemi ya machozi, ili nipate kulia mchana na usiku kwa ajil… Kiswahili