ትንቢተ ኤርምያስ 6

AMHNIVአማርኛ30 ጥቅሶች6:17 አዳምጥ
አዳምጥ 6:17 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1“እናንት የብንያም ልጆች፤ ክፉ ነገር፣ ታላቅም ጥፋት ከሰሜን ድንገት ይመጣልና፣ ከኢየሩሳሌም ሸሽታችሁ አምልጡ፤ በቴቁሔ መለከትን ንፉ፤ በቤትሐካሪም ላይ ምልክት ከፍ አድርጋችሁ አሳዩ።

2ውብና ሽሙንሙን የሆነችዋን፣ የጽዮንን ሴት ልጅ አጠፋታለሁ።

3እረኞች መንጎቻቸውን ይዘው ይመጡባታል፤ ድንኳናቸውን በዙሪያዋ ይተክላሉ፤ እያንዳንዳቸውም በየአቅጣጫቸው መንጋቸውን ያሰማራሉ።

4“በእርሷ ላይ ጦርነት ዐውጁ፤ ተነሡ በቀትር አደጋ እንጣልባት፤ ወይ ጉድ! ቀኑ እኮ መሸብን! ጥላው ረዘመ።

5እንግዲህ ተነሡ በሌሊት እናጥቃት፤ ምሽጎቿንም እንደምስስ!”

6የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ዛፎቹን ቍረጡ፤ በኢየሩሳሌም ዙሪያ የዐፈር ድልድል ሥሩ። ይህቺ ከተማ ቅጣት ይገባታል፤ ግፍን ተሞልታለችና።

7የውሃ ጒድጓድ ውሃ እንደሚያመነጭ፣ እርሷም እንዲሁ ክፋቷን ታፈልቃለች። ዐመፅና ጥፋት በውስጧ ይስተጋባል፤ ሕመሟና ቍስሏ ዘወትር ይታየኛል።

8ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ተጠንቀቂ፤ አለበለዚያ ከአንቺ ዘወር እላለሁ፤ ማንም ሊኖርባት እስከማይችል ድረስ፣ ምድርሽን ባዶ አደርጋለሁ።”

9የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “የወይን ፍሬ ተሟጦ እንደሚቃረም፣ ከእስራኤል የተረፉትን እንዲሁ ይቃርሟቸው። ወይን ለቃሚ እንደሚለቅም፣ እጅህን ወደ ቅርንጫፎቹ ደጋግመህ ዘርጋ።”

10ለማን ልናገር? ማንን ላስጠንቅቅ? ማንስ ይሰማኛል? እነሆ፣ ጆሮዎቻቸው አልተገረዙምና፣ መስማት አይችሉም። በእግዚአብሔር ቃል ይሣለቃሉ፤ ደስም አይሰኙበትም።

11በእነርሱ ላይ በእግዚአብሔር ቍጣ ተሞልቻለሁ፤ በውስጤም ልይዘው አልቻልሁም። “መንገድ ላይ በሚገኙ ሕፃናት፣ በተሰበሰቡ ወጣቶችም ላይ አፍስሰው፤ ባልም ሚስትም፣ ያረጁና የጃጁም አያመልጡም።

12በምድሪቱ በሚኖሩት ላይ፣ እጄን በምዘረጋበት ጊዜ፣ ዕርሻቸውና ሚስቶቻቸው ሳይቀሩ፣ ቤቶቻቸው ለሌሎች ይሆናሉ፤” ይላል እግዚአብሔር።

13“ከትንሹ እስከ ትልቁ ሰው፣ ሁሉም ለጥቅም የሚስገበገቡ ናቸው፤ ነቢያቱም ካህናቱም ሳይቀሩ፣ ሁሉም ያጭበረብራሉ።

14የሕዝቤን ቍስል እንደ ቀላል ቈጠሩ፣ እንዲፈወስም ተገቢውን እንክብካቤ አላደረጉለትም፤ ሰላምም ሳይኖር፣ ‘ሰላም፣ ሰላም’ ይላሉ።

15ስለ ጸያፉ ተግባራቸው ዐፍረዋል እንዴ? ኧረ ጨርሶ ዕፍረት የላቸውም! ዕፍረት ምን እንደሆነ እንኳ አያውቁም፤ ስለዚህ ከሚወድቁት ጋር ይወድቃሉ፤ በምቀጣቸውም ጊዜ ይዋረዳሉ፤” ይላል እግዚአብሔር።

16እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “መንታ መንገድ ላይ ቁሙ፣ ተመልከቱም፤ መልካሟን፣ የጥንቷን መንገድ ጠይቁ፤ በእርሷም ላይ ሂዱ። ለነፍሳችሁ ዕረፍት ታገኛላችሁ፤ እናንተ ግን፣ ‘በእርሷ አንሄድም’ አላችሁ።

17ጠባቂዎችን አቆምሁላችሁ፤ ‘የመለከትንም ድምፅ ስሙ’ አልኋችሁ፤ እናንተ ግን፣ ‘አንሰማም’ አላችሁ።

18እንግዲህ ሕዝቦች ሆይ ስሙ፤ እናንተም ምስክሮች ምን እንደሚገጥማቸው አስተውሉ።

19ምድር ሆይ፤ ስሚ፤ ቃሌን ስላላደመጡ፣ ሕጌንም ስለናቁ፣ በዚህ ሕዝብ ላይ የሐሳባቸውን ውጤት፣ ጥፋትን አመጣባቸዋለሁ።

20ዕጣን ከሳባ ምድር፣ ጣፋጩ ቅመም ከሩቅ አገር ቢመጣ ምን ይጠቅመኛል? የሚቃጠል መሥዋዕታችሁን አልቀበልም፤ ሌላውም መሥዋዕታችሁ ደስ አያሰኙኝም፤

21ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ በዚህ ሕዝብ ፊት መሰናክልን አስቀምጣለሁ፤ አባቶችና ወንዶች ልጆች በአንድነት ይደናቀፉበታል፤ ጎረቤቶችና ባልንጀሮችም ይጠፋሉ።”

22እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እነሆ፤ ሰራዊት፣ ከሰሜን ምድር እየመጣ ነው፤ ከምድር ዳርቻም፣ ታላቅ ሕዝብ እየተነሣሣ ነው።

23ቀስትና ጦር ይዘዋል፤ ጨካኞችና ምሕረት የለሽ ናቸው፤ ፈረሶቻቸውን ሲጋልቡ፤ ድምፃቸው እንደተናወጠ ባሕር ነው፤ የጽዮን ልጅ ሆይ፤ ለሰልፍ የታጠቁ ሆነው፣ ሊወጉሽ ይመጣሉ።”

24ስለ እነርሱ ወሬ ደርሶናል፤ ክንዶቻችንም ዝለዋል፤ ጭንቀት ይዞናል፤ እንደምታምጥም ሴት ሆነናል።

25ጠላት ሰይፍ ታጥቆአል፤ በየቦታውም ሽብር ሞልቶአል፤ ስለዚህ ወደ ውጭ አትውጡ፤ በየመንገዱ አትዘዋወሩ።

26የሕዝቤ ልጅ ሆይ፤ ማቅ ልበሺ፤ በዐመድም ላይ ተንከባለዪ፤ አንድያ ልጁን እንዳጣ ሰው፣ ምርር ብለሽ አልቅሺ፤ አጥፊው በድንገት፣ በላያችን ይመጣልና።

27“ብረት እንደሚፈተን፣ የሕዝቤን መንገድ፣ አካሄዳቸውንም እንድትፈትን፣ አንተን ፈታኝ አድርጌሃለሁ።

28ሁሉም ለማማት የሚዞሩ፣ ድድር ዐመፀኞች፣ ናስና ብረት የሆኑ፣ ምግባረ ብልሹዎች ናቸው።

29ርሳሱን ለማቅለጥ፣ ወናፉ በብርቱ አናፋ፤ ግን ምን ይሆናል፣ ከንቱ ልፋት ነው፤ ክፉዎች ጠርገው አልወጡምና።

30እግዚአብሔር ንቆአቸዋልና፣ የተናቀ ብር ተብለው ይጠራሉ።

ማብራሪያ

፮፥፩-፰ ምንም ዓይነት ዘዴዎች ቢሠራባቸውም፣ ከእግዚአብሔር ፍርዶች ጋር መከራከር ከንቱ ነው። በዚህ ሕይወት ደስታዎች ውስጥ በጠለቅን ቁጥር፣ ለዚህ ሕይወት ችግሮች ራሳችንን የማንመጥን እንሆናለን። የከለዳውያን ሠራዊት በይሁዳ ምድር ላይ ሰብሮ ይገባል፤ በጥቂት ጊዜ ውስጥም ሁሉንም ይውጣል። በኃጢአት መንገዶች ውስጥ ግድ የለሾችና ደህንነት የተሰማቸው የሚጎበኙበት ቀን ይመጣል። ዘላለማዊ ድነትን የምንሠራለትና የዚያን ድነት ጠላቶች የምንዋጋቸው ሲኖር፣ ቸል ማለት ሞኝነት ነው። እነርሱ ግን በዚህ መልኩ የጓጉት የእግዚአብሔርን ምክሮች ለመፈጸም ሳይሆን የራሳቸውን ሀብት ለመሙላት ነበር፤ ሆኖም እግዚአብሔር በዚህ የራሱን ዓላማ አሳካ። የሰው የረከሰ ልብ፣ በተፈጥሮአዊ ሁኔታው፣ ልክ ምንጭ ውኃውን እንደሚያፈልቀው ሁሉ፣ ክፉ ሐሳቦችን ያፈልቃል። ሁልጊዜ ይፈሳል፣ ሆኖም ሁልጊዜ ሙሉ ነው። የምሕረት አምላክ የሚያስቆጣ ሕዝብ ቢሆንም እንኳን ለመልቀቅ አይፈልግም፤ ነገሮች ወደ ጽንፍ እንዳይደርሱ በንስሐና በማስተካከል ሊያስቀሩ ይችሉ ዘንድ ከእነርሱ ጋር በቅንነት ይለምናል።

፮፥፱-፲፯ ጌታ በቀልን ሊፈጽም ሲነሳ፣ በየትኛውም ዕድሜ፣ ደረጃ ወይም ጾታ ያሉ ኃጢአተኞች ማንም አያመልጥም። ልባቸው በዓለም ላይ አርፎ ነበርና፣ ፍቅሯም ሙሉ በሙሉ ወስዷቸው ነበር።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG እናንተ የብንያም ልጆች፥ ክፉ ነገር ታላቅም ጥፋት ከሰሜን ይጐበኛልና ከኢየሩሳሌም ውስጥ ሽሹ፥ በቴቁሔ መለከቱን ንፉ፥ በቤትሐካሪም ላይ ምልክት አንሡ። አማርኛ ENGNIV “Flee for safety, people of Benjamin! Flee from Jerusalem! Sound the trumpet in Tekoa! Raise the signal over Beth Hakke… English BCV ኣቱም ደቂ ብንያም፥ መዓትን ዓብዪ ጥፍኣትን ካብ ሰሜን ይመፅእ ኣሎ እሞ፥ ካብ ማእኸል ኢየሩሳሌም ህደሙ፤ ኣብ ቴቁሔ መለኸት ንፍሑ፤ ኣብ ርእሲ ቤት ሃካሪም ምልክት ኣልዕሉ። ትግርኛ GAZBIB Waaqayyo,“Yaa ijoollee Benyaamiin, badiisi biyya gara bitaatii sababii dhufaa jiruuf, diigamuu guddaanis waan dhi'aatee… Afaan Oromoo BCV GIZ ጽንዑ ደቂቀ ብንያም በማዕከለ ኢየሩሳሌም ወበቴቁሔ ንፍሑ ቀርነ፡ ወንሥኡ ትእምርተ በቤተ ካሪም፡ እስመ ሐወፀት እኪት እምነ መስዕ ወይከውን ዓቢይ ቅጥቃጤ። giz GAZGAZ Waaqayyo,“Yaa ijoollee Benyaamiin, badiisi biyya gara bitaatii sababii dhufaa jiruuf, diigamuu guddaanis waan dhi'aatee… Afaan Oromoo BCV aksum ኣቱም ደቂ ብንያም፥ መዓትን ዓብዪ ጥፍኣትን ካብ ሰሜን ይመፅእ ኣሎ እሞ፥ ካብ ማእኸል ኢየሩሳሌም ህደሙ፤ ኣብ ቴቁሔ መለኸት ንፍሑ፤ ኣብ ርእሲ ቤት ሃካሪም ምልክት ኣልዕሉ። ትግርኛ SWAHSUV Kimbieni mpate kuwa salama, enyi wana wa Benyamini; tokeni katika Yerusalemu, pigeni tarumbeta katika Tekoa, simamishen… Kiswahili