ትንቢተ ኤርምያስ 49

AMHEVGአማርኛ39 ጥቅሶች7:49 አዳምጥ
አዳምጥ 7:49 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ስለ አሞን ልጆች፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ለእስራኤል ልጆች የሉትምን? ወይስ ወራሽ የለውምን? ስለ ምን ሚልኮም ጋድን ወረሰ? ሕዝቡስ በከተሞቹ ላይ ስለ ምን ተቀመጠ?

2ስለዚህ፥ እነሆ፥ በአሞን ልጆች ከተማ በረባት ላይ የሰልፍ ውካታን የማሰማበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር፤ የፍርስራሽ ክምርም ትሆናለች፥ ሴቶች ልጆችዋም በእሳት ይቃጠላሉ፥ እስራኤልም የወረሱትን ይወርሳል፥ ይላል እግዚአብሔር።

3ሐሴቦን ሆይ፥ ጋይ ፈርሳለችና አልቅሺላት እናንተም የረባት ሴቶች ልጆች ሆይ፥ ሚልኮም ካህናቱና አለቆቹም በአንድነት ይማረካሉና ጩኹ፥ ማቅም ታጠቁ፥ አልቅሱም፥ በቅጥሮችም መካከል ተርዋርዋጡ።

4ማን ይመጣብኛል ብለሽ በመዝገብሽ የታመንሽ አንቺ ከዳተኛ ልጅ ሆይ፥ በሸለቆችሽ፥ ውኃ በሚያረካቸው ሸለቆችሽ፥ ስለ ምን ትመኪያለሽ?

5እነሆ፥ በዙሪያሽ ካሉት ሁሉ ዘንድ ፍርሃትን አመጣብሻለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ እያንዳንዳችሁም በፊታችሁ ወዳለው ስፍራ ትሰደዳላችሁ፥ የሚሸሹትንም የሚሰበስብ የለም።

6ነገር ግን ከዚያ በኋላ የአሞንን ልጆች ምርኮ እመልሳለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።

7ስለ ኤዶምያስ፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በውኑ በቴማን ጥበብ የለምን? ከብልሃተኞችስ ምክር ጠፍቶአልን?

8ጥበባቸውስ አልቆአልን? እናንተ በድዳን የምትኖሩ ሆይ፥ የዔሳውን ጥፋት፥ የምጐበኝበትን ጊዜ፥ አመጣበታለሁና ሽሹ፥ ወደ ኋላ ተመለሱ፥ በጥልቅም ውስጥ ተቀመጡ።

9ወይን ለቃሚዎች ቢመጡብህ፥ ቃርሚያውን አይተውልህምን? ሌቦችስ በሌሊት ቢመጡ፥ የሚያጠፉት እስኪበቃቸው ድረስ አይደለምን?

10እኔ ግን ዔሳውን ዐራቈትሁት፥ የተሸሸጉትንም ስፍራዎች ገለጥሁ፥ ይሸሸግም ዘንድ አይችልም፤ ዘሩም ወንድሞቹም ጎረቤቶቹም ጠፍተዋል እርሱም የለም።

11ድሀ አደጎችህን ተው፥ እኔም በሕይወት አኖራቸዋለሁ፤ መበለቶችህም በእኔ ይታመኑ።

12እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ እነሆ፥ ጽዋውን ያልተገባቸው ሰዎች ጠጥተውታል፤ አንተም ሳትቀጣ ትቀራለህን? በእርግጥ ትጠጣለህ እንጂ ያለ ቅጣት አትቀርም።

13ባሶራ መደነቂያና መሰደቢያ መረገሚያም እንድትሆን በራሴ ምያለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ከተሞችዋም ሁሉ ለዘላለም ባድማ ይሆናሉ።

14ከእግዚአብሔር ዘንድ ወሬ ሰምቻለሁ በአሕዛብም መካከል፦ ተሰብሰቡ፥ በእርስዋም ላይ ኑ ለሰልፍም ተነሡ የሚል መልእክተኛ ተልኮአል።

15እነሆ፥ በአሕዛብ ዘንድ የተጠቃህ፥ በሰዎችም ዘንድ የተናቅህ አድርጌሃለሁ።

16በዓለት ንቃቃት ውስጥ የምትቀመጥ፥ የተራራውን ከፍታ የምትይዝ ሆይ፥ ድፍረትህና የልብህ ኵራት አታልለውሃል። ቤትህን ምንም እንደ ንስር ከፍ ብታደርግ፥ ከዚያ አወርድሃለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።

17ኤዶምያስም መደነቂያ ትሆናለች፥ የሚያልፍባትም ሁሉ ይደነቃል፥ ስለ መጣባትም መቅሠፍት ሁሉ ያፍዋጭባታል።

18ሰዶምና ገሞራ በእነርሱም አጠገብ የነበሩት ከተሞች እንደ ተገለበጡ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ እንዲሁ በዚያ ሰው አይቀመጥም የሰው ልጅም አይኖርባትም።

19እነሆ፥ ከእርስዋ ዘንድ በቶሎ አባርራቸዋለሁና በጠነከረው አምባ ላይ ከዮርዳኖስ ትዕቢት ውስጥ እንደ አንበሳ ይወጣል፤ የተመረጠውንም በእርስዋ ላይ እሾመዋለሁ፤ እንደ እኔ ያለ ማን ነው? ወይስ ለእኔ ጊዜ የሚወስን ማን ነው? ወይስ ፊቴን የሚቃወም እረኛ ማን ነው?

20ስለዚህ እግዚአብሔር በኤዶምያስ ላይ የመከረባትን ምክር፥ በቴማንም በሚኖሩ ሰዎች ላይ ያሰባትን አሳብ ስሙ፤ በእውነት የመንጋ ትንንሾች ይጐተታሉ፤ በእውነት ማደሪያቸውን ባድማ ያደርግባቸዋል።

21ከመውደቃቸው ድምፅ የተነሣ ምድር ተናወጠች፥ የጩኸታቸውም ድምፅ በኤርትራ ባሕር ተሰማ።

22እነሆ፥ እንደ ንስር ወጥቶ ይበራል ክንፉንም በባሶራ ላይ ይዘረጋል፥ በዚያም ቀን የኤዶምያስ ኃያላን ልብ ምጥ እንደ ያዛት ሴት ልብ ይሆናል።

23ስለ ደማስቆ፤ ክፉ ወሬ ሰምተዋልና ሐማትና አርፋድ አፈሩ ቀለጡም፤ በባሕርም ላይ ኅዘን አለ፥ ታርፍም ዘንድ አትችልም።

24ደማስቆ ደከመች ትሸሽም ዘንድ ዘወር አለች እንቅጥቅጥም ያዛት፥ እንደ ወላድም ሴት ጣርና ምጥ ያዛት።

25የተመሰገነችው ከተማ፥ የደስታዬ ከተማ፥ ሳትለቀቅ እንዴት ቀረች?

26ስለዚህ ጐበዛዝትዋ በአደባባይዋ ላይ ይወድቃሉ፥ በዚያም ቀን ሰልፈኞች ሁሉ ይጠፋሉ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።

27በደማስቆም ቅጥር ላይ እሳት አነድዳለሁ የወልደ አዴርንም አዳራሾች ትበላለች።

28የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ስለ መታ ስለ ቄዳርና ስለ አሶር መንግሥታት፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ተነሡ ወደ ቄዳርም ውጡ፥ የምሥራቅንም ልጆች አጥፉ።

29ድንኳናቸውንና መንጋቸውን ይወስዳሉ፤ መጋረጆቻቸውንና ዕቃቸውን ሁሉ ግመሎቻቸውንም ለራሳቸው ይወስዳሉ፥ በዙሪያቸውም ሁሉ ጥፋትን ጥሩባቸው።

30እናንተ በአሶር የምትኖሩ ሆይ፥ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ተማክሮባችኋልና፥ አሳብም አስቦባችኋልና ሽሹ ወደ ሩቅም ሂዱ በጥልቅም ውስጥ ተቀመጡ፥ ይላል እግዚአብሔር።

31ተነሡ፥ ዕርፊት ወዳለበት ተዘልሎም ወደ ተቀመጠው፥ ደጅና መወርወሪያ ወደሌለው ብቻውንም ወደ ተቀመጠው ሕዝብ ውጡ።

32ግመሎቻቸው ይበዘበዛሉ የእንስሶቻቸውም ብዛት ይማረካል፤ ጠጕራቸውንም በዙሪያ የሚላጩትን ሰዎች ወደ ነፋሳት ሁሉ እበትናቸዋለሁ፤ ከዳርቻቸውም ሁሉ ጥፋት አመጣባቸዋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።

33አሶርም የቀበሮ መኖሪያና የዘላለም ባድማ ትሆናለች፤ በዚያም ሰው አይኖርም፥ የሰው ልጅም አይቀመጥባትም።

34በይሁዳ ንጉሥ በሴዴቅያስ መንግሥት መጀመሪያ ስለ ኤላም ወደ ነቢዩ ወደ ኤርምያስ የመጣው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው።

35የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ዋና የኃይላቸው መሣሪያ የሆነውን የኤላምን ቀስት እሰብራለሁ።

36ከአራቱም ከሰማይ ማዕዘናት አራቱን ነፋሳት በኤላም ላይ አመጣለሁ፥ ወደ እነዚያም ነፋሳት ሁሉ እበትናቸዋለሁ፤ ከኤላም የተሰደዱ ሰዎች የማይደርሱበት ሕዝብ አይገኝም።

37በጠላቶቻቸውና ነፍሳቸውን በሚሹአት ፊት ኤላምን አስደነግጣለሁ፤ ክፉ ነገርን እርሱም ጽኑ ቍጣዬን አመጣባቸዋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ እስካጠፋቸውም ድረስ በኋላቸው ሰይፍ እሰድድባቸዋለሁ፤

38ዙፋኔንም በኤላም አኖራለሁ ከዚያም ንጉሡንና አለቆቹን አጠፋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።

39ነገር ግን በኋለኛው ዘመን የኤላምን ምርኮ እመልሳለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።

ማብራሪያ

፵፱፡፩-፮። በሰዎች መካከል ኃይል ብዙውን ጊዜ ጽድቅን ያሸንፋል፤ ይሁን እንጂ ያ ኃይል በጽድቅ በሚፈርድ ሁሉን በሚችለው አምላክ ቁጥጥር ሥር ይውላል። እንደ አሞናውያንም ሁሉ እጃቸውን የጣሉበትን ሁሉ የራሳቸው አድርገው የሚያስቡት ሰዎች የተሳሳቱ መሆናቸውን ያገኙታል። እግዚአብሔር ሰዎችን ለእያንዳንዱ የሐቀኝነት ማጣት ተጠያቂ ያደርጋል፣ በተለይም ደግሞ ችግረኞችን በሚመለከት።

49:7-22

ኤዶማውያን ለእግዚአብሔር እስራኤል የረጅም ጊዜ ጠላቶች ነበሩ። ነገር ግን ቀናቸው አሁን ደርሷል፤ ይህም የተነገረው እነርሱን ለማስጠንቀቅ ብቻ ሳይሆን፣ መከራቸው በእነርሱ የከበደባቸው የእግዚአብሔር እስራኤል ሲልም ነው። እንዲህም መለኮታዊ ፍርዶች ከብሔር ወደ ብሔር ይዞራሉ። ምድርም ሁከት ሞልቷታል፤ የመለኮታዊ በቀል አገልጋዮችንም ምንም ሊያመልጥ አይችልም። የእግዚአብሔር ጽድቅ በሰው ልጆች ግፍ መካከል መታየት ይገባዋል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV Concerning the Ammonites: This is what the Lord says: “Has Israel no sons? Has she no heirs? Why then has Molech taken … English BCV እግዚኣብሄር ብዛዕባ ደቂ ኣሞን ዝበሎ እዙይ እዩ፦ “ንእስራኤልዶ ውሉድ የብሉን እዩ? ወረስቲኸ የብሉን ድዩ? ስለ ምንታይ ድኣ እቲ ሚልኮም ንጉሶም ንጋድ ዝወረሳ? ህዝቡ ኸዓ ኣብ ከተማታቱ … ትግርኛ GAZBIB Waaqayyo waa'ee biyya Amooniif kanatti fufee kan jiru in dubbate; inni,“Israa'el ilmaan isa dhaalan hin qabuu ree” Maal… Afaan Oromoo BCV GIZ በእንተ ደቂቀ አሞን፤ ከመዝ ይቤ እግዚአብሔር፦ አልቦኑ ደቂቅ በውስተ እስራኤል፤ ወአልቦኑ ዘይወርስ እምኔሆሙ ከመ ይረስ ሞሎክ ለጋድ ወሕዝቡ ውስተ አህጉሪሁ ይንበር። giz GAZGAZ Waaqayyo waa'ee biyya Amooniif kanatti fufee kan jiru in dubbate; inni,“Israa'el ilmaan isa dhaalan hin qabuu ree” Maal… Afaan Oromoo BCV aksum እግዚኣብሄር ብዛዕባ ደቂ ኣሞን ዝበሎ እዙይ እዩ፦ “ንእስራኤልዶ ውሉድ የብሉን እዩ? ወረስቲኸ የብሉን ድዩ? ስለ ምንታይ ድኣ እቲ ሚልኮም ንጉሶም ንጋድ ዝወረሳ? ህዝቡ ኸዓ ኣብ ከተማታቱ … ትግርኛ AMHNIV ስለ አሞናውያን፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እስራኤል ወንዶች ልጆች አልወለደምን? ወራሾችስ የሉትምን? ታዲያ፣ ሚልኮምሸ ጋድን ለምን ወረሰ? የእርሱ ሰዎች ለምን በከተሞቿ ይኖራሉ? አማርኛ SWAHSUV Habari za wana wa Amoni. Bwana asema hivi, Je, Israeli hana wana? Je! Hana mrithi? Basi, mbona Malkamu anamiliki Gadi, … Kiswahili