ትንቢተ ኤርምያስ 49

AMHNIVአማርኛ39 ጥቅሶች8:13 አዳምጥ
አዳምጥ 8:13 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ስለ አሞናውያን፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እስራኤል ወንዶች ልጆች አልወለደምን? ወራሾችስ የሉትምን? ታዲያ፣ ሚልኮምሸ ጋድን ለምን ወረሰ? የእርሱ ሰዎች ለምን በከተሞቿ ይኖራሉ?

2ስለዚህ በአሞናውያን ከተማ በረባት ላይ፣ የጦርነት ውካታ ድምፅ፣ የሚሰማበት ጊዜ ይመጣል፤” ይላል እግዚአብሔር፤ “እርሷም የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች፤ በዙሪያዋ ያሉት መንደሮችም ይቃጠላሉ፤ እስራኤልም ከአገሯ ያስወጧትን፣ ከአገሯ ታስወጣለች፤” ይላል እግዚአብሔር፤

3ሐሴቦን ሆይ፤ ጋይ ጠፍታለችና ዋይ በይ፤ የራባት ሴቶች ልጆች ሆይ ጩኹ፤ ማቅ ለብሳችሁ አልቅሱ፤ ሚልኮም ከካህናቱና ከመኳንንቱ ጋር፣ ተማርኮ ይወሰዳልና፣ በቅጥር ውስጥ ወዲያ ወዲህ ተሯሯጡ።

4አንቺ ከዳተኛ ልጅ ሆይ፣ በሸለቆችሽ ለምን ትመኪያለሽ? ለምንስ በፍሬያማ ሸለቆሽ ትኵራሪያለሽ? በብልጽግናሽ ተማምነሽ፣ ‘ማን ሊነካኝ ይችላል?’ ትያለሽ።

5በዙሪያሽ ካሉት ሁሉ ዘንድ፣ ሽብር አመጣብሻለሁ፤” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ “እያንዳንዳችሁ ትሰደዳላችሁ፤ በሽሽት ላይ ያሉትንም የሚሰበስብ አይገኝም።

6“ከዚያ በኋላ ግን፣ የአሞናውያንን ምርኮ እመልሳለሁ፣” ይላል እግዚአብሔር።

7ስለ ኤዶም፤ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ጥበብ ከቴማን ጠፍቶአልን? ምክር ከአስተዋዮች ርቆአልን? ጥበባቸውስ ተሟጧልን?

8ዔሳውን በምቀጣ ጊዜ፣ ጥፋት ስለማመጣበት፣ እናንተ በድዳን የምትኖሩ ሆይ፤ ወደ ኋላ ተመልሳችሁ ሽሹ፤ ጥልቅ ጒድጓድ ውስጥ ተደበቁ።

9ወይን ለቃሚዎች ወዳንተ ቢመጡ፣ ጥቂት ወይን አያስቀሩምን? ሌቦችስ በሌሊት ቢመጡ፣ የሚሰርቁት የሚፈልጉትን ብቻ አይደለምን?

10እኔ ግን ዔሳውን አራቍተዋለሁ፤ መደበቅም እንዳይችል፣ መሸሸጊያ ስፍራዎቹን እገልጣለሁ፤ ልጆቹ፣ ዘመዶቹና ጎረቤቶቹ ይጠፋሉ፤ እርሱም ራሱ አይኖርም።

11ወላጆች የሌላቸውን ልጆችህን ተዋቸው፤ እኔ ለሕይወታቸው እጠነቀቃለሁ፤ መበለቶቻችሁም በእኔ ይታመኑ።”

12እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ከጽዋው መጠጣት የማይገባቸው ሊጠጡ ግድ ከሆነ፣ አንተ እንዴት ሳትቀጣ ትቀራለህ? መቀጣትህ አይቀርም፤ መጠጣት ይገባሃል።

13ባሶራ ፈራርሳ የድንጋጤ፣ የመዘባበቻና የርግማን ምልክት እንደምትሆን በራሴ ምያለሁ” ይላል እግዚአብሔር፤ “ከተሞቿም ሁሉ ለዘላለም ባድማ ይሆናሉ።”

14ከእግዚአብሔር ዘንድ መልእክት ሰምቻለሁ፤ “እርሷን ለመውጋት ተሰብሰቡ፤ ለጦርነትም ውጡ” የሚል መልእክተኛ ወደ ሕዝቦች ተልኮአል።

15“እነሆ፤ በሕዝቦች መካከል ታናሽ፣ በሰዎችም ዘንድ የተናቅህ አደርግሃለሁ።

16አንተ በዐለት ንቃቃት ውስጥ የምትኖር፣ የተራራውንም ከፍታ የያዝህ ሆይ፤ የምትነዛው ሽብር፣ የልብህም ኵራት አታሎሃል፤ መኖሪያህን እንደ ንስር በከፍታ ቦታ ብትሠራም፣ ከዚያ ወደ ታች እጥልሃለሁ፤” ይላል እግዚአብሔር።

17“ኤዶም የድንጋጤ ምልክት ትሆናለች፤ ከቍስሎቿም ሁሉ የተነሣ፣ በዚያ የሚያልፍ ሁሉ በመደነቅ ያላግጥባታል።”

18በዙሪያቸው ካሉት ከተሞች ጋር፣ ሰዶምና ገሞራ እንደ ተገለበጡ፣” ይላል እግዚአብሔር፤ እንዲሁ ማንም በዚያ አይኖርም፤ አንድም ሰው አይቀመጥባትም።

19“አንበሳ ከዮርዳኖስ ደኖች፣ ወደ ግጦሽ ሜዳ ብቅ እንደሚል፣ እኔም በኤዶም ላይ ድንገት እወጣለሁ፤ ከምድሩም አባርረዋለሁ። የመረጥሁትን በእርሱ ላይ እሾማለሁ፤ እንደ እኔ ያለ ማን ነው? ማንስ ሊገዳደረኝ ይችላል? የትኛውስ እረኛ ሊቋቋመኝ ይችላል?

20ስለዚህ እግዚአብሔር በኤዶም ላይ ያለውን ዕቅድ፣ በቴማን በሚኖሩትም ላይ ያሰበውን አሳብ ስሙ፤ ታናናሹ መንጋ ተጐትቶ ይወሰዳል፤ በእነርሱም ምክንያት መሰማሪያቸውን ፈጽሞ ያጠፋል።

21በውድቀታቸው ድምፅ ምድር ትናወጣለች፤ ጩኸታቸውም እስከ ቀይ ባሕር ያስተጋባል።

22እነሆ፤ እንደ ንስር ተወርውሮ ይወርድባታል፤ ክንፎቹንም በባሶራ ላይ ይዘረጋል፤ በዚያን ቀን የኤዶም ጦረኞች ልብ፣ በምጥ እንደ ተያዘች ሴት ልብ ይሆናል።

23ስለ ደማስቆ፤ “ክፉ ወሬ ሰምተዋልና፣ ሐማትና አርፋድ ደንግጠዋል፤ እንደ ተናወጠ ባሕርም ታውከዋል፤ ልባቸውም ቀልጦአል።

24ደማስቆ ተዳከመች፤ ትሸሽም ዘንድ ወደ ኋላ ተመለሰች፤ ብርክ ያዛት፣ ምጥ እንደ ያዛት ሴት፣ ጭንቅና መከራ ዋጣት።

25ደስ የምሰኝባት፣ የታወቀችው ከተማ እንዴት ተተወች?

26በርግጥ ወንዶች ወጣቶቿ በየአደባባዩ ይረግፋሉ፤ በዚያ ቀን ወታደሮቿ ሁሉ ይወድቃሉ፤” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤

27“በደማስቆ ቅጥር ላይ እሳት እለኵሳለሁ፤ የወልደ አዴርንም ዐምባ ይበላል።”

28የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ስለ ወጋቸው ስለ ቄዳርና ስለ ሐጾር መንግሥታት የተነገረ፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ተነሡ፣ ቄዳርን ውጉ፤ የምሥራቅንም ሕዝብ ደምስሱ።

29ድንኳኖቻቸውና መንጎቻቸው ይወሰዳሉ፤ መጠለያቸውና ግመሎቻቸው ሳይቀሩ፣ ከነዕቃዎቸው ይነጠቃሉ፤ ሰዎች፣ ‘ሽብር በሽብር ላይ መጥቶባቸዋል፤’ እያሉ ይጮኹባቸዋል።

30በሐጾር የምትኖሩ ሆይ፣ በጥድፊያ ሽሹ በጥልቅ ጒድጓድ ተሸሸጉ፤” ይላል እግዚአብሔር፤ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር በእናንተ ላይ መክሮአልና፣ ወረራም ዶልቶባችኋል።

31“ተነሡ፣ ተዘልሎ የተቀመጠውን፣ በራሱ ተማምኖ የሚኖረውን ሕዝብ ውጉ፤” ይላል እግዚአብሔር፤ “መዝጊያና መቀርቀሪያ በሌለው፤ ለብቻው በሚኖረው ሕዝብ ላይ ዝመቱ።

32ግመሎቻቸው ይዘረፋሉ፤ ከብቶቻቸውንም አንጋግተው ይነዱባቸዋል፤ ጠጒሩን የሚቀነብበውን ወገን እበትናለሁ ከየአቅጣጫው መዓት ይላል እግዚአብሔር፤

33“ሐጾር የቀበሮዎች መፈንጫ፣ ለዘላለም ባድማ ትሆናለች፤ ማንም በዚያ አይኖርም፤ የሚቀመጥባትም አይገኝም።”

34በይሁዳ ንጉሥ በሴዴቅያስ ዘመነ መንግሥት መጀመሪያ ላይ ወደ ነቢዩ ወደ ኤርምያስ የመጣው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው፤

35የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እነሆ፤ የኀያልነቷን መሠረት፣ የኤላምን ቀስት እሰብራለሁ።

36ከአራቱ የሰማይ ማእዘናት፣ በኤላም ላይ አራቱን ነፋሳት አመጣለሁ፤ ወደ አራቱም ነፋሳት እበትናቸዋለሁ፤ ከኤላም የሚማረኩት የማይደርሱበት፣ አገር አይገኝም።

37ነፍሳቸውን በሚሹ ጠላቶቻቸው ፊት፣ ኤላምን አርበደብዳለሁ፤ በላያቸው ላይ መዓትን፣ ይኸውም ቍጣዬን አመጣባቸዋለሁ፤” ይላል እግዚአብሔር፤ “ፈጽሜ አስካጠፋቸውም ድረስ፣ በሰይፍ አሳድዳቸዋለሁ።

38ዙፋኔን በኤላም እዘረጋለሁ፤ ነገሥታቷንና መኳንንቷን አጠፋለሁ፤” ይላል እግዚአብሔር፤

39“ነገር ግን የኋላ ኋላ፣ የኤላምን ምርኮ እመልሳለሁ፤” ይላል እግዚአብሔር።

ማብራሪያ

፵፱፡፩-፮። በሰዎች መካከል ኃይል ብዙውን ጊዜ ጽድቅን ያሸንፋል፤ ይሁን እንጂ ያ ኃይል በጽድቅ በሚፈርድ ሁሉን በሚችለው አምላክ ቁጥጥር ሥር ይውላል። እንደ አሞናውያንም ሁሉ እጃቸውን የጣሉበትን ሁሉ የራሳቸው አድርገው የሚያስቡት ሰዎች የተሳሳቱ መሆናቸውን ያገኙታል። እግዚአብሔር ሰዎችን ለእያንዳንዱ የሐቀኝነት ማጣት ተጠያቂ ያደርጋል፣ በተለይም ደግሞ ችግረኞችን በሚመለከት።

49:7-22

ኤዶማውያን ለእግዚአብሔር እስራኤል የረጅም ጊዜ ጠላቶች ነበሩ። ነገር ግን ቀናቸው አሁን ደርሷል፤ ይህም የተነገረው እነርሱን ለማስጠንቀቅ ብቻ ሳይሆን፣ መከራቸው በእነርሱ የከበደባቸው የእግዚአብሔር እስራኤል ሲልም ነው። እንዲህም መለኮታዊ ፍርዶች ከብሔር ወደ ብሔር ይዞራሉ። ምድርም ሁከት ሞልቷታል፤ የመለኮታዊ በቀል አገልጋዮችንም ምንም ሊያመልጥ አይችልም። የእግዚአብሔር ጽድቅ በሰው ልጆች ግፍ መካከል መታየት ይገባዋል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG ስለ አሞን ልጆች፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ለእስራኤል ልጆች የሉትምን? ወይስ ወራሽ የለውምን? ስለ ምን ሚልኮም ጋድን ወረሰ? ሕዝቡስ በከተሞቹ ላይ ስለ ምን ተቀመጠ? አማርኛ ENGNIV Concerning the Ammonites: This is what the Lord says: “Has Israel no sons? Has she no heirs? Why then has Molech taken … English BCV እግዚኣብሄር ብዛዕባ ደቂ ኣሞን ዝበሎ እዙይ እዩ፦ “ንእስራኤልዶ ውሉድ የብሉን እዩ? ወረስቲኸ የብሉን ድዩ? ስለ ምንታይ ድኣ እቲ ሚልኮም ንጉሶም ንጋድ ዝወረሳ? ህዝቡ ኸዓ ኣብ ከተማታቱ … ትግርኛ GAZBIB Waaqayyo waa'ee biyya Amooniif kanatti fufee kan jiru in dubbate; inni,“Israa'el ilmaan isa dhaalan hin qabuu ree” Maal… Afaan Oromoo BCV GIZ በእንተ ደቂቀ አሞን፤ ከመዝ ይቤ እግዚአብሔር፦ አልቦኑ ደቂቅ በውስተ እስራኤል፤ ወአልቦኑ ዘይወርስ እምኔሆሙ ከመ ይረስ ሞሎክ ለጋድ ወሕዝቡ ውስተ አህጉሪሁ ይንበር። giz GAZGAZ Waaqayyo waa'ee biyya Amooniif kanatti fufee kan jiru in dubbate; inni,“Israa'el ilmaan isa dhaalan hin qabuu ree” Maal… Afaan Oromoo BCV aksum እግዚኣብሄር ብዛዕባ ደቂ ኣሞን ዝበሎ እዙይ እዩ፦ “ንእስራኤልዶ ውሉድ የብሉን እዩ? ወረስቲኸ የብሉን ድዩ? ስለ ምንታይ ድኣ እቲ ሚልኮም ንጉሶም ንጋድ ዝወረሳ? ህዝቡ ኸዓ ኣብ ከተማታቱ … ትግርኛ SWAHSUV Habari za wana wa Amoni. Bwana asema hivi, Je, Israeli hana wana? Je! Hana mrithi? Basi, mbona Malkamu anamiliki Gadi, … Kiswahili