ትንቢተ ኤርምያስ 48

AMHNIVአማርኛ47 ጥቅሶች8:27 አዳምጥ
አዳምጥ 8:27 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ስለ ሞዓብ፤ የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ናባው ትጠፋለችና ወዮላት፤ ቂርያታይም ትዋረዳለች፤ ትያዛለችም፤ ምሽጎች ይደፈራሉ፤ ይፈራርሳሉም።

2ከእንግዲህ ሞዓብ አትከበርም፤ ሰዎች በሐሴቦን ተቀምጠው፣ ‘ኑ ያቺን አገር እናጥፋት’ ብለው ይዶልቱባታል። መድሜን ሆይ፤ አንቺም ደግሞ ጸጥ ትደረጊያለሽ፤ ሰይፍም ያሳድድሻል።

3ከሖሮናይም የሚወጣውን ጩኸት፣ የመውደምና የታላቅ ጥፋት ድምፅ ስሙ!

4ሞዓብ ትሰበራለች፤ ልጆቿም ጩኸት ያሰማሉ።

5ክፉኛ እያለቀሱ፣ ወደ ሉሒት ሽቅብ ይወጣሉ፤ ስለ ደረሰባቸውም ጥፋት መራራ ጩኸት እያሰሙ፣ ወደ ሖርናይም ቍልቍል ይወርዳሉ።

6ሽሹ፤ ሕይወታችሁንም አትርፉ! በምድረ በዳ እንዳለ ቍጥቋጦ ሁኑ።

7በድርጊታችሁና በብልጽግናችሁ ስለምትታመኑ፣ እናንተም ትማረካላችሁ፣ ካሞሽም ከካህናቱና ከመኳንንቱ ጋር፣ በምርኮ ይወሰዳል።

8በእያንዳንዱ ከተማ ላይ አጥፊ ይመጣል፤ አንድም ከተማ አያመልጥም። እግዚአብሔር ተናግሮአልና፣ ሸለቆው ይጠፋል፤ ዐምባውም ይፈርሳል።

9በራ እንድታመልጥ፣ ለሞዓብ ክንፍ ስጧት፤ ከተሞቿም ምንም እስከማይኖርባቸው ድረስ፣ ባድማ ይሆናሉ።

10“የእግዚአብሔርን ሥራ በቸልታ የሚያከናውን ርጉም ይሁን፤ ሰይፉን ደም ከማፍሰስ የሚከላከል የተረገመ ይሁን፤

11“ሞዓብ በአምቡላው ላይ እንዳረፈ የወይን ጠጅ፣ ከልጅነት ጀምሮ የተረጋጋ ነበረ፤ ከዕቃ ወደ ዕቃ አልተገላበጠም፤ በምርኮም አልተወሰደም፤ ቃናው እንዳለ ነው፤ መዐዛውም አልተለወጠም።

12ስለዚህ ዕቃውን የሚገለብጡ ሰዎችን፤ የምልክበት ጊዜ ይመጣል፤” ይላል እግዚአብሔር። “እነርሱም ይደፉታል፤ ዕቃውን ባዶ ያስቀራሉ፤ ማንቆርቆሪያዎቹንም ይሰባብራሉ።

13የእስራኤል ቤት፤ በቤቴል ታምኖ እንዳፈረ ሁሉ፣ ሞዓብም በካሞሽ ያፍራል።

14“እናንተ፣ ‘እኛ ተዋጊዎች ነን፤ በጦርነትም ብርቱ ነን’ ልትሉ እንዴት ቻላችሁ?

15ሞዓብ ትጠፋለች፤ ከተሞቿም ይወረራሉ፤ ምርጥ ወጣቶቿም ወደ መታረድ ይወርዳሉ፤” ይላል ስሙ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር የሆነው ንጉሥ፤

16“የሞዓብ ውድቀት ተቃርቦአል፤ ጥፋቱም ፈጥኖ ይመጣበታል።

17በዙሪያው የምትኖሩ ሁሉ፤ ዝናውን የምታውቁ ሁሉ አልቅሱለት፤ ‘ብርቱው ከዘራ፣ የከበረው በትር እንዴት ሊሰበር ቻለ’ በሉ።

18“ሞዓብን የሚያጠፋ፣ በአንቺ ላይ ይመጣልና፤ የተመሸጉ ከተሞችሽንም ያጠፋልና፤ አንቺ የዲቦን ሴት ልጅ ሆይ፣ ከክብርሽ ውረጂ፣ በደረቅም መሬት ተቀመጪ።

19አንቺ በአሮዔር የምትኖሪ ሆይ፤ በመንገድ አጠገብ ቆመሽ ተመልከቺ፤ የሚሸሸውን ወንድ፣ የምታመልጠውንም ሴት፣ ምን ተፈጠረ?’ ብለሽ ጠይቂ።

20ሞዓብ በመፍረሱ ተዋርዷል፤ ዋይ በሉ፤ ጩኹ፤ የሞዓብን መደምሰስ፣ በአርኖን አጠገብ አስታውቁ።

21ፍርድ በዐምባው ምድር፦ በሖሎን፣ በያሳና በሜፍዓት ላይ፣

22በዲቦን፣ በናባውና በቤት ዲብላታይም ላይ፣

23በቂርያታይም፣ በቤትጋሙልና በቤትምዖን ላይ፣

24በቂርዮትና በባሶራ ላይ፤ በሩቅና በቅርብ፣ ባሉት በሞዓብ ከተሞች ሁሉ ላይ መጥቶአል።

25የሞዓብ ቀንድ ተቈርጦአል፤ እጁም ተሰባብሮአል፤” ይላል እግዚአብሔር።

26“እግዚአብሔርን ንቆአልና፣ ሞዓብን በመጠጥ አስክሩት። ሞዓብ በትፋቱ ላይ ይንከባለል፤ ለመዘባበቻም ይሁን።

27በእስራኤል ላይ ስታላግጥ አልነበረምን? ስለ እርሷ በተናገርህ ቍጥር፣ እያቃለልሃት ራስህን የምትነቀንቀውስ፣ ከሌቦች ጋር ስትሰርቅ ተይዛለችን?

28እናንተ በሞዓብ የምትኖሩ ሆይ፤ ከከተማ ወጥታችሁ በዐለት መካከል ኑሩ፤ በገደል አፋፍ ላይ ጐጆዋን እንደምትሠራ፣ እንደ ርግብ ሁኑ።

29“ስለ ሞዓብ ትዕቢት፣ ስለ እብሪቱና ስለ ኵራቱ፣ ስለ ትምክሕቱና ስለ መጓደዱ፣ ስለ ልቡም ማበጥ ሰምተናል።

30መዳፉን ዐውቃለሁ፤ ነገር ግን ከንቱ ነው፤” ይላል እግዚአብሔር። “ጒራውም ፋይዳ አይኖረውም።

31ስለዚህ ለሞዓብ አለቅሳለሁ፤ ለሞዓብ ምድር ሁሉ ዋይ እላለሁ፤ ለቂርሔሬስ ሰዎችም የልቅሶ ድምፅ አሰማለሁ።

32የሴባማ ወይን ሆይ፤ ለኢያዜር ካለቀስሁት እንኳ ይልቅ አለቅስልሻለሁ፤ ቅርንጫፎችሽ እስከ ባሕሩ ተዘርግተዋል፤ እስከ ኢያዜርም ደርሰዋል፤ ለመከር በደረሰው ፍሬሽና በወይንሽ ላይ፣ አጥፊው መጥቶአል።

33ከሞዓብ የአትክልት ቦታና እርሻ፣ ሐሤትና ደስታ ርቆአል፤ የወይን ጠጅ ከመጭመቂያው እንዳይወርድ አድርቄዋለሁ፤ በእልልታ የሚጨምቀውም አይገኝም፤ በዚያ ድምፅ ቢሰማም፣ የእልልታ ድምፅ አይደለም።

34“ከሐሴቦን እስከ ኤልያሊና እስከ ያሀጽ፣ ከዞዓር እስከ ሖሮናይም፣ እስከ ዔግላት ሺሊሺያ ድረስ፣ ጩኸታቸው ከፍ ብሎ ይሰማል፤ የኔሞሬም ውሃ እንኳ ደርቆአልና።

35በመስገጃ ኰረብቶች ላይ የሚሠዉትን፣ ለአማልክታቸው የሚያጥኑትን፣ ከሞዓብ አጠፋለሁ፤” ይላል እግዚአብሔር፤

36“ስለዚህ ልቤ ለሞዓብ እንደ ዋሽንት ያንጐራጒራል፤ ለቂርሔሬስ ሰዎችም እንደ ዋሽንት ያንጐራጒራል። ያከማቹት ንብረት ጠፍቶአልና።

37የእያንዳንዱ ሰው ራስ፣ ጢምም ሁሉ ተላጭቶአል፤ እጅ ሁሉ ተቸፍችፎአል፤ ወገብም ሁሉ ማቅ ታጥቆአል።

38በሞዓብ ቤቶች ጣራ ሁሉ ላይ፤፣ በሕዝብም አደባባዮች፣ ሐዘን እንጂ ሌላ የለም፤ እንደማይፈለግ እንስራ፣ ሞዓብን ሰብሬአለሁና፤” ይላል እግዚአብሔር።

39“እንዴት ተንኰታኰተ! ምንኛስ አለቀሱ! ሞዓብ እንዴት ዐፍሮ ጀርባውን አዞረ! ሞዓብ የመሰደቢያ፣ በዙሪያው ላሉትም ሁሉ የሽብር ምልክት ሆነ።”

40እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እነሆ፤ እንደ ንስር ተወርውሮ ይወርድበታል፤ ክንፎቹንም በሞዓብ ላይ ይዘረጋል።

41ከተሞቹ ይወረራሉ፤ ምሽጎቹም ይያዛሉ፤ በዚያን ቀን የሞዓብ ጦረኞች ልብ፣ በምጥ እንደ ተያዘች ሴት ልብ ይሆናል።

42ሞዓብ እግዚአብሔርን አቃልሎአልና ይጠፋል፤ መንግሥትነቱም ይቀራል።

43የሞዓብ ሕዝብ ሆይ፤ ሽብርና ጒድጓድ፣ ወጥመድም ይጠብቅሃል፤” ይላል እግዚአብሔር።

44“ከሽብር የሚሸሽ ሁሉ፣ ጒድጓድ ውስጥ ይገባል፤ ከጒድጓዱም የሚወጣ፣ በወጥመድ ይያዛል፤ በሞዓብ ላይ፣ የቅጣቱን ዓመት አመጣለሁና፣” ይላል እግዚአብሔር፤

45“የሞዓብን ግንባር፣ የደንፊዎችን ዐናት የሚያቃጥል፣ እሳት ከሐሴቦን፣ ነበልባል ከሴዎን ቤት ወጥቶአልና፤ ኰብላዮች በሐሴቦን ጥላ ሥር፣ ተስፋ ቈርጠው ቆመዋል።

46ሞዓብ ሆይ፤ ወዮልህ! የካሞሽ ሕዝብ ተደምስሶአል፤ ወንዶች ልጆችህ በምርኮ ተወስደዋል፤ ሴቶች ልጆችህም ተግዘዋል።

47“ነገር ግን የኋላ ኋላ፣ የሞዓብን ምርኮ እመልሳለሁ፤” ይላል እግዚአብሔር። በሞዓብ ላይ የተወሰነው ፍርድ ይኸው ነው።

ማብራሪያ

48:1-13. ከለዳውያን ሞዓባውያንን ሊያጠፉ ነው። የሰዎችን ሕይወት መዳንና የነፍሶቻቸውን መዳን እንድንፈልግ እንጂ ደማቸውን እንድናፈስ እንዳልተጠየቅን ልናመሰግን ይገባል። ነገር ግን ይህንን አስደሳች ሥራ በማታለል ብናደርግ፣ ይበልጥ መመካከሪያ የለንም። ከተሞች ፍርስርስ ይሆናሉ፤ አገሪቱም ትባክናለች። ታላቅ ሐዘን ይኖራል። ታላቅ ሽሽትም ይኖራል። ኃጢአተኞች ክንፍ ቢኖራቸው እንኳ፣ ከመለኮታዊ ቁጣ እጅ ማምለጥ አይችሉም ነበር። ባልተጸጸቱ ኃጢአት የሚጸኑ ብዙዎች አሉ፤ ይሁን እንጂ ለረጅም ጊዜ የውጭ ብልጽግናን ያጣጥማሉ። ለረጅም ጊዜ የተበላሹና ያልተለወጡ፣ በብልጽግና ውስጥ ደኅንነት የተሰማቸውና ሥጋዊ ምኞትን የተከተሉ ነበሩ።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG ስለ ሞዓብ፤ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ናባው ጠፍታለችና ወዮላት! ቂርያታይም አፍራለች ተይዛማለች፤ ሚሥጋብ አፍራለች ደንግጣማለች። አማርኛ ENGNIV Concerning Moab: This is what the Lord Almighty, the God of Israel, says: “Woe to Nebo, for it will be ruined. Kiriatha… English BCV ጐይታ ሰራዊት ኣምላኽ እስራኤል እግዚኣብሄር፥ ብዛዕባ ሞኣብ ከምዙይ ይብል፦ ናባው ጠፊኣ እያ እሞ፥ ወይለኣ! ቅርያታይም ነወረት፤ ተትሓዘትውን፤ ሚስጋብ ሓፈረት፤ ደንገፀትውን። ትግርኛ GAZBIB Waaqayyo gooftaan maccaa, Waaqayyo inni kan Israa'el waa'ee biyya Mo'aab kanatti fufe kan jiru in dubbate; inni,“Mandar… Afaan Oromoo BCV GIZ ነገር ዘበእንተ ሞአብ፤ ከመዝ ይቤ እግዚአብሔር ፀባዖት እምላከ እስራኤል፦ ወይሌ ላዕለ ናባው እስመ ጠፍአት ወተኃፍረት ወተነሥአት ቀርያታርም ወተኀፍረ ፀወና ወተመውዐ። giz GAZGAZ Waaqayyo gooftaan maccaa, Waaqayyo inni kan Israa'el waa'ee biyya Mo'aab kanatti fufe kan jiru in dubbate; inni,“Mandar… Afaan Oromoo BCV aksum ጐይታ ሰራዊት ኣምላኽ እስራኤል እግዚኣብሄር፥ ብዛዕባ ሞኣብ ከምዙይ ይብል፦ ናባው ጠፊኣ እያ እሞ፥ ወይለኣ! ቅርያታይም ነወረት፤ ተትሓዘትውን፤ ሚስጋብ ሓፈረት፤ ደንገፀትውን። ትግርኛ SWAHSUV Habari za Moabu. Bwana wa majeshi, Mungu wa Israeli, asema hivi, Ole wake Nebo! Kwa maana umeharibika; Kiriathaimu umea… Kiswahili