ትንቢተ ኤርምያስ 43

AMHNIVአማርኛ13 ጥቅሶች2:59 አዳምጥ
አዳምጥ 2:59 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ኤርምያስ፣ እግዚአብሔር ለእነርሱ እንዲነግራቸው የላከውን የአምላካቸውን የእግዚአብሔርን ቃል ሁሉ ለሕዝቡ ተናግሮ በጨረሰ ጊዜ፣

2የሆሽያ ልጅ ዓዛርያስ፣ የቃሬያ ልጅ ዮሐናንና ትዕቢተኞች የሆኑ ሰዎች ሁሉ ኤርምያስን እንዲህ አሉት፤ “ትዋሻለህ! አምላካችን እግዚአብሔር፣ ‘እዚያ ለመኖር ወደ ግብፅ አትሂዱ ብለህ ንገራቸው’ ብሎ አልላከህም፤

3ነገር ግን ባቢሎናውያን እንዲገድሉን ወይም ማርከው ወደ ባቢሎን እንዲወስዱን ለእነርሱ አሳልፈህ ትሰጠን ዘንድ የኔርያ ልጅ ባሮክ በእኛ ላይ አነሣሥቶሃል።”

4ስለዚህ የቃሬያ ልጅ ዮሐናንና፣ የጦር መኰንኖቹ ሁሉ እንዲሁም ሕዝቡ በሙሉ እግዚአብሔር በይሁዳ ምድር እንዲቀመጡ ያዘዛቸውን ቃል አልሰሙም።

5ነገር ግን፣ የቃሪያ ልጅ ዮሐናንና የጦር መኮንኖቹ ሁሉ፣ በይሁዳ ምድር ለመቀመጥ ከተበተኑበት ከአሕዛብ ሁሉ መካከል የተመለሱትን የይሁዳን ቅሬታዎች ሁሉ ይዘው ሄዱ፤

6በተጨማሪም ወንዶችን፣ ሴቶችንና ሕፃናትን እንዲሁም የክብር ዘበኞች አዛዥ ናቡዘረዳን በአኪቃም ልጅ በጎዶልያስ እጅ የተዋቸውን የንጉሡን ሴቶች ልጆች፣ ነቢዩ ኤርምያስንና የኔርያን ልጅ ባሮክን ወሰዷቸው፤

7የእግዚአብሔርንም ቃል ባለመታዘዝ ወደ ግብፅ ገቡ፤ ዘልቀውም እስከ ጣፍናስ ድረስ ሄዱ።

8በጣፍናስም የእግዚአብሔር ቃል ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ፤

9“ትልልቅ ድንጋዮች ውሰድና በጣፍናስ ባለው የፈርዖን ቤተ መንግሥት በር ላይ የይሁዳ ሰዎች እያዩ በሸክላ ጡብ ወለል ውስጥ ቅበራቸው፤

10እንዲህም በላቸው፤ ‘የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ አገልጋዬን የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን እንዲመጣ አደርጋለሁ፤ ዙፋኑንም እዚህ በቀበርኋቸው ድንጋዮች ላይ እዘረጋለሁ፤ የንጉሥ ድንኳኑንም በላያቸው ይተክላል።

11እርሱም መጥቶ ግብፅን ይወጋል፤ ሞት የሚገባቸውን ለሞት፣ ለምርኮ የተመደቡትን ወደ ምርኮ፣ ለሰይፍ የተዳረጉትን ለሰይፍ አሳልፎ ይሰጣል።

12እርሱ የግብፅ አማልክት ቤተ ጣዖቶች ላይ እሳት ይለኵሳል፤ ያቃጥላቸዋልም፣ አማልክታቸውንም ማርኮ ይወስዳል። እረኛ ልብሱን እንደሚጐናጸፍ የግብፅን ምድር ተጐናጽፎ ከዚያ በሰላም ይሄዳል።

13በግብፅ ምድር የሚገኙትን የፀሓይ አምላክ ቤተ ጣዖት ሐውልቶች ይሰባብራል፤ የግብፅንም አማልክት ቤተ ጣዖቶች በእሳት ያቃጥላል።

ማብራሪያ

43:1-7 ጠብ ከእግዚአብሔርም ከሰውም ጋር የሚመጣው በኩራት ብቻ ነው። እነርሱም የራሳቸውን ጥበብ ለእግዚአብሔር ከተገለጠው ፈቃድ አስበልጠው መርጠዋል። ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን የእግዚአብሔር ቃል አይደለም ይላሉ፣ ምክንያቱም ራሳቸውን ለመጽሐፍ ቅዱስ ሕግጋት ላለማስገዛት ወስነዋልና። ሰዎች በኃጢአት ለመጽናት ሲወስኑ፣ መልካም የሆኑ ሥራዎችን ለመጥፎ ዓላማ ይፈርጃሉ።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG የአምላካቸውን የእግዚአብሔርን ቃል ሁሉ፥ ለእነርሱ አምላካቸው እግዚአብሔር የላከውን ይህን ቃል ሁሉ፥ ኤርምያስ ለሕዝቡ ሁሉ መናገርን በፈጸመ ጊዜ፥ አማርኛ ENGNIV When Jeremiah finished telling the people all the words of the Lord their God–everything the Lord had sent him to tell … English BCV ኤርሚያስ፥ እግዚኣብሄር ኣምላኾም ንኣኣቶም ክነግሮም ዝለኣኾ ንዅሉ ቓል እግዚኣብሄር ኣምላኾም ነቶም ህዝቢ ተናጊሩ ምስ ወድአ፥ ትግርኛ GAZBIB Ani Ermiyaas wanta Waaqayyo gooftaan isaanii jara kanatti akkan himuuf na abboome hundumaa guutummaa sabaatti himee erg… Afaan Oromoo BCV GIZ ወኮነ ሶበ አኅለቀ ኤርምያስ እንዘ ይነግር ለኵሉ ሕዝብ ኵሎ ቃለ እግዚአብሔር በከመ ፈነዎ እግዚአብሔር አምላኮሙ ኀቤሆሙ ዘንተ ኵሉ ቃላተ፤ giz GAZGAZ Ani Ermiyaas wanta Waaqayyo gooftaan isaanii jara kanatti akkan himuuf na abboome hundumaa guutummaa sabaatti himee erg… Afaan Oromoo BCV aksum ኤርሚያስ፥ እግዚኣብሄር ኣምላኾም ንኣኣቶም ክነግሮም ዝለኣኾ ንዅሉ ቓል እግዚኣብሄር ኣምላኾም ነቶም ህዝቢ ተናጊሩ ምስ ወድአ፥ ትግርኛ SWAHSUV Ikawa Yeremia alipokwisha kuwaambia watu wote maneno yote ya Bwana, Mungu wao, ambayo Bwana, Mungu wao, amemtuma kwao, … Kiswahili