ትንቢተ ኤርምያስ 25

AMHNIVአማርኛ38 ጥቅሶች7:39 አዳምጥ
አዳምጥ 7:39 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1የይሁዳ ንጉሥ የኢዮስያስ ልጅ ኢዮአቄም በነገሠ በአራተኛው ዓመት፣ ይህም ማለት በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር ዘመነ መንግሥት በመጀመሪያው ዓመት፣ ስለ ይሁዳ ሕዝብ ሁሉ ለኤርምያስ ቃል መጣለት፤

2ስለዚህ ነቢዩ ኤርምያስ ለይሁዳ ሕዝብ ሁሉ፣ በኢየሩሳሌም ለሚኖሩትም ሁሉ እንዲህ ሲል ተናገረ፦

3የይሁዳ ንጉሥ የአሞን ልጅ ኢዮስያስ ከነገሠበት ከዐሥራ ሦስተኛው ዓመት ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ሃያ ሦስት ዓመት ሙሉ የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ መጣ፤ ደጋግሜም ነገርኋችሁ፤ እናንተ ግን አልሰማችሁም።

4እግዚአብሔር አገልጋዮቹን ነቢያትን ሁሉ ደጋግሞ ወደ እናንተ ላከ፤ ሆኖም አልሰማችሁም፤ ትኵረትም አልሰጣችሁትም።

5እነርሱም እንዲህ አሉ፤ “እንግዲህ ሁላችሁ ከክፉ መንገዳችሁና ከክፉ ሥራችሁ ተመለሱ፤ እግዚአብሔር ለእናንተና ለአባቶቻችሁ በሰጣት ምድር ለዘላለም ትቀመጣላችሁ።

6ታገለግሏቸውና ታመልኳቸው ዘንድ ሌሎቹን አማልክት አትከተሉ፤ እጃችሁ በሠራው ነገር አታስቈጡኝ፤ እኔም ክፉ አላደርግባችሁም።”

7“ነገር ግን አልሰማችሁኝም” ይላል እግዚአብሔር፤ ኋእጃችሁ በሠራው ነገር አስቈጣችሁኝ፤ በራሳችሁም ላይ ክፉ ነገር አመጣችሁ።”

8ስለዚህ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ቃሌን ስላልሰማችሁ፣

9የሰሜንን ሕዝብ ሁሉ፣ አገልጋዬንም የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን እጠራለሁ” ይላል እግዚአብሔር፤ “በዚህች ምድርና በነዋሪዎቿም ላይ፣ በአካባቢዋም ባሉ ሕዝቦች ሁሉ ላይ አመጣባቸዋለሁ፤ ፈጽሜም አጠፋቸዋለሁ፤ ሰዎች የሚጸየፉአቸውና የሚሣለቁባቸው፣ የዘላለምም ባድማ አደርጋቸዋለሁ፤

10የደስታንና የእልልታን ድምፅ፣ የሙሽራውንና የሙሽራዪቱን ድምፅ፣ የወፍጮን ድምፅና የመብራትን ብርሃን አስቀራለሁ።

11አገሪቱ በሞላ ባድማና ጠፍ ትሆናለች፤ እነዚህም ሕዝቦች ለባቢሎን ንጉሥ ሰባ ዓመት ይገዛሉ።

12“ነገር ግን ሰባው ዓመት ከተፈጸመ በኋላ፣ የባቢሎንን ንጉሥና ሕዝቡን፣ የባቢሎናውያንንም ምድር ስለ በደላቸው እቀጣቸዋለሁ” ይላል እግዚአብሔር፤ “ለዘላለምም ባድማ አደርጋታለሁ፤

13በምድሪቱ ላይ የተናገርሁትን ሁሉ ይኸውም በዚህ መጽሐፍ የተጻፈውንና ኤርምያስ በሕዝቦች ሁሉ ላይ የተናገረውን ትንቢት አመጣባታለሁ።

14ሕዝቧም ለብዙ ሕዝቦችና ለታላላቅ ነገሥታት ባሮች ይሆናሉ፤ እንደ አድራጎታቸውና እንደ እጃቸውም ሥራ እከፍላቸዋለሁ።”

15የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፤ “በቍጣዬ የወይን ጠጅ የተሞላውን ይህን ጽዋ ከእጄ ውሰድ፤ እኔ ወደ ምልክህም ሕዝቦች ሁሉ ሄደህ አጠጣቸው።

16በጠጡም ጊዜ ይንገዳገዳሉ፤ በመካከላቸው ከምሰደው ሰይፍ የተነሣ ያብዳሉ።”

17ስለዚህ ጽዋውን ከእግዚአብሔር እጅ ተቀብዬ እርሱ ወደ ላከኝ ሕዝቦች ሁሉ ሄድሁ፤ እንዲጠጡትም አደረግሁ፤

18ዛሬ እንደሆነው ሁሉ ባድማና ሰዎች የሚጸየፉአቸው መዘባበቻና ርግማን እንዲሆኑ፦ ኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ከተሞች፣ ነገሥታቷንና ባለሥልጣኖቿን፣

19የግብፅን ንጉሥ ፈርዖንን፣ አገልጋዮቹን፣ ባለሥልጣኖቹንና ሕዝቡን ሁሉ፣

20በዚያ የሚኖሩትን ድብልቅ ሕዝብ ሁሉ፣ የዖፅ ምድር ነገሥታትን ሁሉ፣ በአስቀሎና፣ በጋዛ፣ በአቃሮንና በአዛጦንም ሕዝብ ቅሬታ ያሉትን የፍልስጥኤም ነገሥታት፣

21ኤዶምን፣ ሞዓብን፣ አሞንን፣

22የጢሮስንና የሲዶናን ነገሥታት ሁሉ፣ ከባሕሩ ማዶ ያሉ የጠረፍ ምድር ነገሥታትን፣

23ድዳንን፣ ቴማንን፣ ቡዝን፣ ጠጒራቸውን ዙሪያውን የሚከረከሙትን ሕዝብ ሁሉ፣

24የዐረብ ነገሥታትን ሁሉ፣ በምድረ በዳ የሚኖሩትን የድብልቅ ሕዝብ ነገሥታት ሁሉ፣

25የዘምሪ፣ የኤላምና የሜዶን ነገሥታትን ሁሉ፣

26በቅርብና በሩቅ ያሉትን የሰሜን ነገሥታትንም ሁሉ በማከታተል፣ በምድር ላይ ያሉትን መንግሥታት ሁሉ አጠጣኋቸው፤ ከእነዚህም ሁሉ በኋላ የሺሻክ ንጉሥ ደግሞ ይጠጣል።

27“አንተም እንዲህ ብለህ ንገራቸው፤ ‘የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጠጡ፤ ስከሩ፤ አስታውኩም፤ ዳግመኛም ላትነሡ በመካከላችሁ በምሰደው ሰይፍ ፊት ውደቁ።’

28ነገር ግን ጽዋውን ከእጅህ ለመውሰድና ለመጠጣት እንቢ ካሉ፣ እንዲህ በላቸው፦ ‘የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ በግድ ትጠጣላችሁ።

29እነሆ፤ ስሜ የተጠራበትን ከተማ ማጥፋት እጀምራለሁ፤ ታዲያ ያለ ቅጣት ታመልጣላችሁን? ሳትቀጡ አትለቀቁም፤ በምድር በሚኖሩት ሁሉ ላይ ሰይፍን እጠራለሁና ሳትቀጡ አታመልጡም፤ ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።’

30“እንግዲህ ይህን ቃል ሁሉ ትንቢት ተናገርባቸው፤ እንዲህም በላቸው፣ “ ‘እግዚአብሔር ከላይ ይጮኻል፤ ከቅዱስ ማደሪያው ነጐድጓዳማ ድምፁን ያሰማል፤ በራሱ ምድር ላይ እጅግ ይጮኻል፤ እንደ ወይን ጨማቂዎች፣ በምድር በሚኖሩት ሁሉ ላይም ያስገመግማል፤

31እግዚአብሔር ከሕዝቦች ጋር ይፋረዳልና፣ ታላቅ ጩኸት እስከ ምድር ዳርቻ ያስተጋባል፤ በሰው ሁሉ ላይ ፍርድን ያመጣል፤ ክፉዎችንም ለሰይፍ ይዳርጋል” ይላል እግዚአብሔር።

32የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እነሆ፤ ጥፋት፣ ከአገር ወደ አገር እየተዛመተ መጥቶአል፤ ብርቱ ዐውሎ ነፋስ፣ ከምድር ዳርቻ ተነሥቶአል።

33በዚያን ጊዜ በእግዚአብሔር የተገደሉት ከምድር ዳር እስከ ምድር ዳር በሁሉ ስፍራ ተረፍርፈው ይታያሉ፤ እንደ ጒድፍ በምድር ላይ ይጣላሉ እንጂ፣ አይለቀስላቸውም፤ ሬሳቸውም አይሰበሰብም፤ አይቀበርምም።

34እናንት እረኞች፤ አልቅሱ፤ ዋይ በሉ፤ እናንት የመንጋው ጌቶች፤ በዐመድ ላይ ተንከባለሉ፤ የምትታረዱበት ቀን ደርሶአልና፤ እንደ ውብ የሸክላ ዕቃ ወድቃችሁ ትከሰክሳላችሁ።

35እረኞች የሚሸሹበት፣ የመንጋ ጠባቂዎችም የሚያመልጡበት የለም።

36እግዚአብሔር ማሰማሪያቸውን አጥፍቶአልና፣ የእረኞችን ጩኸት፣ የመንጋ ጠባቂዎችን ዋይታ ስሙ።

37ከእግዚአብሔር ጽኑ ቍጣ የተነሣ፣ ሰላማዊው ምድር ባድማ ይሆናል።

38እንደ አንበሳ ከጐሬው ይወጣል፤ ከአስጨናቂው ሰይፍ፣ ከቍጣውም የተነሣ፣ ምድራቸው ባድማ ትሆናለች።

ማብራሪያ

25:1-7 ከክፉ መንገዶች ወደ እግዚአብሔር አምልኮና አገልግሎት የመመለስ፣ ኃጢአተኞችም ክርስቶስን እንዲታመኑና በቤዛነቱም እንዲካፈሉ የተሰጠው ጥሪ ሁሉን ይመለከታል። እግዚአብሔር የጸጋን መንገዶች የያዝንበትን ዘመን ይመዘግባል፤ ባለንባቸውም በዛን ቁጥር ካላሻሻልናቸው የተጠያቂነታችን መጠን ይከብዳል። ማልዶ መነሳት ይህ ሕዝብ እንዲመለስና በሕይወት እንዲኖር ያለውን ጥልቅ ፍላጎት ያሳያል። ለብሔራዊ መዳን አስፈላጊ እንደመሆኑ መጠን ግለሰባዊና ዝርዝር ለውጥ አጥብቆ ሊገፋበት ይገባል፤ እያንዳንዱም ከራሱ ክፉ መንገድ መመለስ አለበት። ሆኖም ግን ይህ ሁሉ ከንቱ ነበር። የእግዚአብሔርን ቁጣ ለማስወገድ ትክክለኛውንና ብቸኛውን መንገድ አልተጠቀሙም።

25:8-14 የአይሁድ ምርኮ የሚቆይበት ጊዜ መወሰኑ ትንቢቱን የሚያጸና ብቻ ሳይሆን፣ የእግዚአብሔርን ሕዝብ የሚያጽናናና እምነትንና ጸሎትን የሚያበረታታ ይሆናል። የባቢሎን ውድቀት አስቀድሞ ተነግሯል፤ የማረሚያው ሥራ ሲጠናቀቅ በትሩ እሳት ውስጥ ይጣላል። ለጽዮን ምቹ ጊዜው ሲደርስ፣ ባቢሎን በበደሏ ትቀጣለች፤ ልክ ሌሎች አሕዛብ በኃጢአታቸው እንደተቀጡ ሁሉ ማለት ነው። የመጽሐፍ ቅዱስ ማስጠንቀቂያ ሁሉ በእርግጠኝነት ይፈጸማል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም በአራተኛው ዓመት፥ በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር በመጀመሪያው ዓመት፥ ስለ ይሁዳ ሕዝብ ሁሉ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው። አማርኛ ENGNIV The word came to Jeremiah concerning all the people of Judah in the fourth year of Jehoiakim son of Josiah king of Juda… English BCV ኢዮኣቄም ወዲ ኢዮስያስ፥ ኣብ ይሁዳ ምስ ነገሰ ኣብ ራብዐይቲ ዓመቱ፤ ናቡከደነፆር ከዓ ኣብ ባቢሎን ምስ ነገሰ ኣብ ቀዳመይቲ ዓመቱ፤ ንዅሎም ህዝቢ ይሁዳ ዝምልከት ቃል፥ ካብ እግዚኣብሄር ና… ትግርኛ GAZBIB Yehoyaaqiim ilmi Yosiyaas biyya Yihudaa irratti mo'ee waggaa afuraffaatti, Nebukadnezaar mootiin biyya Baabilon mo'ee w… Afaan Oromoo BCV GIZ ነገር ዘኮነ ኀበ ኤርምያስ እምኅበ እግዚአብሔር በእንተ ኵሉ ሕዝበ ይሁዳ በራብዕ ዓመተ መንግሥቱ ለኢዮአቄም ወልደ ኢዮስያስ ንጉሥ ይሁዳ። giz GAZGAZ Yehoyaaqiim ilmi Yosiyaas biyya Yihudaa irratti mo'ee waggaa afuraffaatti, Nebukadnezaar mootiin biyya Baabilon mo'ee w… Afaan Oromoo BCV aksum ኢዮኣቄም ወዲ ኢዮስያስ፥ ኣብ ይሁዳ ምስ ነገሰ ኣብ ራብዐይቲ ዓመቱ፤ ናቡከደነፆር ከዓ ኣብ ባቢሎን ምስ ነገሰ ኣብ ቀዳመይቲ ዓመቱ፤ ንዅሎም ህዝቢ ይሁዳ ዝምልከት ቃል፥ ካብ እግዚኣብሄር ና… ትግርኛ SWAHSUV Neno hili ndilo lililomjia Yeremia, katika habari za watu wote wa Yuda; katika mwaka wa nne wa Yehoyakimu, mwana wa Yos… Kiswahili