ትንቢተ ኤርምያስ 15

AMHNIVአማርኛ21 ጥቅሶች4:49 አዳምጥ
አዳምጥ 4:49 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፤ “ሙሴና ሳሙኤል እንኳ በፊቴ ቢቆሙ፣ ልቤ ለዚህ ሕዝብ አይራራምና፤ ከፊቴ አስወጣቸው፤ ይሂዱ።

2እነርሱም፣ ‘ወዴት እንሂድ?’ ቢሉህ፣ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፤ ‘እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ ‘ለሞት የተመደበ ወደ ሞት፣ ለሰይፍ የተመደበ ወደ ሰይፍ፣ ለራብ የተመደበ ወደ ራብ፣ ለምርኮ የተመደበ ወደ ምርኮ ይሄዳል።’

3“እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘አራት ዐይነት አጥፊዎችን እሰድባቸዋለሁ፤ እነዚህም፦ ለመግደል ሰይፍ፣ ለመጐተት ውሾች፣ እንዲሁም ጠራርጎ ለመብላትና ለማጥፋት የሰማይ ወፎችና የምድር አራዊት ናቸው።

4የይሁዳ ንጉሥ የሕዝቅያስ ልጅ ምናሴ በኢየሩሳሌም ካደረገው በደል የተነሣ፣ ለምድር ነገሥታት ሁሉ መሰቀቂያ አደርጋቸዋለሁ።

5“ኢየሩሳሌም ሆይ፤ የሚራራልሽ ማን ነው? ማንስ ያለቅስልሻል? ደኅንነትሽንስ ማን ጎራ ብሎ ይጠይቃል?

6እኔን ጥለሽኛል” ይላል እግዚአብሔር፤ “ወደ ኋላም እያፈገፈግሽ ነው፤ ስለዚህ እጄን በአንቺ ላይ አነሣለሁ፤ አጠፋሻለሁም፤ ከእንግዲህም አልራራልሽም።

7በአገሪቱ የከተማ ደጆች፣ በመንሽ እበትናቸዋለሁ፤ ከመንገዳቸው አልተመለሱምና፣ ሕዝቤን በሐዘን እመታለሁ፤ ጥፋትም አመጣባቸዋለሁ፤

8የመበለቶቻቸውን ቍጥር፣ ከባሕር አሸዋ ይልቅ አበዛለሁ፤ የጐበዛዝት እናቶች በሆኑትም ላይ፣ አጥፊውን በቀትር አመጣባቸዋለሁ። ሽብርንና ድንጋጤን፣ በድንገት አወርድባቸዋለሁ።

9የሰባቶቹ እናት ትዝለፈለፋለች፤ ትንፋሿም ይጠፋል፤ ገና ቀን ሳለ ፀሓይዋ ትጠልቃለች፤ እርሷም ታፍራለች፤ ትዋረዳለችም፤ የተረፉትንም በጠላቶቻቸው ፊት፣ ለሰይፍ እዳርጋቸዋለሁ፤” ይላል እግዚአብሔር።

10ወይኔ እናቴ! ለምድር ሁሉ፣ የጭቅጭቅና የክርክር ሰው የሆንሁትን ምነው ወለድሽ! ለማንም አላበደርሁም፤ ከማንም አልተበደርሁም፤ ነገር ግን ሰው ሁሉ ይረግመኛል።

11እግዚአብሔር እንዲህ አለ፤ “በእርግጥ ለበጎ ዐላማ እታደግሃለሁ፤ በመከራና በጭንቅ ጊዜም፣ ጠላቶችህ ደጅ እንዲጠኑህ በእውነት አደርጋለሁ።

12“ሰው ብረትን፣ ከሰሜን የመጣን ብረት፣ ነሐስንስ መስበር ይችላልን?

13በመላ አገርህ፣ ስላለው ኀጢአትህ ሁሉ፣ ሀብትና ንብረትህን፣ ያለ ዋጋ አሳልፌ ለምርኮ እሰጣለሁ።

14ቍጣዬ በላያችሁ፣ የሚነድ እሳት ትጭራለችና፣ በማታውቀው አገር፣ ለጠላቶችህ ባሪያ አደርግሃለሁ።”

15እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ታውቃለህ፤ እንግዲህ አስበኝ፤ ጐብኘኝም፤ አሳዳጆቼን ተበቀልልኝ። ታጋሽ እንደ መሆንህ አታጥፋኝ፤ ባንተ ምክንያት የሚደርስብኝን ነቀፋ አስብ።

16ቃልህ በተገኘ ጊዜ በላሁት፤ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ በስምህ ተጠርቻለሁና፣ ቃልህ ሐሤትና የልብ ደስታ ሆነልኝ።

17ፈንጠዝያ ከሚያደርጉት ጋር አልተቀመጥሁም፤ ከእነርሱም ጋር አልፈነጨሁም፤ እጅህ በላዬ ስለ ነበር፣ በቍጣህ ስለ ሞላኸኝ፣ ለብቻዬ ተቀመጥሁ።

18ሕመሜ ለምን ጸናብኝ? ቍስሌስ ለምን በረታብኝ? ለምንስ የማይፈወስ ሆነ? እንደሚያታልል ወንዝ፣ እንደሚያሳስት ምንጭ ትሆንብኛለህን?

19ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ብትመለስ፣ መልሼ አቆምሃለሁ፤ ታገለግለኛለህም፤ የከበረውን ከማይረባው ለይተህ ብትናገር፣ አፍ ትሆነኛለህ፤ እነርሱ ወደ አንተ ይመለሳሉ እንጂ፣ አንተ ወደ እነርሱ አትመለስም፤

20ለዚህ ሕዝብ የናስ ቅጥር፣ የተመሸገ የናስ ቅጥር አደርግሃለሁ፤ ልታደግህና፣ ላድንህም፣ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና፤ ቢዋጉህም እንኳ፣ ሊያሸንፉህ አይችሉም፤” ይላል እግዚአብሔር፤

21“ከክፉዎች እጅ እቤዥሃለሁ፤ ከጨካኞችም ጭምደዳ እታደግሃለሁ።”

ማብራሪያ

15:1-9 ጌታ ሙሴና ሳሙኤልም እንኳ ቢለምኑት በከንቱ እንደሚሆን ገለጸ። ይህ 'ምንም እንኳ በፊቱ ቢቆሙም' ተብሎ የቀረበው አገላለጽ፣ እነርሱ ያንን እንደማያደርጉና በሰማይ ያሉ ቅዱሳንም በምድር ላይ ላሉ ቅዱሳን እንደማይማልዱ ያሳያል። አይሁዶች በእግዚአብሔር ጽድቅ ፍርድ ለተለያዩ የመከራ አይነቶች ተፈረደባቸው፤ የቀሩትም እንደ ገለባ ወደ ምርኮ ይሰደዳሉ። ከዚያም ሕዝበ ብዙ ከተማዋ ባድማ ሆነች። መጥፎ ምሳሌዎችና በስህተት የዋለ ሥልጣን ሰዎች ከሞቱ ወይም ከወንጀላቸው ንስሐ ከገቡ በኋላም ቢሆን ብዙውን ጊዜ ገዳይ ውጤቶችን ያስከትላሉ። ይህም ለሌሎች ኃጢአት መንስኤ ከመሆን ሁላችንንም በከፍተኛ ሁኔታ ሊያስፈራን ይገባል።

ኤርምያስ 15:10-14

ኤርምያስ ብዙ ንቀትና ነቀፋ ደርሶበታል፤ እነርሱ ሊባርኩትና ስለ እርሱም እግዚአብሔርን ሊያመሰግኑት ሲገባ ነበር።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG እግዚአብሔርም እንደዚህ አለኝ፦ ሙሴና ሳሙኤል በፊቴ ቢቆሙም፥ ልቤ ወደዚህ ሕዝብ አይዘነብልም፤ ከፊቴ ጣላቸው፤ ይውጡ። አማርኛ ENGNIV Then the Lord said to me: “Even if Moses and Samuel were to stand before me, my heart would not go out to this people. … English BCV ሽዑ እግዚኣብሄር ከምዙይ በለኒ፤ “ሙሴን ሳሙኤልን እኳ ኣብ ቅድመይ ደው ኢሎም እንተ ዝልምኑኒ፥ ነዞም ህዝቢ እዚኣቶም ልበይ ኣይርህርሀሎምን፥ ካብ ቅድሚ ገፀይ ኣውፅኣዮምሞ ይኺዱ። ትግርኛ GAZBIB Ergasiis Waaqayyo anatti dubbatee,“Musee fi Saamu'el dhufanii yoo ana kadhataniif illee, ani saba kanaaf garaa hin laaf… Afaan Oromoo BCV GIZ ወይቤለኒ እግዚአብሔር፦ እመ ቆሙ ሙሴ ወሳሙኤል ቅደመ ገጽየ፡ ኢሀሎ ነፍስየ ኀቤሆሙ፤ ፈንዎሙ ዳእሙ ለዝ ሕዝብ ይሑሩ። giz GAZGAZ Ergasiis Waaqayyo anatti dubbatee,“Musee fi Saamu'el dhufanii yoo ana kadhataniif illee, ani saba kanaaf garaa hin laaf… Afaan Oromoo BCV aksum ሽዑ እግዚኣብሄር ከምዙይ በለኒ፤ “ሙሴን ሳሙኤልን እኳ ኣብ ቅድመይ ደው ኢሎም እንተ ዝልምኑኒ፥ ነዞም ህዝቢ እዚኣቶም ልበይ ኣይርህርሀሎምን፥ ካብ ቅድሚ ገፀይ ኣውፅኣዮምሞ ይኺዱ። ትግርኛ SWAHSUV Ndipo Bwana akaniambia, Hata wangesimama mbele zangu Musa na Samweli, moyo wangu usingewaelekea watu hawa; watupe, wato… Kiswahili