ትንቢተ ኤርምያስ 15

AMHEVGአማርኛ21 ጥቅሶች3:58 አዳምጥ
አዳምጥ 3:58 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1እግዚአብሔርም እንደዚህ አለኝ፦ ሙሴና ሳሙኤል በፊቴ ቢቆሙም፥ ልቤ ወደዚህ ሕዝብ አይዘነብልም፤ ከፊቴ ጣላቸው፤ ይውጡ።

2እነርሱም፦ ወዴት እንውጣ፡ ቢሉህ፥ አንተ፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ለሞት የሆነ ወደ ሞት፥ ለሰይፍም የሆነ ወደ ሰይፍ፥ ለራብም የሆነ ወደ ራብ፥ ለምርኮም የሆነ ወደ ምርኮ፡ ትላቸዋለህ።

3ሰይፍን ለመግደል ውሾችንም ለመጐተት የሰማያትንም ወፎች የምድርንም አራዊት ለመብላትና ለማጥፋት፥ አራቱን ዓይነት ጥፋት አዝዝባቸዋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።

4የይሁዳም ንጉሥ የሕዝቅያስ ልጅ ምናሴ በኢየሩሳሌም ስላደረገው ሁሉ በምድር መንግሥታት ሁሉ መካከል ለመከራ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ።

5ኢየሩሳሌም ሆይ፥ የሚራራልሽ ማን ነው? የሚያዝንልሽስ ማን ነው? ወይስ ስለ ደኅንነትሽ ይጠይቅ ዘንድ ፈቀቅ የሚል ማነ ነው?

6አንቺ እኔን ጥለሻል፥ ይላል እግዚአብሔር፥ ወደ ኋላሽም ተመልሰሻል፤ ስለዚህ እጄን በአንቺ ላይ ዘርግቼ አጥፍቼሻለሁ፤ ከይቅርታ ደክሜአለሁ።

7በአገርም ደጆች ውስጥ በመንሽ አበጥሬአቸዋለሁ፤ የወላድ መካን አድርጌአቸዋለሁ፥ ሕዝቤንም አጥፍቼአለሁ፤ ከመንገዳቸውም አልተመለሱም።

8መበለቶቻቸውም ከባሕር አሸዋ ይልቅ በዝተውብኛል፤ በብላቴኖች እናት ላይ በቀትር ጊዜ አጥፊውን አምጥቻለሁ፤ ጣርንና ድንጋጤን በድንገት አምጥቼባታለሁ።

9ሰባት የወለደች ደክማለች፥ ነፍስዋንም አውጥታለች፤ ቀን ገና ሳለ ፀሐይዋ ገብታባታለች፤ አፍራለች ተዋርዳማለች፤ የተረፉትንም በጠላቶቻቸው ፊት ለሰይፍ አሳልፌ እሰጣለሁ።

10እናቴ ሆይ፥ ወዮልኝ! ለምድር ሁሉ የክርክርና የጥል ሰው የሆንሁትን ወለድሽኝ ለማንም አላበደርሁም፥ ማንም ለእኔ አላበደረም፥ ነገር ግን ሁሉ ይረግመኛል።

11እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ በእውነት ለደኅንነትህ አጸናሃለሁ፤ በእውነት በመከራና በጭንቅ ጊዜ ጠላትህ እንዲለምንህ አደርገዋለሁ።

12በውኑ ብረትን፥ የሰሜንን ብረት፥ ናስንም የሚሰብር አለን?

13በዳርቻህ ሁሉ ስላለ ኃጢአትህ ሁሉ ባለጠግነትህንና መዝገብህን ለመበዝበዝ በከንቱ እሰጣለሁ።

14የምታቃጥላችሁ እሳት ከቍጣዬ ትነድዳለችና ከጠላቶችህ ጋር ወደማታውቀው ምድር አሳልፍሃለሁ።

15አቤቱ፥ አንተ ታውቃለህ፤ አስበኝ ጐብኘኝም የሚያሳድዱኝንም ተበቀላቸው እንጂ አትታገሣቸው፤ ስለ አንተ ስድብን እንደ ታገሥሁ እወቅ።

16ቃልህ ተገኝቶአል እኔም በልቼዋለሁ፤ አቤቱ፥ የሠራዊት አምላክ ሆይ፥ በስምህ ተጠርቻለሁና ቃልህ ሐሤትና የልብ ደስታ ሆነኝ።

17በዋዘኞችና በደስተኞች ጉባኤ አልተቀመጥሁም፤ ቍጣን ሞልተህብኛልና በእጅህ ፊት ለብቻዬ ተቀመጥሁ።

18ስለ ምን ሕመሜ አዘወተረኝ? ቍስሌስ ስለ ምን የማይፈወስ ሆነ? ስለ ምንስ፦ አልሽርም፡ አለ? በውኑ እንደ ሐሰተኛ ምንጭ፥ እንዳልታመነች ውኃ ትሆነኛለህን?

19ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ብትመለስ እመልስሃለሁ፥ በፊቴም ትቆማለህ፤ የከበረውንም ከተዋረደው ብትለይ እንደ አፌ ትሆናለህ፤ እነርሱ ወደ አንተ ይመለሳሉ፥ አንተ ግን ወደ እነርሱ አትመለስም።

20ለዚህም ሕዝብ የተመሸገ የናስ ቅጥር አደርግሃለሁ፤ ይዋጉሃል እኔ ግን ለማዳን ከአንተ ጋር ነኝና አያሸንፉህም።

21ከክፉ ሰዎችም እጅ እታደግሃለሁ፥ ከጨካኞችም ጡጫ እቤዥሃለሁ።

ማብራሪያ

15:1-9 ጌታ ሙሴና ሳሙኤልም እንኳ ቢለምኑት በከንቱ እንደሚሆን ገለጸ። ይህ 'ምንም እንኳ በፊቱ ቢቆሙም' ተብሎ የቀረበው አገላለጽ፣ እነርሱ ያንን እንደማያደርጉና በሰማይ ያሉ ቅዱሳንም በምድር ላይ ላሉ ቅዱሳን እንደማይማልዱ ያሳያል። አይሁዶች በእግዚአብሔር ጽድቅ ፍርድ ለተለያዩ የመከራ አይነቶች ተፈረደባቸው፤ የቀሩትም እንደ ገለባ ወደ ምርኮ ይሰደዳሉ። ከዚያም ሕዝበ ብዙ ከተማዋ ባድማ ሆነች። መጥፎ ምሳሌዎችና በስህተት የዋለ ሥልጣን ሰዎች ከሞቱ ወይም ከወንጀላቸው ንስሐ ከገቡ በኋላም ቢሆን ብዙውን ጊዜ ገዳይ ውጤቶችን ያስከትላሉ። ይህም ለሌሎች ኃጢአት መንስኤ ከመሆን ሁላችንንም በከፍተኛ ሁኔታ ሊያስፈራን ይገባል።

ኤርምያስ 15:10-14

ኤርምያስ ብዙ ንቀትና ነቀፋ ደርሶበታል፤ እነርሱ ሊባርኩትና ስለ እርሱም እግዚአብሔርን ሊያመሰግኑት ሲገባ ነበር።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV Then the Lord said to me: “Even if Moses and Samuel were to stand before me, my heart would not go out to this people. … English BCV ሽዑ እግዚኣብሄር ከምዙይ በለኒ፤ “ሙሴን ሳሙኤልን እኳ ኣብ ቅድመይ ደው ኢሎም እንተ ዝልምኑኒ፥ ነዞም ህዝቢ እዚኣቶም ልበይ ኣይርህርሀሎምን፥ ካብ ቅድሚ ገፀይ ኣውፅኣዮምሞ ይኺዱ። ትግርኛ GAZBIB Ergasiis Waaqayyo anatti dubbatee,“Musee fi Saamu'el dhufanii yoo ana kadhataniif illee, ani saba kanaaf garaa hin laaf… Afaan Oromoo BCV GIZ ወይቤለኒ እግዚአብሔር፦ እመ ቆሙ ሙሴ ወሳሙኤል ቅደመ ገጽየ፡ ኢሀሎ ነፍስየ ኀቤሆሙ፤ ፈንዎሙ ዳእሙ ለዝ ሕዝብ ይሑሩ። giz GAZGAZ Ergasiis Waaqayyo anatti dubbatee,“Musee fi Saamu'el dhufanii yoo ana kadhataniif illee, ani saba kanaaf garaa hin laaf… Afaan Oromoo BCV aksum ሽዑ እግዚኣብሄር ከምዙይ በለኒ፤ “ሙሴን ሳሙኤልን እኳ ኣብ ቅድመይ ደው ኢሎም እንተ ዝልምኑኒ፥ ነዞም ህዝቢ እዚኣቶም ልበይ ኣይርህርሀሎምን፥ ካብ ቅድሚ ገፀይ ኣውፅኣዮምሞ ይኺዱ። ትግርኛ AMHNIV እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፤ “ሙሴና ሳሙኤል እንኳ በፊቴ ቢቆሙ፣ ልቤ ለዚህ ሕዝብ አይራራምና፤ ከፊቴ አስወጣቸው፤ ይሂዱ። አማርኛ SWAHSUV Ndipo Bwana akaniambia, Hata wangesimama mbele zangu Musa na Samweli, moyo wangu usingewaelekea watu hawa; watupe, wato… Kiswahili