ትንቢተ ኤርምያስ 13

AMHEVGአማርኛ26 ጥቅሶች4:44 አዳምጥ
አዳምጥ 4:44 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1እግዚአብሔር እንዲህ ይለኛል፦ ሂድ፥ ከተልባ እግር የተሠራችን መታጠቂያ ለአንተ ግዛ፥ ወገብህንም ታጠቅባት፤ በውኃውም ውስጥ አትንከራት።

2እንደ እግዚአብሔርም ቃል መታጠቂያን ገዛሁ፥ ወገቤንም ታጠቅሁባት።

3ሁለተኛም ጊዜ፦ የገዛሃትን በወገብህ ያለችውን መታጠቂያ ወስደህ ተነሥ፥ ወደ ኤፍራጥስም ሂድ፥ በዚያም በተሰነጠቀ ዓለት ውስጥ ሸሽጋት፡ የሚል የእግዚአብሔር ቃል መጣልኝ።

5እግዚአብሔርም እንዳዘዘኝ ሄድሁ በኤፍራጥስም አጠገብ ሸሸግኋት።

6ከብዙ ቀንም በኋላ እግዚአብሔር፦ ተነሥተህ ወደ ኤፍራጥስ ሂድ፥ በዚያም ትሸሽጋት ዘንድ ያዘዝሁህን መታጠቂያ ከዚያ ውስጥ ውሰድ፡ አለኝ።

7እኔም ወደ ኤፍራጥስ ሄድሁ ቆፈርሁም፥ ከሸሸግሁበትም ስፍራ መታጠቂያይቱን ወሰድሁ። እነሆም፥ መታጠቂያይቱ ተበላሽታ ነበር፥ ለምንም አልረባችም።

8የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፤

9እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እንዲሁ የይሁዳን ትዕቢት ታላቁንም የኢየሩሳሌምን ትዕቢት አበላሻለሁ።

10ቃሌን ይሰሙ ዘንድ እንቢ የሚሉ፥ በልባቸውም እልከኝነት የሚሄዱ፥ ያመልኩአቸውና ይሰግዱላቸው ዘንድ ሌሎችን አማልክት የሚከተሉ እነዚህ ክፉ ሕዝብ አንዳች እንዳማትረባ እንደዚች መታጠቂያ ይሆናሉ።

11መታጠቂያ በሰው ወገብ ላይ እንደምትጣበቅ፥ እንዲሁ ሕዝብና ስም ምስጋናና ክብር ይሆኑልኝ ዘንድ የእስራኤልን ቤት ሁሉ የይሁዳንም ቤት ሁሉ ከእኔ ጋር አጣብቄአለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ነገር ግን አልሰሙም።

12ስለዚህ፦ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ማድጋ ሁሉ የወይን ጠጅ ይሞላል፡ ብለህ ትነግራቸዋለህ፤ እነርሱም፦ ማድጋ ሁሉ የወይን ጠጅ እንዲሞላ በውኑ እኛ አናውቅምን? ይሉሃል።

13አንተም እንዲህ ትላቸዋለህ፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በዚህች ምድር የሚኖሩትን ሁሉ፥ በዳዊት ዙፋን የሚቀመጡትን ነገሥታት ካህናቱንም ነቢያቱንም በኢየሩሳሌምም የተቀመጡትን ሁሉ በስካር እሞላቸዋለሁ።

14ሰውንም በሰው ላይ፥ አባቶችንና ልጆችን በአንድ ላይ፥ እቀጠቅጣለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ አጠፋቸዋለሁ እንጂ አልራራም፥ አላዝንም፥ አልምርም።

15ስሙ፥ አድምጡ፤ እግዚአብሔር ተናግሮአልና አትታበዩ።

16ሳትጨልም እግራችሁም በጨለመችው ተራራ ላይ ሳትሰናከል፥ በተስፋ የምትጠባበቁትን ብርሃን ለሞት ጥላና ለድቅድቅ ጨለማ ሳይለውጠው ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር ክብርን ስጡ።

17ይህን ባትሰሙ ነፍሴ ስለ ትዕቢታችሁ በስውር ታለቅሳለች፤ የእግዚአብሔርም መንጋ ተማርኮአልና ዓይኔ ታነባለች፥ እንባንም ታፈስሳለች።

18ለንጉሡና ለንጉሥ እናት ለእቴጌይቱ፦ የክብራችሁ አክሊል ከራሳችሁ ወርዶአልና ተዋርዳችሁ ተቀመጡ፡ በል።

19የደቡብ ከተሞች ተዘግተዋል፥ የሚከፍታቸውም የለም፤ ይሁዳ ሁሉ ተማርኮአል፥ ፈጽሞ ተማርኮአል።

20ዓይናችሁን አንሥታችሁ እነዚህን ከሰሜን የሚመጡትን ተመልከቱ፤ ለአንቺ የተሰጠ መንጋ፥ የተዋበ መንጋሽ፥ ወዴት አለ?

21ወዳጆችሽ እንዲሆኑ ያስተማርሻቸውን በራስሽ ላይ አለቆች ባደረጋቸው ጊዜ ምን ትያለሽ? እንደ ወላድ ሴት ምጥ አይዝሽምን?

22በልብሽም፦ እንዲህ ያለ ነገር ስለ ምን ደረሰብኝ? ብትዪ፥ ከኃጢአትሽ ብዛት የተነሣ የልብስሽ ዘርፍ ተገልጦአል ተረከዝሽም ተገፍፎአል።

23በውኑ ኢትዮጵያዊ መልኩን ወይስ ነብር ዝንጕርጕርነትን ይለውጥ ዘንድ ይችላልን? በዚያን ጊዜ ክፋትን የለመዳችሁ እናንተ ደግሞ በጎ ለማድረግ ትችላላችሁ።

24ስለዚህ እንደሚያልፍ እብቅ በምድረ በዳ ነፋስ እበትናቸዋለሁ።

25ረስተሽኛልና፥ በሐሰትም ታምነሻልና ዕጣሽ የለካሁልሽም እድል ፈንታ ይህ ነው፥ ይላል እግዚአብሔር።

26ስለዚህም የልብስሽን ዘርፍ በፊትሽ እገልጣለሁ እፍረትሽም ይታያል።

27አስጸያፊ ሥራሽን፥ ምንዝርናሽን፥ ማሽካካትሽን፥ የግልሙትናሽንም መዳራት በኮረብቶች ላይ በሜዳም አይቻለሁ። ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ወዮልሽ! ለመንጻት እንቢ ብለሻል፤ ይህስ እስከ መቼ ነው?

ማብራሪያ

፲፫፥፩-፲፩ ነቢያት በምልክቶች ማስተማር የተለመደባቸው ነበር። ማብራሪያውንም በቁጥር ፱-፲፩ እናገኘዋለን። የእስራኤል ሕዝብ ለእግዚአብሔር እንደዚህች መታጠቂያ ነበሩ። በሰጣቸው ሕግ፣ በላከላቸው ነቢያት፣ በፈጸመላቸውም ቸርነቶች ከእርሱ ጋር እንዲጣበቁ አደረጋቸው። በጣዖት አምልኮአቸውና በኃጢአቶቻቸው ራሳቸውን በባዕድ ምድር ቀብረው፣ በአሕዛብም መካከል ተቀላቅለው፣ ሙሉ በሙሉ ተበላሽተው ምንም የማይጠቅሙ ሆነው ነበር። በእውቀታችን፣ በኃይላችንና በውጫዊ መብቶቻችን የምንኮራ ከሆነ፣ እግዚአብሔር እነርሱን ቢያደርቃቸው ፍትሐዊ ነው። የሰው ልጆች አእምሮ ስለ በደላቸውና ስላለባቸው አደጋ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ሊነቃቁ ይገባል፤ ሆኖም የመንፈስ ቅዱስ ተጽዕኖ ከሌለ ምንም ነገር ሙሉ በሙሉ ውጤታማ አይሆንም።

፲፫፥፲፪-፲፯ ጠርሙሱ ወይን ለመያዝ እንደተዘጋጀው ሁሉ፣ የሕዝቡ ኃጢአትም የቁጣ ዕቃዎች አደረጋቸው፤ እነሱም ለእግዚአብሔር ፍርዶች የተዘጋጁና እርስ በእርስ ጥፋትን እስኪያመጡ ድረስ የሚሞሉበት ሆኑ።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6