ትንቢተ ኤርምያስ 12

AMHEVGአማርኛ17 ጥቅሶች3:28 አዳምጥ
አዳምጥ 3:28 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1አቤቱ፥ ከአንተ ጋር በተምዋገትሁ ጊዜ አንተ ጻድቅ ነህ፤ ነገር ግን ከአንተ ጋር ስለ ፍርድ ልናገር። የኃጢአተኞች መንገድ ስለምን ይቃናል? በደልንስ ለሚያደርጉ ሁሉ ስለምን ደኅንነት ይሆናል?

2ተክለሃቸዋል፤ ሥር ሰድደዋል፤ አድገዋል አፍርተውማል፤ በአፋቸው አንተ ቅርብ ነህ፥ ከልባቸው ግን ሩቅ ነህ።

3አንተ ግን፥ አቤቱ፥ አውቀኸኛል፤ አይተኸኛል፥ ልቤንም በፊትህ ፈትነሃል፤ እንደ በጎች ለመታረድ ጐትተህ ለያቸው፥ ለመታረድም ቀን አዘጋጃቸው።

4ምድሪቱ የምታለቅሰው፥ የአገሩ ሣርስ ሁሉ የሚደርቀው እስከ መቸ ነው? የተቀመጡባት ሰዎች፦ ፍጻሜያችንን አያይም፡ ብለዋልና ስለ ክፋታቸው እንስሶችና ወፎች ጠፍተዋል።

5ከእግረኞች ጋር በሮጥህ ጊዜ እነርሱ ቢያደክሙህ፥ ከፈረሶች ጋር መታገል እንዴት ትችላለህ? በሰላምም ምድር ታምነህ ብትቀመጥ፥ በዮርዳኖስ ትዕቢት እንዴት ታደርጋለህ?

6ወንድሞችህና የአባትህ ቤት እነርሱ ጭምር አታልለውሃልና፥ በኋላህም ጮኸዋልና፤ በመልካምም ቢናገሩህም አትታመናቸው።

7ቤቴን ትቼአለሁ ርስቴንም ጥያለሁ፥ ነፍሴም የምትወድዳትን በጠላቶችዋ እጅ አሳልፌ ሰጥቻለሁ።

8ርስቴ በዱር እንዳለ አንበሳ ሆናብኛለች፤ ድምፅዋን አንሥታብኛለች፤ ስለዚህ ጠልቻታለሁ።

9ርስቴ እንደ ዝንጕርጕር አሞራ ሆነችብኝን? አሞሮችስ በዙሪያዋና በላይዋ ሆነዋልን? ሂዱ፥ የምድር አራዊትን ሁሉ ሰብስቡ፥ ይበሉም ዘንድ አምጡአቸው።

10ብዙ እረኞች የወይኑን ቦታዬን አጥፍተዋል፥ እድል ፈንታዬንም ረግጠዋል፤ የአምሮቴን እድል ፈንታ ምድረ በዳ አድርገውታል።

11ባድማ አድርገውታል፥ ፈርሶም ወደ እኔ ያለቅሳል፤ ምድር ሁሉ ባድማ ሆናለች በልቡም የሚያስባት የለም።

12በወናዎች ኮረብቶች ሁሉ ላይ በዝባዦች መጥተዋል፥ የእግዚአብሔር ሰይፍ ከምድር ዳር ጀምሮ እስከ ምድር ዳር ድረስ ይበላልና፤ ለሥጋ ለባሽ ሁሉ ሰላም የለም።

13ስንዴን ዘሩ እሾህንም አጨዱ፤ ደከሙ፥ ምንም አልረባቸውም፤ ስለ እግዚአብሔር ጽኑ ቍጣ ከፍሬያችሁ ታፍራላችሁ።

14እግዚአብሔር ለሕዝቤ ለእስራኤል ያወረስሁትን ርስት ለሚነኩት ክፉዎች ጐረቤቶች ሁሉ እንዲህ ይላልና፦ እነሆ፥ ከምድራቸው እነቅላቸዋለሁ፥ የይሁዳንም ቤት ከመካከላቸው እነቅለዋለሁ።

15ከነቀልኋቸውም በኋላ መልሼ እምራቸዋለሁ፥ እያንዳንዱንም ወደ ርስቱ እያንዳንዱንም ወደ ምድሩ እመልሳለሁ።

16በበኣል ይምሉ ዘንድ ሕዝቤን እንዳስተማሩ በስሜ፦ ሕያው እግዚአብሔርን! ብለው ይምሉ ዘንድ የሕዝቤን መንገድ በትጋት ቢማሩ፥ በዚያን ጊዜ በሕዝቤ መካከል ይመሠረታሉ።

17ባይሰሙኝ ግን ያንን ሕዝብ ፈጽሜ እነቅለዋለሁ አጠፋውማለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።

ማብራሪያ

12:1-6 በእግዚአብሔር አሰራር ላይ እጅግ በጨለምን ጊዜ፣ ስለ እግዚአብሔር ትክክለኛ ሀሳቦችን ልንጠብቅ ይገባናል፤ ለፍጥረቱ ከቶም ትንሽ ስህተት እንኳ አንዳላደረገ በማመን። ከእኛም ጋር ይሁን ከሌሎች ጋር የእርሱን አያያዝ ለመረዳት አስቸጋሪ በሆነብን ጊዜ፣ አጠቃላይ እውነቶችን እንደ መሰረታዊ መርሆቻችን ልንመለከትና በእነሱም ልንጸና ይገባናል፤ እግዚአብሔር ጻድቅ ነው። የምናገለግለው አምላክ ልባችን ወደ እርሱ እንዴት እንደሆነ ያውቃል። እርሱ የግብዞችን ተንኮልና የቅን ልቦናን ቅንነት ያውቃል። መለኮታዊ ፍርዶች ክፉዎችን ከመሰማሪያቸው ለመታረድ እንደታሰቡ በጎች ያወጣቸዋል። ይህች ለም መሬት በውስጧ በኖሩት ሰዎች ክፋት የተነሳ ወደ በረሃነት ተለወጠች። እግዚአብሔር ነቢዩን ገሰጸው። የአናቶት ሰዎች ተቃውሞ ከይሁዳ ገዥዎች ከሚጠብቀው ያህል አስፈሪ አልነበረም። እንዲህ ያለ ብዙ ክፋት በመኖሩ የምናዝነው ሐዘን ብዙውን ጊዜ በሚያመጣብን ፈተናዎች የተነሳ ከብስጭት ጋር ይደባለቃል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV You are always righteous, O Lord, when I bring a case before you. Yet I would speak with you about your justice: Why do… English BCV “ኦ እግዚኣብሄር፥ ምሳኻ ብዝማጐተሉ ጊዜ፥ ንስኻ ፃድቕ ኢኻ፤ ምስ ናይ እዙይውን፥ ስለ ፍርዲ ምሳኻ ኽናገር እደሊ ኣለኹ፥ መንገዲ ኸዳዓትስ ንምንታይ ይሳኻዕ? ትግርኛ GAZBIB Yaa Waaqayyo, ati qajeelaa dha; kanaafis falmata koo si duratti nan dhi'eeffadha; haa ta'u iyyuu malee, waa'ee firdiif … Afaan Oromoo BCV GIZ ጻድቅ አንተ እግዚኦ እስመ እትዋቀስ በኀቤከ፡ ወባሕቱ ፍትሐ እነግር፤ ለምንት ፍኖተ ኃጥአን ድሉት፡ ወተፈሥሑ ኵሎሙ ዓላውያን በማዕሌት? giz GAZGAZ Yaa Waaqayyo, ati qajeelaa dha; kanaafis falmata koo si duratti nan dhi'eeffadha; haa ta'u iyyuu malee, waa'ee firdiif … Afaan Oromoo BCV aksum “ኦ እግዚኣብሄር፥ ምሳኻ ብዝማጐተሉ ጊዜ፥ ንስኻ ፃድቕ ኢኻ፤ ምስ ናይ እዙይውን፥ ስለ ፍርዲ ምሳኻ ኽናገር እደሊ ኣለኹ፥ መንገዲ ኸዳዓትስ ንምንታይ ይሳኻዕ? ትግርኛ AMHNIV እግዚአብሔር ሆይ፤ ጒዳዬን በፊትህ ሳቀርብ፣ አንተ ጻድቅ መሆንህን እያወቅሁ ነው። የክፉዎች መንገድ ለምን ይሰምራል? የከዳተኞችስ ኑሮ ለምን ይሳካል? አማርኛ SWAHSUV Wewe u mwenye haki, Ee Bwana, nitetapo nawe, lakini nitasema nawe katika habari ya haki. Mbona njia ya wabaya inasitawi… Kiswahili