ትንቢተ ኢሳይያስ 7

AMHNIVአማርኛ25 ጥቅሶች4:27 አዳምጥ
አዳምጥ 4:27 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1የዖዝያን የልጅ ልጅ፣ የኢዮአታም ልጅ አካዝ የይሁዳ ንጉሥ በነበረበት ዘመን፣ የሶርያ ንጉሥ ረአሶንና የእስራኤል ንጉሥ የሮሜልዩ ልጅ ፋቁሔ ኢየሩሳሌምን ሊወጉ ወጡ፤ ነገር ግን ድል ሊያደርጓት አልቻሉም።

2ለዳዊት ቤት፣ “ሶርያና ኤፍሬም ተባብረዋል” የሚል ወሬ በደረሰ ጊዜ፣ የዱር ዛፍ በነፋስ እንደሚናወጥ የአካዝና የሕዝቡ ልብ እንዲሁ ተናወጠ።

3እግዚአብሔርም ኢሳይያስን እንዲህ አለው፤ “አንተና ልጅህ ሸአር ያሹብ አካዝን ለመገናኘት ወደ ልብስ አጣቢው ዕርሻ በሚወስደው መንገድ ወዳለው ወደ ላይኛው የኵሬ መስኖ ጫፍ ውጡ፤

4እንዲህም በለው፤ ‘ተጠንቀቅ፤ ተረጋጋ፤ አትፍራ በእነዚህ ከእሳት ተርፈው በሚጤሱት በሁለቱ የዕንጨት ጒማጆች፣ በሶርያና በንጉሥዋ በረአሶን እንዲሁም በሮሜልዩ ልጅ ቍጣ አትሸበር።

5ሶርያ ኤፍሬምና፣ የሮሜልዩ ልጅ ሊያጠፉህ እንዲህ ብለው ተማከሩ፤

6“ይሁዳን እንውረር፤ እንበታትነው ተከፋፍለንም እንግዛው፤ የጣብኤልንም ልጅ እናንግሥባት።”

7ልዑል እግዚአብሔር ግን እንዲህ ይላል፦ “ ‘ይህ ምክራቸው አይፈጸምም፤ ከቶም አይደረግም፤

8የሶርያ ራስ ደማስቆ፣ የደማስቆ ራስ ረአሶን ነውና፤ በሥልሳ አምስት ዓመት ውስጥ፣ የኤፍሬም ሕዝብ ይበታተናል፤ ሕዝብ መሆኑም ይቀራል።

9የኤፍሬም ራስ ሰማርያ፣ የሰማርያም ራስ የሮሜልዩ ልጅ ነው። እንግዲህ በእምነታችሁ ካልጸናችሁ፣ ፈጽሞ መቆም አትችሉም።’ ”

10እንደ ገናም እግዚአብሔር አካዝን እንዲህ አለው፤

11“ከጥልቁ ጥልቅ ወይም ከከፍታው ከፍታ ምልክት እንዲሰጥህ ከእግዚአብሔር ከአምላክህ ለምን።”

12አካዝ ግን፣ “አልለምንም፣ እግዚአብሔርንም አልፈታተንም” አለ።

13ኢሳይያስም እንዲህ አለ፤ “እናንተ የዳዊት ቤት ሆይ፤ ስሙ፤ የሰውን ትዕግሥት መፈታተናችሁ አንሶ የአምላኬን ትዕግሥት ትፈታተናላችሁን?

14ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፤ ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።

15ክፉውን መተውና መልካሙን መምረጥ ሲችል ቅቤና ማር ይበላል።

16ነገር ግን ሕፃኑ ክፉውን መተውና መልካሙን መምረጥ ከመቻሉ በፊት የፈራሃቸው የሁለቱ ነገሥታት ምድር ባድማ ይሆናል።

17ኤፍሬም ከይሁዳ ከተለየበት ቀን ጀምሮ እግዚአብሔር ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ ዘመን በአንተ፣ በሕዝብህና በአባትህ ቤት ላይ ያመጣል፤ የሚያመጣውም የአሦርን ንጉሥ ነው።”

18በዚያን ቀን እግዚአብሔር ራቅ ካሉት ከግብፅ ወንዞች ዝንቦችን፣ ከአሦርም ምድር ንቦችን በፉጨት ይጠራል።

19እነርሱም በሙሉ መጥተው፣ በየበረሓው ሸለቆ፣ በየዐለቱ ንቃቃት፣ በየእሾኹ ቍጥቋጦና በየውሃው ጒድጓድ ሁሉ ይሰፍራሉ።

20በዚያን ቀን፣ እግዚአብሔር ከወንዝ ማዶ በተከራየው ምላጭ፣ ማለትም በአሦር ንጉሥ፣ የራስና የእግር ጠጒራችሁን እንዲሁም ጢማችሁን ይላጫል።

21በዚያን ቀን፣ አንድ ሰው አንዲት ጊደርና ሁለት በግ ብቻ ይተርፈዋል።

22ከሚሰጡትም የተትረፈረፈ ወተት ቅቤ ይበላል፤ በምድሪቱም የቀሩ ሁሉ ቅቤና ማር ይበላሉ።

23በዚያን ቀን ሺህ ሰቅል ብር የሚያወጣ አንድ ሺህ የወይን ተክል የነበረበት ቦታ ሁሉ፣ ኵርንችትና እሾኽ ብቻ ይሆናል።

24ምድሪቱ በኵርንችትና በእሾኽ ስለምትሸፈን፣ ሰዎች ወደዚያ የሚገቡት ቀስትና ፍላጻ ይዘው ነው፤

25ኵርንችትና እሾኹን በመፍራት ከዚህ በፊት በመቈፈሪያ ተቈፍረው ወደ ነበሩት ወደ እነዚያ ኰረብታዎች ሁሉ ከእንግዲህ አትሄድም፤ ነገር ግን የከብቶች መሰማሪያና የበጎች መፈንጫ ቦታ ይሆናሉ።

ማብራሪያ

፯:፩-፱ ኃጢአተኞች ሰዎች ብዙውን ጊዜ እንደራሳቸው በሆኑ ክፉዎች ይቀጣሉ። በታላቅ ጭንቀትና ግራ መጋባት ውስጥ ሆነው፣ አይሁዳውያን ሁሉ ነገር እንደጠፋ ተስፋ ቆረጡ። እግዚአብሔርን ጠላታቸው አድርገው ነበርና፣ እርሱን ወዳጃቸው እንዴት ማድረግ እንዳለባቸው አያውቁም ነበር። ነቢዩም በእምነትና በእግዚአብሔር ላይ በመደገፍ ጠላቶቻቸውን እንዲንቁ ሊያስተምራቸው ይገባል። አካዝ በፍርሃት እነርሱን ሁለት ኃያላን ነገሥታት ብሎ ገለጻቸው። ነቢዩም፦ አይደለም፤ እነርሱ አስቀድሞ የጠፉ የሚያጨሱ የችቦ ጭራዎች ብቻ ናቸው አላቸው። የሶርያና የእስራኤል ሁለት መንግሥታት ሊጠፉ ተቃርበው ነበር። እግዚአብሔር ለምድር ችቦዎች ሥራ ሲኖረው፣ በፊታቸው ያለውን ሁሉ ያወድማሉ፤ ነገር ግን ሥራቸው ሲፈጸም፣ በጢስ ውስጥ ይጠፋሉ። አካዝ እጅግ የሚያስፈራው ያሰበው ነገር የሽንፈታቸው ምክንያት ሆነ፤ ምክንያቱም በአንተ ላይ ክፉ ምክር ስለመከሩ ነውና፣ ይህም ለእግዚአብሔር በደል ነው። እግዚአብሔር ተሳላቂዎችን ይጸየፋቸዋልና ያ ጥረት እንዳይሳካ ቃሉን ሰጠ። ሰው ያቅዳል እንጂ፣ እግዚአብሔር ግን ያደርጋል። እነርሱ ራሳቸው የጥፋት አፋፍ ላይ እያሉ ጎረቤቶቻቸውን ሊያጠፉ መሞከራቸው የሞኝነት ሥራ ነበር። ኢሳይያስም አይሁዳውያንን በተሰጣቸው ዋስትናዎች እንዲተማመኑ ሊያበረታታቸው ይገባል። በፈተናዎች ጊዜ አእምሮን ለማረጋጋትና ለማሰባሰብ እምነት ፍጹም አስፈላጊ ነው።

፯፡፲-፲፮

ወደ እግዚአብሔር የተሰወረ ልባዊ አለመውደድ ብዙውን ጊዜ ለእርሱ ባለው የአክብሮት ሽፋን ይሸፈናል። እግዚአብሔርን እንደማያምኑ የወሰኑ ሰዎች ግን እርሱን እንደማይፈትኑት ያስመስላሉ።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG እንዲህም ሆነ፤ በይሁዳ ንጉሥ በዖዝያን ልጅ በኢዮአታም ልጅ በአካዝ ዘመን የሶርያ ንጉሥ ረአሶን የእስራኤልም ንጉሥ የሮሜልዩ ልጅ ፋቁሔ ኢየሩሳሌምን ሊወጉ ወጡ፥ ሊያሸንፉአትም አልቻሉም። አማርኛ ENGNIV When Ahaz son of Jotham, the son of Uzziah, was king of Judah, King Rezin of Aram and Pekah son of Remaliah king of Isr… English BCV ከምዙይ ድማ ኾነ፦ ወዲ ወዱ ንኦዝያን ወዲ ኢዮኣታም ኣካዝ ንጉስ ይሁዳ ኣብ ዝነበረሉ ዘመን፥ ንጉስ ሶርያ ረኣሶንን ንጉስ እስራኤል ወዲ ሮሜልዩ ፋቁሔን ንኢየሩሳሌም ክወግኡ ወፁ፤ ግና ኸሸን… ትግርኛ GAZBIB Bara Ahaaz ilmi Yotaam Uziyaa mootii Yihudaa turetti, Resiin mootiin Sooriyaa fi Pheqaan ilmi Remaaliyaa mootiin Israa'… Afaan Oromoo BCV GIZ ወእምዝ ካዕበ ኮነ በመዋዕለ አካዝ ወልደ ኢዮአታም ወልደ ዖዝያን ንጉሠ ይሁዳ፤ ዓርገ ረአሶን ንጉሠ አራም፤ ወፋቁሔ ወልደ ሮሜልዩ ንጉሠ እስራኤል፤ ይትቃተልዋ ለኢየሩሳሴም ወስእንዋ ቀቲሎታ። giz GAZGAZ Bara Ahaaz ilmi Yotaam Uziyaa mootii Yihudaa turetti, Resiin mootiin Sooriyaa fi Pheqaan ilmi Remaaliyaa mootiin Israa'… Afaan Oromoo BCV aksum ከምዙይ ድማ ኾነ፦ ወዲ ወዱ ንኦዝያን ወዲ ኢዮኣታም ኣካዝ ንጉስ ይሁዳ ኣብ ዝነበረሉ ዘመን፥ ንጉስ ሶርያ ረኣሶንን ንጉስ እስራኤል ወዲ ሮሜልዩ ፋቁሔን ንኢየሩሳሌም ክወግኡ ወፁ፤ ግና ኸሸን… ትግርኛ SWAHSUV Hata ikawa katika siku za Ahazi, mwana wa Yothamu, mwana wa Uzia, mfalme wa Yuda, Resini, mfalme wa Shamu, na Peka, mwa… Kiswahili