ትንቢተ ኢሳይያስ 51

AMHNIVአማርኛ23 ጥቅሶች4:56 አዳምጥ
አዳምጥ 4:56 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1“እናንት ጽድቅን የምትከታተሉ፣ እግዚአብሔርን የምትፈልጉ ስሙኝ፤ ተቈርጣችሁ የወጣችሁበትን ዐለት፣ ተቈፍራችሁ የወጣችሁባትንም ጕድጓድ ተመልከቱ።

2ወደ አባታችሁ ወደ አብርሃም፣ ወደ ወለደቻችሁም ወደ ሣራ ተመልከቱ፤ በጠራሁት ጊዜ አንድ ራሱን ብቻ ነበር፤ ባረክሁት፤ አበዛሁትም።

3እግዚአብሔር ጽዮንን በርግጥ ያጽናናታል፤ ፍርስራሾቿንም በርኅራኄ ይመለከታል፤ ምድረ በዳዋን እንደ ዔድን፣ በረሓዋንም እንደ እግዚአብሔር ተክል ቦታ ያደርጋል፤ ተድላና ደስታ፣ ምስጋናና የዝማሬ ድምፅ በእርሷ ይገኛሉ።

4“ወገኔ ሆይ፤ አድምጠኝ፤ ሕዝቤ ሆይ፤ ስማኝ፤ ሕግ ከእኔ ይወጣል፤ ፍርዴም ለሕዝቦች ብርሃን ይሆናል።

5ጽድቄ በፍጥነት እየቀረበ፣ ማዳኔም እየደረሰ ነው፤ ክንዴም ለመንግሥታት ፍትሕን ያመጣል፤ ደሴቶች ወደ እኔ ይመለከታሉ፤ ክንዴንም በተስፋ ይጠብቃሉ።

6ዐይኖቻችሁን ወደ ሰማያት አንሡ፤ ወደ ታች ወደ ምድርም ተመልከቱ፤ ሰማያት እንደ ጢስ በነው ይጠፋሉ፤ ምድር እንደ ልብስ ታረጃለች፤ ነዋሪዎቿም እንደ አሸን ፈጥነው ይረግፋሉ፤ ማዳኔ ግን ለዘላለም ይኖራል፤ ጽድቄም መጨረሻ የለውም።

7“እናንት ጽድቅን የምታውቁ፣ ሕጌንም በልባችሁ ያኖራችሁ ሰዎች ስሙኝ፤ ሰዎች ሲዘብቱባችሁ አትፍሩ፤ ሲሰድቧችሁ አትደንግጡ።

8ብል እንደ ልብስ ይበላቸዋል፤ ትል እንደ በግ ጠጕር ይውጣቸዋል፤ ጽድቄ ግን ለዘላለም፣ ማዳኔም ከትውልድ እስከ ትውልድ ጸንታ ትኖራለች።”

9የእግዚአብሔር ክንድ ሆይ፤ ተነሥ፤ ተነሥ! ኀይልን ልበስ፤ እንዳለፉት ዘመናት፣ በጥንት ትውልዶችም እንደሆነው ሁሉ ተነሥ። ረዓብን የቈራረጥህ፣ ታላቁን ዘንዶ የወጋህ አንተ አይደለህምን?

10የዳኑት እንዲሻገሩ ባሕሩን፣ የታላቁን ጥልቅ ውሆች ያደረቅህ፣ በጥልቁም ውስጥ መንገድ ያበጀህ፣ አንተ አይደለህምን?

11እግዚአብሔር የተቤዣቸው ይመለሳሉ፤ በዝማሬ ወደ ጽዮን ይገባሉ፤ የዘላለማዊ ደስታን አክሊል ይቀዳጃሉ፤ ተድላና ደስታ ያገኛሉ፤ ሐዘንና ልቅሶም ከእነርሱ ይሸሻል።

12“የማጽናናችሁ እኔ፣ እኔው ብቻ ነኝ፤ ሟች የሆኑትን ሰዎች፣ እንደ ሣር የሚጠወልጉትን የሰው ልጆች ለምን ትፈራለህ?

13የፈጠረህን፣ ሰማያትን የዘረጋውን፣ ምድርን የመሠረተውን እግዚአብሔርን ረስተሃል፤ ሊያጠፋህ ከተዘጋጀው፣ ከጨቋኙ ቊጣ የተነሣ፣ በየቀኑ በሽብር ትኖራለህ፤ ታዲያ የጨቋኙ ቊጣ የት አለ?

14ዐንገታቸውን የደፉ እስረኞች በፍጥነት ነጻ ይወጣሉ፤ በታሰሩበትም ጕድጓድ ውስጥ አይሞቱም፤ እንጀራ አያጡም።

15ሞገዱ እንዲተም ባሕሩን የማናውጥ፣ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ነኝና፤ ስሙም የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው።

16ቃሌን በአፍህ አኖርሁ፤ በእጄ ጥላ ጋረድሁህ፤ ሰማያትን በስፍራቸው ያስቀመጥሁ፣ ምድርን የመሠረትሁ፣ ጽዮንንም፣ ‘አንቺ ሕዝቤ ነሽ’ ያልሁ እኔ ነኝ።

17ከእግዚአብሔር እጅ፣ የቍጣውን ጽዋ የጠጣሽ፣ ዝቃጩ እንኳ ሳይቀር፣ ሰዎችን የሚያንገደግደውን ዋንጫ የጨለጥሽ፣ ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ተነሺ፤ ተነሺ፤ ተነሺ።

18ከወለደቻቸው ወንዶች ልጆች ሁሉ፣ የመራት አንድም አልነበረም፤ ካሳደገቻቸው ወንዶች ልጆች ሁሉ፣ እጇን ይዞ የወሰዳት ማንም አልነበረም።

19እነሆ፤ በጥፋት ላይ ጥፋት መጥተውብሻል፤ ታዲያ ማን ያጽናናሻል? እነርሱም መፈራረስና ጥፋት፣ ራብና ሰይፍ ናቸው፤ ታዲያ ማን ያስተዛዝንሽኀሀ

20ወንዶች ልጆችሽ ዝለዋል፤ በወጥመድ እንደ ተያዘ ሚዳቋ፣ በየጐዳናው አደባባይ ላይ ተኝተዋል። የእግዚአብሔር ቊጣ፣ የአምላክሽም ተግሣጽ ሞልቶባቸዋል።

21ስለዚህ አንቺ የተጐዳሽ፣ ያለ ወይን ጠጅ የሰከርሽ ይህን ስሚ።

22ሕዝቡን የሚታደግ አምላክሽ፣ ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እነሆ፤ ከእጅሽ፣ ያንገደገደሽን ጽዋ ወስጃለሁ፤ ያንን ጽዋ፣ የቊጣዬን ዋንጫ፣ ዳግም አትጠጪውም፤

23ባስጨነቁሽ፣ ‘በላይሽ ላይ እንድንሄድ ተነጠፊልን’ ባሉሽ እጅ ላይ አደርገዋለሁ፤ ጀርባሽን እንደ መሬት፣ እንደ መሸጋገሪያም መንገድ አደረግሽላቸው።”

ማብራሪያ

51:1-3 እንደገና በመወለድ ጸጋ ያገኙ ሰዎች በኃጢአት እንደተፈጠሩ ማሰባቸው መልካም ነው። ይህም ስለራሳችን ዝቅ ብለን እንድናስብ፣ ስለመለኮታዊው ጸጋ ደግሞ ከፍ ከፍ ብለን እንድናስብ ሊያደርግ ይገባል። ለእግዚአብሔር ክብር አገልግሎት መስጠት መቻላችን ታላቁ መጽናኛ ነው። ሰዎች የያዙት ቅድስና በጨመረ መጠን፣ የሚያደርጉትም መልካም ሥራ በጨመረ መጠን፣ የሚያገኙት ደስታ ይበልጣል። ስለ በደላችን በአንክሮ እናስብ። ይህ ደግሞ ልብን ትሁት እንዲሆን፣ ህሊናንም ነቅቶና ለስላሳ እንዲሆን ያደርጋል። ክርስቶስንም ለነፍስ እጅግ ውድ ያደርጉታል፤ ለሌሎችም በምናደርገው ጥረትና ጸሎት ብርታትን ይሰጣሉ።

51:4-8 የክርስቶስ ወንጌል ይሰበካል ይገለጥማል። ቸል ብንለውስ እንዴት እናመልጣለን? ያለ ጽድቅ መዳን የለም። ነፍስ በዚህ ዓለም አንጻር እንደ ጭስ ትጠፋለች፤ አካልም እንደ አሮጌ ልብስ ይጣላል። ነገር ግን ደስታቸው በክርስቶስ ጽድቅና በመዳን የሆኑት፣ ጊዜና ቀናት በሌሉበት ጊዜም ቢሆን መጽናናታቸው አይለያቸውም። ደመናዎች ፀሐይን ያጨልማሉ እንጂ አካሄዷን ግን አያቆሙም።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG እናንተ ጽድቅን የምትከተሉ እግዚአብሔርንም የምትሹ፥ ስሙኝ፤ ከእርሱ የተቈረጣችሁበትን ድንጋይ ከእርሱም የተቈፈራችሁበትን ጕድጓድ ተመልከቱ። አማርኛ ENGNIV “Listen to me, you who pursue righteousness and who seek the Lord: Look to the rock from which you were cut and to the … English BCV “ኣቱም ንፅድቂ እትኽተሉ፥ ንእግዚኣብሄር ከዓ እትደልዩዎ ስምዑኒ። ናብቲ ዝተቘረፅኩምሉ እምንን፥ ናብቲ ዝተዅዓትኩሙሉ ጕድጓድን ተመልከቱ። ትግርኛ GAZBIB Waaqayyo namoota Xiyooniin, “Isin warri qajeelummaa duukaa buutan, warri ana Waaqayyoon barbaaddattan na dhaggeeffadhaa… Afaan Oromoo BCV GIZ ስምዑኒ ኵልክሙ እለ ትዴግንዎ ለጽድቅ ወእለ ተኀሥሥዎ ለእግዚአብሔር፤ ርእይዋ ለኰኵሕ ጽንዕት እንተ ወቀርክሙ ወዐዘቅተ ዕምቅተ እንተ ከረይክሙ። giz GAZGAZ Waaqayyo namoota Xiyooniin, “Isin warri qajeelummaa duukaa buutan, warri ana Waaqayyoon barbaaddattan na dhaggeeffadhaa… Afaan Oromoo BCV aksum “ኣቱም ንፅድቂ እትኽተሉ፥ ንእግዚኣብሄር ከዓ እትደልዩዎ ስምዑኒ። ናብቲ ዝተቘረፅኩምሉ እምንን፥ ናብቲ ዝተዅዓትኩሙሉ ጕድጓድን ተመልከቱ። ትግርኛ SWAHSUV Nisikilizeni, ninyi mnaoifuatia haki; ninyi mnaomtafuta Bwana; uangalieni mwamba ule ambao mlitolewa kwa kuchongwa, na … Kiswahili