ትንቢተ ኢሳይያስ 50

AMHNIVአማርኛ11 ጥቅሶች2:33 አዳምጥ
አዳምጥ 2:33 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እናታችሁን የፈታሁበት የፍቺ ወረቀት የት አለ? ወይስ እናንተን የሸጥኋችሁ ለየትኛው አበዳሪዬ ነው? እነሆ፤ ስለ ኀጢአታችሁ ተሸጣችኋል፤ ስለ መተላለፋችሁም እናታችሁ ተፈታለች።

2በመጣሁ ጊዜ ለምን በዚያ ሰው አልነበረም? በተጣራሁስ ጊዜ የሚመልስ ሰው እንዴት በዚያ ታጣ? ስለ እናንተ ወጆ ለመክፈል ክንዴ አጥራ ነበርን? እናንተንስ ለማዳን ኀይል አነሰኝን? እነሆ፤ በተግሣጼ ባሕሩን አደርቃለሁ፤ ወንዞችን ምድረ በዳ አደርጋለሁ፤ ዓሦቻቸው ውሃ በማጣት ይሸታሉ፤ በጥማትም ይሞታሉ።

3ሰማይን ጨለማ አለብሰዋለሁ፤ ማቅን መሸፈኛው አደርጋለሁ።

4ልዑል እግዚአብሔር የተባ አንደበት ሰጥቶኛል፤ ስለዚህ ደካሞችን ብርቱ ለማድረግ ምን ማለት እንዳለብኝ ዐውቃለሁ፤ በየማለዳው ያነቃኛል፤ በመማር ላይ እንዳለ ተማሪ ለመስማት ጆሮዬን ያነቃዋል።

5ልዑል እግዚአብሔር ጆሮዬን ከፍቶታል፤ እኔም ዐመፀኛ አይደለሁም፤ ወደ ኋላም አላፈገፈግሁም።

6ለሚገርፉኝ ጀርባዬን፣ ጢሜን ለሚነጩ ጕንጬን ሰጠሁ፤ ፊቴን ከውርደት፣ ከጥፋትም አልሰወርሁም።

7ልዑል እግዚአብሔር ስለሚረዳኝ አልዋረድም፤ ስለዚህ ፊቴን እንደ ባልጩት ድንጋይ አድርጌአለሁ፤ እንደማላፍርም ዐውቃለሁ።

8ንጹሕ መሆኔን የሚያረጋግጥልኝ በአጠገቤ አለ፤ ታዲያ ማን ሊከሰኝ ይችላል? እስቲ ፊት ለፊት እንጋጠም! ተቃዋሚዬስ ማን ነው? እስቲ ይምጣ!

9የሚረዳኝ እርሱ ጌታ እግዚአብሔር ነው፤ የሚፈርድብኝስ ማን ነው? እነሆ፤ ሁሉም እንደ ልብስ ያረጃሉ፤ ብልም ይበላቸዋል።

10ከእናንተ እግዚአብሔርን የሚፈራ፣ የባሪያውንም ቃል የሚሰማ ማን ነው? ያ ሰው በጨለማ የሚሄድ ከሆነና፣ ብርሃንም ከሌለው፣ በእግዚአብሔር ስም ይታመን፤ በአምላኩም ይደገፍ።

11አሁን ግን እናንተ እሳት አንድዳችሁ፣ የራሳችሁን የሚንቦገቦግ ችቦ የያዛችሁ ሁሉ፣ በሉ በእሳታችሁ ብርሃን ሂዱ፤ ባንቦገቦጋችሁትም የችቦ ብርሃን ተመላለሱ። እንግዲህ ከእጄ የምትቀበሉት ይህ ነው፤ በሥቃይም ትጋደማላችሁ።

ማብራሪያ

ኢሳ 50:1-3 የእግዚአብሔር ሕዝብ ነን ብለው የተናገሩና በከባድ ሁኔታ እየተያዙ እንደሆነ የሚመስላቸው ሰዎች፣ እግዚአብሔር ከነሱ ጋር ከባድ እንደሆነ በማሰብ ለማጉረምረም ይቀናቸዋል። ለእንዲህ ዓይነቱ ማጉረምረም መልስ ይህ ነው፤ እግዚአብሔር ከኃጢአቶቻቸው በስተቀር ማንንም ከጥቅሞቻቸው አልከለከለም። አይሁዶች ወደ ባቢሎን የተላኩት ቃል ኪዳኑን የጣሰ በሆነው በጣዖት አምልኮአቸው ምክንያት ነበር፤ በመጨረሻም የክብርን ጌታ በመስቀላቸው ምክንያት ተጥለዋል። እግዚአብሔር ኃጢአታቸውን እንዲተውና የራሳቸውን ጥፋት እንዲያስወግዱ ጠራቸው። ከሁሉ በኋላ፣ ወልድ ወደ ራሱ ወደሆኑት መጣ፤ ነገር ግን የራሱ የሆኑት አልተቀበሉትም። እግዚአብሔር ሰዎችን ወደ ደስታ ሲጠራ፣ እነርሱም ምላሽ ሳይሰጡ ሲቀሩ፣ በፍትሐዊነትም ለስቃይ ተተዉ። ስለ ኃይሉ የነበሩትን ጥርጣሬዎች ለማስወገድ፣ ማስረጃዎች ተሰጥተዋል። ከመከራውና ከሞቱ ጋር ተያይዘው የነበሩት ድንቅ ነገሮች የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን አወጁ፣ ማቴ 27:54።

50:4-9 ኢየሱስ በአንድ አካል አምላክና ሰው እንደነበረ፣ አንዳንዴ እንደ ጌታ አምላክ ሲናገር ወይም ሲወሳ እናገኛለን፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ እንደ ሰውና እንደ ይሖዋ አገልጋይ ይወሳል። የተሰበረውንና የተጸጸተውን ልብ፣ በኃጢአት የደከሙትን፣ በስቃይ የተቸገሩትን የሚያጽናኑ እውነቶችን ሊናገር ነበር።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እናታችሁን የፈታሁበት የፍችዋ ጽሕፈት የት አለ? ወይስ እናንተን የሸጥሁ ከአበዳሪዎች ለየትኛው ነው? እነሆ፥ ስለ ኃጢአታችሁ ተሽጣችኋል፥ ስለ በደላችሁም እናታች… አማርኛ ENGNIV This is what the Lord says: “Where is your mother's certificate of divorce with which I sent her away? Or to which of m… English BCV እግዚኣብሄር ከምዙይ ይብል ኣሎ፦ “እቲ ንኖኹም ዝፈታሕኹሉ፥ ናይ ፍትሕ ፅሑፍ ኣበይ ኣሎ? ነየናይ መለቅሒ እየኸ፥ ንኣኻትኩም ዝሸጥኩኹም? እንሆ፥ ንስኻትኩምስ፥ ብሰንኪ ሓጢኣታትኩም ኢኹም ዝ… ትግርኛ GAZBIB Waaqayyo,“Caaffanni ani ittiin haadha keessan gad dhiise meerree” Yookiis eenyutu gatii ana irraa qabaa iyyuun itti isi… Afaan Oromoo BCV GIZ ከመዝ ይቤ እግዚአብሔር፦ አይኑ ዝንቱ መጽሐፈ ኅዳጋቲሃ ለእምክሙ ዘፈነውኩ ላቲ ወለመኑ እፈዲ ዕዳ ዘሤጥኩክሙ፤ አኮኑ በኀጢአትክሙ ሤጥኩክሙ ወበጌጋይክሙ ፈነውክዋ ለእምክሙ። giz GAZGAZ Waaqayyo,“Caaffanni ani ittiin haadha keessan gad dhiise meerree” Yookiis eenyutu gatii ana irraa qabaa iyyuun itti isi… Afaan Oromoo BCV aksum እግዚኣብሄር ከምዙይ ይብል ኣሎ፦ “እቲ ንኖኹም ዝፈታሕኹሉ፥ ናይ ፍትሕ ፅሑፍ ኣበይ ኣሎ? ነየናይ መለቅሒ እየኸ፥ ንኣኻትኩም ዝሸጥኩኹም? እንሆ፥ ንስኻትኩምስ፥ ብሰንኪ ሓጢኣታትኩም ኢኹም ዝ… ትግርኛ SWAHSUV Bwana asema hivi, Iko wapi hati ya talaka ya mama yenu, ambayo kwa hiyo naliachana naye? Au nimewauza ninyi kwa nani ka… Kiswahili