ትንቢተ ኢሳይያስ 4

AMHNIVአማርኛ6 ጥቅሶች1:21 አዳምጥ
አዳምጥ 1:21 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1በዚያን ቀን ሰባት ሴቶች አንዱን ወንድ ይዘው፣ “የራሳችንን ምግብ እንበላለን፤ የራሳችንንም ልብስ እንለብሳለን፤ በአንተ ስም ብቻ እንጠራና፣ ውርደታችንን አስቀርልን” ይሉታል።

2በዚያን ቀን የእግዚአብሔር ዛፍ ቅርንጫፍ ያማረና የከበረ ይሆናል፤ የምድሪቱም ፍሬ ከጥፋት ለተረፈው የእስራኤል ወገን ኵራትና ክብር ይሆናል።

3በጽዮን የቀሩት፣ በኢየሩሳሌምም የተረፉት፣ በኢየሩሳሌም በሕይወት ከተመዘገቡት ሁሉ ጋር ቅዱሳን ተብለው ይጠራሉ።

4ጌታ የጽዮንን ሴቶች እድፍ ያጥባል፤ ኢየሩሳሌምንም ከተነከረችበት ደም በፍርድና በሚያቃጥል መንፈስ ያነጻታል።

5ከዚያም እግዚአብሔር በጽዮን ተራራ ላይና በዚያ በሚሰበሰቡትም ሁሉ ላይ በቀን ደመናንና ጢስን፣ በሌሊትም የሚንበለበለውን የእሳት ብርሃን ይፈጥራል፤ በክብሩ ሁሉ ላይ መጋረጃ ይሆናል፤

6ከቀኑ ሙቀት ጥላና መከለያ፣ ከውሽንፍርና ከዝናብም መጠጊያና መሸሸጊያ ስፍራ ይሆናል።

ማብራሪያ

፬፡፩ ይህ የመጀመሪያው ቁጥር የሦስተኛው ምዕራፍ ክፍል ነው። መከራ በምድሪቱ ላይ ሲመጣ፣ ያላገባች ሴት መሆን በአይሁድ ዘንድ እንደ ውርደት ይቆጠር ነበርና፣ እነዚህ ሴቶች ከተለመደው ልማድ በተጻራሪ ለራሳቸው ባሎችን ይፈልጉም ነበር።

ኢሳይያስ 4:2-6

የክርስቶስ መንግሥት በሐዋርያት ዘመን የተቋቋመበትን ብቻ ሳይሆን፣ የተበተኑት አይሁድ ወደ ቤተ ክርስቲያን ተሰብስበው መስፋፋቱ አስቀድሞ ተነግሯል። ክርስቶስ የእግዚአብሔር “ቡቃያ” ተብሎ ተጠርቷል፤ በኃይሉ የተተከለና ለክብሩ ያበበ ነው። ወንጌል የእግዚአብሔር ቡቃያ ፍሬ ነው፤ የወንጌል ጸጋዎችና መጽናናት ሁሉ ከክርስቶስ የሚመነጩ ናቸው። የምድር ፍሬ ተብሎም ተጠርቷል፣ ምክንያቱም በዚህ ዓለም የበቀለና ለአሁኑ ሁኔታ ተስማሚ ስለሆነ ነው። በክርስቶስ ያለውን ውበት ሁሉ፣ ቅድስናንም እንድናይ ከተደረግን፣ እኛ ከስም አይሁድ የተለየን መሆናችን ጥሩ ማስረጃ ይሆናል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG በዚያም ቀን ሰባት ሴቶች፦ የገዛ እንጀራችንን እንበላለን የገዛ ልብሳችንንም እንለብሳለን፤ ስምህ ብቻ በእኛ ላይ ይጠራ፥ መሰደባችንንም አርቅ፡ ብለው አንዱን ወንድ ይይዙታል። አማርኛ ENGNIV In that day seven women will take hold of one man and say, “We will eat our own food and provide our own clothes; only … English BCV በታ መዓልቲ እቲኣ፥ ሸውዓተ ኣንስቲ ንሓደ ሰብኣይ “እንጀራና ንበልዕ፤ ክዳንናውን ንኽደን፥ ግና ጥራሕ ስምካ ኣብ ልዕሌና ይፀዋዕ፤ ውርደትናውን ኣወግደልና” እናበላ ኽሕዛኦ እየን። ትግርኛ GAZBIB Yeroo sanatti dubartoonni torba dhiira tokko qabatanii,“Nuyi buddeena ofii qabnu in nyaanna, uffata ofii qabnus in uffa… Afaan Oromoo BCV GIZ ወይእኅዛሁ ሰብዑ አንስት ለአሐዱ ብእሲ ወይብላሁ፦ እክለ ዚአነ ንሴሰይ ወአልባሰኒ ዘዚአነ ንትዔረዝ፡ ዳእሙ ስመ ዚአከ ይሰመይ በላዕሌነ ወአኅድገነ ጽዕለተ። giz GAZGAZ Yeroo sanatti dubartoonni torba dhiira tokko qabatanii,“Nuyi buddeena ofii qabnu in nyaanna, uffata ofii qabnus in uffa… Afaan Oromoo BCV aksum በታ መዓልቲ እቲኣ፥ ሸውዓተ ኣንስቲ ንሓደ ሰብኣይ “እንጀራና ንበልዕ፤ ክዳንናውን ንኽደን፥ ግና ጥራሕ ስምካ ኣብ ልዕሌና ይፀዋዕ፤ ውርደትናውን ኣወግደልና” እናበላ ኽሕዛኦ እየን። ትግርኛ SWAHSUV Na siku hiyo wanawake saba watamshika mtu mume mmoja wakisema, Tutakula chakula chetu, na kuvaa nguo zetu wenyewe, laki… Kiswahili