ትንቢተ ኢሳይያስ 38

AMHEVGአማርኛ22 ጥቅሶች3:29 አዳምጥ
አዳምጥ 3:29 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1በዚያም ወራት ሕዝቅያስ ለሞት እስኪደርስ ታመመ። ነቢዩም የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ወደ እርሱ መጥቶ፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ትሞታለህ እንጂ በሕይወት አትኖርምና ቤትህን አስተካክል፡ አለው።

2ሕዝቅያስም ፊቱን ወደ ግድግዳው መልሶ እንዲህ ሲል ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፦

3አቤቱ፥ በፊትህ በእውነትና በፍጹም ልብ እንደ ሄድሁ ደስ የሚያሰኝህንም እንዳደረግሁ ታስብ ዘንድ እለምንሃለሁ። ሕዝቅያስም እጅግ አድርጎ አለቀሰ።

4የእግዚአብሔርም ቃል ወደ ኢሳይያስ እንዲህ ሲል መጣ፦

5ሂድ፥ ሕዝቅያስን እንዲህ በለው፦ የአባትህ የዳዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጸሎትህን ሰምቻለሁ፥ እንባህንም አይቻለሁ፤ እነሆ፥ በዕድሜህ ላይ አሥራ አምስት ዓመት አጨምራለሁ።

6አንተንና ይህችንም ከተማ ከአሦር ንጉሥ እጅ እታደጋለሁ፥ ይህችንም ከተማ እጋርዳታለሁ።

7እግዚአብሔርም የተናገረውን ነገር እንዲፈጽመው ከእግዚአብሔር ዘንድ ምልክቱ ይህ ይሆንልሃል።

8እነሆ፥ በአካዝ የጥላ ስፍረ ሰዓት ላይ ከፀሐይ ጋር የወረደውን በደረጃዎች ያለውን ጥላ አሥር ደረጃ ወደ ኋላ እንዲመለስ አደርጋለሁ። ፀሐይም በጥላ ስፍረ ሰዓት ላይ የወረደበት አሥር ደረጃ ወደ ኋላ ተመለሰ።

9የይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስ ታምሞ ከደዌው በተፈወሰ ጊዜ የጻፈው ጽሕፈት ይህ ነው፦

10እኔ፦ በሕይወት ዘመኔ መካከል ወደ ሲኦል በሮች እገባለሁ፤ የቀረው ዘመኔ ጐደለብኝ፡ አልሁ።

11ደግሞም፦ በሕያዋን ምድር እግዚአብሔርን አላይም፤ በዓለምም ከሚኖሩ ጋር ሰውን እንግዲህ አልመለከትም፡ አልሁ።

12ማደሪያዬ ተነቀለች፥ እንደ እረኛ ድንኳንም ከእኔ ዘንድ ተወገደች፤ ሕይወቴንም እንደ ሸማኔ ጠቀለልሁ፥ እርሱም ከመጠቅለያው ይቈርጠኛል፤ ከማለዳም ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ ታጠፋኛለህ።

13እስኪነጋ ድረስ ቈይቼ ነበር፤ እርሱ እንደ አንበሳ አጥንቴን ሁሉ ሰበረ፤ ከማለዳ ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ ታጠፋኛለህ።

14እንደ ጨረባና እንደ ሽመላ ተንጫጫሁ፥ እንደ ርግብም አጕረመረምሁ፤ ዓይኖቼ ወደ ላይ ከማየት ደከሙ። ጌታ ሆይ፥ ተጨንቄአለሁና መከታ ሁነኝ።

15ምን እላለሁ? እርሱ ተናግሮኛል፥ እርሱ ራሱም ይህን አድርጎአል፤ በዘመኔ ሁሉ ስለ ነፍሴ ምሬት ቀስ ብዬ እሄዳለሁ።

16ጌታ ሆይ፥ በዚህ ነገር ሰዎች በሕይወት ይኖራሉ፥ በዚህም ሁሉ የመንፈሴ ሕይወት ነው፤ አንተም ፈወስኸኝ ወደ ሕይወትም መለስኸኝ።

17እነሆ፥ ታላቅ ምሬት ለደኅንነቴ ሆነ፤ አንተም ነፍሴን ከጥፋት ጕድጓድ አዳንሃት፥ ኃጢአቴንም ሁሉ ወደ ኋላህ ጣልህ።

18ሲኦል አያመሰግንህምና፥ ሞትም አያከብርህምና፤ ወደ ጕድጓዱ የሚወርዱ እውነትህን ተስፋ አያደርጉም።

19እኔ ዛሬ አንደማደርግ ሕያዋን እነርሱ ያመሰግኑሃል፤ አባት ለልጆች እውነትህን ያስታውቃል።

20እግዚአብሔር ያድነኛል፤ ስለዚህ በዕድሜያችን ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት ቅኔዎችን አውታር ባለው ዕቃ እንዘምራለን።

21ኢሳይያስም፦ የበለስ ጥፍጥፍ አምጥተው በእባጩ ላይ ይለብጡት፥ እርሱም ይፈወሳል፡ ብሎ ነበር።

22ሕዝቅያስም፦ ወደ እግዚአብሔር ቤት እወጣ ዘንድ ምልክቱ ምንድር ነው? ብሎ ነበር።

ማብራሪያ

38:1-8 በበሽታችን ሳለን ስንጸልይ፣ እግዚአብሔር እዚህ ለሕዝቅያስ የላከውን ዓይነት መልስ ባይልክልንም እንኳን፣ ቢሆንም ግን፣ በመንፈሱ አማካኝነት ደስ ይበላችሁ ብሎ ቢያዘን፣ ኃጢአታችን ይቅር እንደተባለልን ቢያረጋግጥልን፣ እንዲሁም እንኖርም እንሞትም የእርሱ እንደምንሆን ቢያረጋግጥልን፣ በከንቱ አንጸልይም። 2ነገሥት 20:1-11 ተመልከት።

38:9-22. እዚህ ላይ የሕዝቅያስን ምስጋና እናገኛለን። በበሽታችን ወቅት የምንቀበላቸውን ምሕረቶች ማስታወስ ለእኛ መልካም ነገር ነው። ሕዝቅያስ የነበረበትን ሁኔታ በዝርዝር አስቀምጧል። በዚህ ላይ አጽንዖት ሰጥቷል፤ 'እግዚአብሔርን ከእንግዲህ ወዲህ አላይም' በማለት። ጻድቅ ሰው እግዚአብሔርን ከማገልገልና ከእርሱ ጋር ህብረት ከማድረግ ውጭ ለሌላ ዓላማ መኖር አይሻም። የአሁን መኖሪያችን እረኛ በጎጆው ውስጥ እንዳለ ነው፤ ደካማ፣ ትሑትና ቀዝቃዛ ማደሪያ ነው። እረኛም እንዳለው ሁሉ፣ በእኛም እንክብካቤ ሥር አደራ የተሰጠው ነገር አለ።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV In those days Hezekiah became ill and was at the point of death. The prophet Isaiah son of Amoz went to him and said, “… English BCV በቲ ዘመን እቱይ ሕዝቅያስ ንሞት ክሳዕ ዝበፅሕ ሓመመ። ነቢይ ኢሳይያስ ወዲ ኣሞፅ ከዓ ናብኡ መፂኡ፥ “እግዚኣብሄር ‘ክትመውት ኢኻ እምበር ብህይወት ኣይትነብርን ኢኻሞ፥ ቤትካ ኣመዓራሪ’ ይ… ትግርኛ GAZBIB Baras Hisqiyaas dhukkubsatee du'uu ga'ee ture; Isaayaas ilmi Amoz inni raajichi gara isaa dhaqee,“Ati in duuta malee hi… Afaan Oromoo BCV GIZ ወበውእት መዋዕል ደወየ ሕዝቂያስ ወበጽሐ ለሞት፤ ወመጽአ ኀቤሁ ኢሳይያስ ወልደ አሞጽ ነቢይ፤ ወይቤሎ፦ ከመዝ ይቤ እግዚአብሔር፦ ሥራዕ ቤተከ እስመ ትመውት ወኢተሐዩ። giz GAZGAZ Baras Hisqiyaas dhukkubsatee du'uu ga'ee ture; Isaayaas ilmi Amoz inni raajichi gara isaa dhaqee,“Ati in duuta malee hi… Afaan Oromoo BCV aksum በቲ ዘመን እቱይ ሕዝቅያስ ንሞት ክሳዕ ዝበፅሕ ሓመመ። ነቢይ ኢሳይያስ ወዲ ኣሞፅ ከዓ ናብኡ መፂኡ፥ “እግዚኣብሄር ‘ክትመውት ኢኻ እምበር ብህይወት ኣይትነብርን ኢኻሞ፥ ቤትካ ኣመዓራሪ’ ይ… ትግርኛ AMHNIV በዚያ ጊዜ ሕዝቅያስ ታመመ፤ ሞት አፋፍ ደረሰ፤ የአሞጽ ልጅ ነቢዩ ኢሳይያስም ወደ እርሱ መጥቶ፣ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ከሕመምህ አትድንም፤ ትሞታለህና ቤትህን አሰናዳ’ ” አለው። አማርኛ SWAHSUV Siku hizo Hezekia aliugua, akawa katika hatari ya kufa; na Isaya nabii, mwana wa Amozi, akaenda kwa mfalme, akamwambia,… Kiswahili