ትንቢተ ኢሳይያስ 31

AMHNIVአማርኛ9 ጥቅሶች2:12 አዳምጥ
አዳምጥ 2:12 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ወደ እስራኤል ቅዱስ ለማይመለከቱ፣ ከእግዚአብሔርም ርዳታን ለማይሹ፣ ነገር ግን፤ ለርዳታ ብለው ወደ ግብፅ ለሚወርዱ፣ በፈረሶች ለሚታመኑ፣ በሠረገሎቻቸው ብዛት፣ በፈረሶቻቸውም ታላቅ ብርታት ለሚመኩ ወዮላቸው!

2እርሱም ግን ጠቢብ ነው፤ ጥፋትን ያመጣል፤ ቃሉን አያጥፍም። በክፉ አድራጊዎች ቤት ላይ፣ በደለኞችንም በሚረዱ ላይ ይነሣል።

3ግብፃውያን ሰዎች እንጂ አምላክ አይደሉም፤ ፈረሶቻቸውም ሥጋ እንጂ መንፈስ አይደሉም፤ እግዚአብሔር እጁን ሲዘረጋ፣ ርዳታ ሰጪው ይሰናከላል፤ ተረጂውም ይወድቃል፤ ሁለቱም በአንድ ላይ ይጠፋሉ።

4እግዚአብሔር እንዲህ ብሎኛል፤ “አንበሳ ወይም የአንበሳ ደቦል የሰበረውን ይዞ ሲያገሣ፣ ብዙ እረኞች ተጠራርተው ሲመጡበት፣ ጩኸታቸው እንደማያስፈራው፣ በድምፃቸውም እንደማይታወክ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ በጽዮን ተራራና በከፍታዎቿ ላይ ለውጊያ እንዲሁ ይወርዳል።

5በዐናት ላይ እንደሚያንዣብቡ ወፎች፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን እንዲሁ ይጋርዳታል፤ ይከልላታል፤ ይታደጋታል፤ በላይዋ ያልፋል፤ ያድናታልም።”

6እናንተ እስራኤላውያን ሆይ፤ እጅግ ወዳ መፃችሁበት ወደ እርሱ ተመለሱ።

7በዚያን ቀን በኀጢአት የተሞላ እጃችሁ የሠራቸውን የወርቅና የብር ጣዖቶች ሁላችሁም ትጥላላችሁና።

8“አሦር የሰው ባልሆነ ሰይፍ ይወድቃል፤ የሥጋ ለባሽ ያልሆነም ሰይፍ ይበላዋል። ከሰይፍ ፊት ይሸሻል፤ ጐልማሶቹም የግዳጅ ሥራ ይሠራሉ።

9ጠንካራ ምሽጉ በሽብር ምክንያት ይወድቃል፤ መሪዎቹም የጦር ዐርማ ሲያዩ በድንጋጤ ይዋጣሉ” ይላል እሳቱ በጽዮን፣ ማንደጃውም በኢየሩሳሌም የሆነ እግዚአብሔር።

ማብራሪያ

31:1-5 እግዚአብሔር ከዐመፅ ሠራተኞች የሚፈለገውን እርዳታ ይቃወማል። ኃጢአተኞች ግልጽ በሆኑና በራሳቸው ግልጽ በሆኑ እውነቶች የሞኝነታቸውን ስህተት ሊረዱ ይችላሉ፤ ሊክዷቸው የማይችሏቸውን ነገር ግን የማያምኗቸውን። የእግዚአብሔርን ፍርዶች ማምለጥ አይቻልም፤ ክፋትም ኃጢአተኞችን ይከተላል። የሠራዊት ጌታ ለጽዮን ተራራ ሊዋጋ ይወርዳል። የይሁዳ ነገድ አንበሳ ቤተ ክርስቲያኑን ለመከላከል ይታያል። ወፎች ጫጩቶቻቸውን ለመጠበቅ በላያቸው እንደሚንዣብቡ ሁሉ፣ የሠራዊት ጌታም እንደዚያ ባለ ርኅራኄና ፍቅር ኢየሩሳሌምን ይከላከላል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG ስለ እርዳታ ወደ ግብፅ ለሚወርዱ በፈረሶችም ለሚደገፉ፥ ስለ ብዛታቸውም በሰረገሎች፥ እጅግ ብርቱዎችም ስለ ሆኑ በፈረሰኞች ለሚታመኑ፥ ወደ እስራኤልም ቅዱስ ለማይመለከቱ እግዚአብሔርንም ለማይ… አማርኛ ENGNIV Woe to those who go down to Egypt for help, who rely on horses, who trust in the multitude of their chariots and in the… English BCV ናብ ናይ እስራኤል ቅዱስ ዘይምልከቱ፥ ንእግዚኣብሄርውን ዘይደልዩ፥ ግና ሓገዝ ደልዮም ናብ ግብፂ ንዝወርዱ፥ በፍራስ ንዝእመኑ፥ ብብዝሒ ሰረገላታት የመናውን ብርቱዓት ስለ ዝኾኑ፥ ብጕልበት ፈ… ትግርኛ GAZBIB Warra, Gibxi biraa gargaarsa argachuudhaaf achitti gad bu'aniif, warra, fardeenitti irkataniif, warra, baay'ina konkola… Afaan Oromoo BCV GIZ አሌ ሎሙ ለእለ ይወርዱ ብሔረ ግብፅ ይርድእዎሙ ወይተአመኑ በአፍራሲሆሙ ወበሰረገላቲሆሙ እስመ ምሉእ አፍራሲሆሙ ወበዝኀ ፈድፋደ ወኢተወከሉ በቅዱሰ እስራኤል ወኢኀሠሥዎ ለእግዚአብሔር። giz GAZGAZ Warra, Gibxi biraa gargaarsa argachuudhaaf achitti gad bu'aniif, warra, fardeenitti irkataniif, warra, baay'ina konkola… Afaan Oromoo BCV aksum ናብ ናይ እስራኤል ቅዱስ ዘይምልከቱ፥ ንእግዚኣብሄርውን ዘይደልዩ፥ ግና ሓገዝ ደልዮም ናብ ግብፂ ንዝወርዱ፥ በፍራስ ንዝእመኑ፥ ብብዝሒ ሰረገላታት የመናውን ብርቱዓት ስለ ዝኾኑ፥ ብጕልበት ፈ… ትግርኛ SWAHSUV Ole wao watelemkao kwenda Misri wapate msaada, na kutegemea farasi; watumainio magari kwa kuwa ni mengi, na wapanda far… Kiswahili