ትንቢተ ኢሳይያስ 31

AMHEVGአማርኛ9 ጥቅሶች1:57 አዳምጥ
አዳምጥ 1:57 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ስለ እርዳታ ወደ ግብፅ ለሚወርዱ በፈረሶችም ለሚደገፉ፥ ስለ ብዛታቸውም በሰረገሎች፥ እጅግ ብርቱዎችም ስለ ሆኑ በፈረሰኞች ለሚታመኑ፥ ወደ እስራኤልም ቅዱስ ለማይመለከቱ እግዚአብሔርንም ለማይፈልጉ ወዮላቸው!

2እርሱ ግን ደግሞ ጠቢብ ነው፥ ክፉንም ነገር ያመጣል፥ ቃሉንም አይመልስም፥ በክፉም አድራጊዎች ቤት ላይ በደልንም በሚሠሩ ረዳት ላይ ይነሣል።

3ግብጻውያን ሰዎች እንጂ አምላክ አይደሉም፥ ፈረሶቻቸውም ሥጋ እንጂ መንፈስ አይደሉም፤ እግዚአብሔርም እጁን በዘረጋ ጊዜ፥ ረጂው ይሰናከላል ተረጂውም ይወድቃል፥ ሁሉም በአንድ ላይ ይጠፋሉ።

4እግዚአብሔርም እንዲህ ይለኛልና፦ አንበሳ ወይም የአንበሳ ደቦል በንጥቂያው ላይ ሲያገሳ፥ ብዙ እረኞች ቢከማቹበት ከቃላቸው እንደማይፈራ ከድምፃቸውም እንደማይዋረድ፥ እንዲሁ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በጽዮን ተራራና በኮረብታዋ ላይ ይዋጋ ዘንድ ይወርዳል።

5እንደሚበርር ወፍ እንዲሁ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን ይጋርዳታል፤ ይከልላታል፥ ይታደጋታል፥ አልፎም ያድናታል።

6እናንተ የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ አጥብቃችሁ ወደ ዐመፃችሁበት ተመለሱ።

7በዚያም ቀን እያንዳንዳቸው እጆቻቸው ለኃጢአት የሠሩላቸውን የብሩንና የወርቁን ጣዖቶቻቸውን ይጥላሉ።

8አሦርም የሰው ባልሆነ ሰይፍ ይወድቃል፥ የሰውም ያልሆነ ሰይፍ ይበላዋል፤ ከሰይፍም ይሸሻሉ ጐበዛዝቱም ገባሮች ይሆናሉ።

9አምባው ከፍርሃት የተነሣ ያልፋል መሳፍንቱም ከዓላማው የተነሣ ይደነግጣሉ፥ ይላል እሳቱ በጽዮን እቶኑም በኢየሩሳሌም የሆነ እግዚአብሔር።

ማብራሪያ

31:1-5 እግዚአብሔር ከዐመፅ ሠራተኞች የሚፈለገውን እርዳታ ይቃወማል። ኃጢአተኞች ግልጽ በሆኑና በራሳቸው ግልጽ በሆኑ እውነቶች የሞኝነታቸውን ስህተት ሊረዱ ይችላሉ፤ ሊክዷቸው የማይችሏቸውን ነገር ግን የማያምኗቸውን። የእግዚአብሔርን ፍርዶች ማምለጥ አይቻልም፤ ክፋትም ኃጢአተኞችን ይከተላል። የሠራዊት ጌታ ለጽዮን ተራራ ሊዋጋ ይወርዳል። የይሁዳ ነገድ አንበሳ ቤተ ክርስቲያኑን ለመከላከል ይታያል። ወፎች ጫጩቶቻቸውን ለመጠበቅ በላያቸው እንደሚንዣብቡ ሁሉ፣ የሠራዊት ጌታም እንደዚያ ባለ ርኅራኄና ፍቅር ኢየሩሳሌምን ይከላከላል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV Woe to those who go down to Egypt for help, who rely on horses, who trust in the multitude of their chariots and in the… English BCV ናብ ናይ እስራኤል ቅዱስ ዘይምልከቱ፥ ንእግዚኣብሄርውን ዘይደልዩ፥ ግና ሓገዝ ደልዮም ናብ ግብፂ ንዝወርዱ፥ በፍራስ ንዝእመኑ፥ ብብዝሒ ሰረገላታት የመናውን ብርቱዓት ስለ ዝኾኑ፥ ብጕልበት ፈ… ትግርኛ GAZBIB Warra, Gibxi biraa gargaarsa argachuudhaaf achitti gad bu'aniif, warra, fardeenitti irkataniif, warra, baay'ina konkola… Afaan Oromoo BCV GIZ አሌ ሎሙ ለእለ ይወርዱ ብሔረ ግብፅ ይርድእዎሙ ወይተአመኑ በአፍራሲሆሙ ወበሰረገላቲሆሙ እስመ ምሉእ አፍራሲሆሙ ወበዝኀ ፈድፋደ ወኢተወከሉ በቅዱሰ እስራኤል ወኢኀሠሥዎ ለእግዚአብሔር። giz GAZGAZ Warra, Gibxi biraa gargaarsa argachuudhaaf achitti gad bu'aniif, warra, fardeenitti irkataniif, warra, baay'ina konkola… Afaan Oromoo BCV aksum ናብ ናይ እስራኤል ቅዱስ ዘይምልከቱ፥ ንእግዚኣብሄርውን ዘይደልዩ፥ ግና ሓገዝ ደልዮም ናብ ግብፂ ንዝወርዱ፥ በፍራስ ንዝእመኑ፥ ብብዝሒ ሰረገላታት የመናውን ብርቱዓት ስለ ዝኾኑ፥ ብጕልበት ፈ… ትግርኛ AMHNIV ወደ እስራኤል ቅዱስ ለማይመለከቱ፣ ከእግዚአብሔርም ርዳታን ለማይሹ፣ ነገር ግን፤ ለርዳታ ብለው ወደ ግብፅ ለሚወርዱ፣ በፈረሶች ለሚታመኑ፣ በሠረገሎቻቸው ብዛት፣ በፈረሶቻቸውም ታላቅ ብርታት … አማርኛ SWAHSUV Ole wao watelemkao kwenda Misri wapate msaada, na kutegemea farasi; watumainio magari kwa kuwa ni mengi, na wapanda far… Kiswahili