ትንቢተ ኢሳይያስ 23

AMHEVGአማርኛ18 ጥቅሶች3:18 አዳምጥ
አዳምጥ 3:18 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ስለ ጢሮስ የተነገረ ሸክም። የተርሴስ መርከቦች ሆይ፥ አልቅሱ፤ ፈርሶአልና ቤት የለም፥ መግባትም የለም፤ ከኪቲም አገር ጀምሮ ተገልጦላቸዋል።

2እናንተ በደሴት የምትኖሩ በባሕርም የምትሻገሩ የሲዶና ነጋዴዎች ንግድ የሞሉባችሁ ሆይ፥ ጸጥ በሉ።

3የሺሖር ዘርና የዓባይ ወንዝ መከር በብዙ ውኆች ላይ ገቢዋ ነበረ፤ እርስዋም የአሕዛብ መናገጃ ነበረች።

4ሲዶና ሆይ፥ ባሕር፥ የባሕር ምሽግ፦ አላማጥሁም፥ አልወለድሁም፤ ጐበዛዝትንም አላሳደግሁም፥ ደናግልንም አላሳደግሁም፡ ብሎ ተናግሮአልና እፈሪ።

5ወሬዋ ወደ ግብፅ በደረሰ ጊዜ በጢሮስ ወሬ ምጥ ይይዛቸዋል።

6ወደ ተርሴስ ተሻገሩ፤ እናንተ በደሴት የምትኖሩ አልቅሱ።

7በቀድሞ ዘመን ተመሥርታ የነበረችው፥ በዚያም እንደ እንግዳ ሆና ትኖር ዘንድ እግሮችዋ ወደ ሩቅ ያፈለሱአት የደስታችሁ ከተማ ይህች ናትን?

8አክሊል ባስጫነች ከተማ በጢሮስ ላይ ይህን የወሰነ ማን ነው? ነጋዴዎችዋ አለቆች ናቸው፥ በእርስዋም የሚሸጡና የሚለውጡ የምድር ክቡራን ናቸው።

9የክብርን ሁሉ ትዕቢት ይሽር ዘንድ የምድርንም ክቡራን ሁሉ ያስንቅ ዘንድ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ወስኖታል።

10የተርሴስ ልጅ ሆይ፥ የሚከለክልሽ የለምና እንደ ዓባይ ወንዝ በአገርሽ ላይ ጐርፈሽ እለፊ።

11በባሕር ላይ እጁን ዘረጋ መንግሥታትንም አናወጠ፤ ምሽጎችዋንም ያጠፉ ዘንድ እግዚአብሔር ስለ ከነዓን አገር አዘዘ።

12እርሱም፦ አንቺ የተበደልሽ የሲዶና ድንግል ልጅ ሆይ፥ ከእንግዲህ ወዲህ ደስ አይበልሽ፤ ተነሥተሽ ወደ ኪቲም ተሻገሪ፥ በዚያም ደግሞ አታርፊም፥ አለ።

13እነሆ፥ የከለዳውያን አገር! ይህ ሕዝብ ሆኖ አይገኝም፤ አሦራውያን ለምድረ በዳ አራዊት ሰጥተውታል፤ ግንቦቻቸውን ሠሩ፥ አዳራሾችዋንም አፈረሱ፥ ባድማም አደረጓት።

14እናንተ የተርሴስ መርከቦች ሆይ፥ ምሽጋችሁ ፈርሶአልና ዋይ በሉ።

15በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፤ ጢሮስ እንደ አንድ ንጉሥ ዘመን ሰባ ዓመት ያህል የተረሳች ትሆናለች፤ ከሰባ ዓመት በኋላ ግን ለጢሮስ በጋለሞታ ዘፈን እንደሚሆን እንዲሁ ይሆናል።

16አንቺ የተረሳሽ ጋለሞታ ሆይ፥ መሰንቆ ያዢ በከተማ ላይም ዙሪ፤ መታሰቢያም ይሆንልሽ ዘንድ ዜማን አሳምሪ ዘፈንሽንም አብዢ።

17ከሰባ ዓመትም በኋላ እግዚአብሔር ጢሮስን ይጐበኛታል፥ ወደ ዋጋዋም ትምለሳለች፥ ደግሞም በምድር ፊት ላይ ከሆኑ ከዓለም መንግሥታት ሁሉ ጋር ትገለሙታለች።

18ንግድዋና ዋጋዋ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ይሆናል፤ ንግድዋም በልተው ይጠግቡ ዘንድ ማለፊያም ልብስ ይለብሱ ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት ለሚኖሩ ይሆናል እንጂ በዕቃ ቤትና በግምጃ ቤት ውስጥ አይከተትም።

ማብራሪያ

23:1-14 ጢሮስ የብሔራት ሁሉ የንግድ ማዕከል ነበረች። በደስታዋና በመዝናናትዋ የታወቀች ነበረች፤ ይህም እግዚአብሔር በአገልጋዮቹ በኩል የሰጣትን ማስጠንቀቂያዎች እንድትሰማ እንዳትፈልግ አደረጋት። ነጋዴዎቿ መሳፍንት ነበሩ፤ እንደ መሳፍንትም ይኖሩ ነበር። ጢሮስ ከጠፋችና ባድማ ከሆነች በኋላ፣ ነጋዴዎቿ ሊተዋት ይገባል። ለመዳን ሽሽ፤ ነገር ግን በአንድ ቦታ የማይመቻቸው በሌላም እንዲሁ ይሆናሉ፤ ምክንያቱም የእግዚአብሔር ፍርዶች ኃጢአተኞችን ሲያሳድዱ ያገኛቸዋል። ይህ ሁሉ ችግር ከወዴት ይመጣል? ሁሉን ከሚችለው ከአምላክ የመጣ ጥፋት ነው።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV An oracle concerning Tyre: Wail, O ships of Tarshish! For Tyre is destroyed and left without house or harbor. From the … English BCV ብዛዕባ ጢሮስ ዝተነግረ ፆር። ከተማ ጢሮስ ዓንያ እያ እሞ፥ ቤት የለን፤ ምእታው ድማ የለን እሞ፥ ኣትን መራኽብ ተርሴስ፥ ዋይ ዋይ በላ። ካብ ምድሪ ኪቲም ጀሚሩ ተገሊፁሎም እዩ። ትግርኛ GAZBIB Wanti mandara Xiiros irratti ta'uuf jiru kanatti fufee jira; markaboonni Tarshiish biyya Qophrosii utuu deebi'anii, Xii… Afaan Oromoo BCV GIZ ነገር ዘበእንተ ጢሮስ፤ ለየዐወይዋ አሕማረ ኬልቄዶኖስ እስመ ተሀጕለ ወኢይመጽኣ እንከ እምብሔረ ኬጤዎን ወያመጽእዎሙ ፄዋ። giz GAZGAZ Wanti mandara Xiiros irratti ta'uuf jiru kanatti fufee jira; markaboonni Tarshiish biyya Qophrosii utuu deebi'anii, Xii… Afaan Oromoo BCV aksum ብዛዕባ ጢሮስ ዝተነግረ ፆር። ከተማ ጢሮስ ዓንያ እያ እሞ፥ ቤት የለን፤ ምእታው ድማ የለን እሞ፥ ኣትን መራኽብ ተርሴስ፥ ዋይ ዋይ በላ። ካብ ምድሪ ኪቲም ጀሚሩ ተገሊፁሎም እዩ። ትግርኛ AMHNIV ስለ ጢሮስ የተነገረ ንግር፤ የተርሴስ መርከቦች ሆይ፤ ዋይ በሉ፤ ጢሮስ ተደምስሳለችና፤ ያለ ቤትና ያለ ወደብ ቀርታለች። ከቆጵሮስ ምድር፣ ዜናው ወጥቶላቸዋል። አማርኛ SWAHSUV Ufunuo juu ya Tiro. Toeni sauti za uchungu, enyi merikebu za Tarshishi, kwa maana umeharibika kabisa, hata hapana nyumb… Kiswahili