ትንቢተ ኢሳይያስ 15

AMHNIVአማርኛ9 ጥቅሶች1:49 አዳምጥ
አዳምጥ 1:49 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ስለ ሞዓብ የተነገረው ንግር ይህ ነው፤ የሞዓብ ዔር ፈራረሰች፤ በአንድ ሌሊትም ተደመሰሰች። የሞዓብ ቂር ፈራረሰች፣ በአንድ ሌሊት ተደመሰሰች።

2ዲቦን ወደ መቅደሱ ወጣ፤ ሊያለቅስም ወደ ኰረብታው ሄደ፤ ሞዓብ ስለ ናባው፣ ስለ ሜድባም ዋይታ ያሰማል፤ ራስ ሁሉ ተመድምዶአል፤ ጢምም ሁሉ ተላጭቶአል።

3በየመንገዱም ማቅ ይለብሳሉ፤ በየሰገነቱና በየአደባባዩ ሁሉም ያለቅሳሉ፤ እንባም ይራጫሉ።

4ሐሴቦንና ኤልያሊ ጮኹ፤ ድምፃቸው እስከ ያሀድ ድረስ ተሰማ፤ ስለዚህ የሞዓብ ጦረኞች ጮኹ፤ ልባቸውም ራደ።

5ልቤ ስለ ሞዓብ አለቀሰ፤ ስደተኞቿም እስከ ዞዓር፣ እስከ ዔግላት ሺሊሺያ ሸሹ፤ እንባቸውን እያፈሰሱ ወደ ሉሒት ወጡ፤ በሖሮናይም መንገድም፣ ስለ ጥፋታቸው ዋይ እያሉ ነጐዱ።

6የኔምሬ ውሆች ደርቀዋል፤ ሣሩ ጠውልጎአል፤ ቡቃያውም ጠፍቶአል፤ ለምለም ነገር አይታይም።

7ስለዚህ ያገኙትን ሀብት፣ ያከማቹትን ንብረት ከአኻያ ወንዝ ማዶ ተሸክመው ያሻግሩታል።

8ጩኸታቸው እስከ ሞዓብ ዳርቻ ድረስ ያስተጋባል፤ ዋይታቸው እስከ ኤግላይም፣ ሰቈቃቸውም እስከ ብኤርኢሊም ደረሰ።

9የዲሞን ወንዞች በደም ተሞልተዋል፤ በዲሞን ላይ ግን ከዚያ ነገር የበለጠ አመጣለሁ፤ ከሞዓብ በሚሸሹት፣ በምድሪቱም ላይ በሚቀሩት አንበሳ እሰድዳለሁ።

ማብራሪያ

15:1-9 በሞዓባውያን ላይ ሊመጡ የነበሩት መለኮታዊ ፍርዶች። – ይህ ትንቢት በሦስት ዓመት ውስጥ መፈጸሙ የነቢዩን ተልእኮና በሌሎቹ ትንቢቶቹ ሁሉ ላይ ያለውን እምነት ያረጋግጣል። ሞዓብን በተመለከተ አስቀድሞ የተነገረው፡ 1. ዋና ዋና ከተሞቻቸው በጠላት ድንገት እንደሚወረሩ ነው። ታላላቅና በጣም አስከፊ የሆኑ ለውጦች በጣም በአጭር ጊዜ ውስጥ ሊከሰቱ ይችላሉ። 2. ሞዓባውያን ለእርዳታ ወደ ጣዖቶቻቸው እንደሚመለሱ። አምላክ የለሽ ሰዎች፣ በመከራ ውስጥ ሲሆኑ፣ አጽናኝ የላቸውም። ነገር ግን የሚያስደነግጣቸው ነገር በእውነተኛ ሐዘንና በማመን ጸሎት ይቅር ባይ ወደሆነው ወደ አምላካችን እንዲቀርቡ የሚያደርጋቸው እምብዛም አይደ…

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6