ትንቢተ ኢሳይያስ 16

AMHEVGአማርኛ14 ጥቅሶች2:46 አዳምጥ
አዳምጥ 2:46 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1በምድርም ላይ ለሠለጠነው አለቃ የበግ ጠቦቶችን በምድረ በዳ ካለችው ከሴላ ወደ ጽዮን ሴት ልጅ ተራራ ስደዱ።

2እንደሚበርር ወፍ እንደ ተበተኑም ጫጩቶች እንዲሁ የሞዓብ ሴቶች ልጆች በአርኖን መሻገሪያዎች ይሆናሉ።

3ምክርን ምከሪ፥ ፍርድን አድርጊ፥ በቀትር ጊዜ ጥላሽን እንደ ሌሊት አድርጊ፤ የተሰደዱትን ሸሽጊ፥ የሸሹትን አትግለጪ።

4ከሞዓብ የተሰደዱት ከአንቺ ጋር ይቀመጡ፤ ከሚያጠፋቸው ፊት መጋረጃ ሁኛቸው። የሚያስጨንቁ አልቀዋል፥ ጥፋትም ቀርቶአል፤ ይጨቍኑ የነበሩ ከምድር ጠፍተዋል።

5ዙፋንም በምሕረት ይቀናል፥ በዚያም ላይ በዳዊት ድንኳን ፍርድን የሚሻ ጽድቅንም የሚያፈጥን ፈራጅ በእውነት ይቀመጣል

6ስለ ሞዓብ ትዕቢት እጅግ ስለ መታበዩ፥ ስለ ኵራቱና ስለ ትዕቢቱ ስለ ቍጣውም ሰምተናል፤ ትምሕክቱ ከንቱ ነው።

7ስለዚህ ሞዓብ ስለ ሞዓብ ዋይ ይላል፤ ሁሉም ዋይ ይላል፤ ስለ ቂርሐራሴት መሠራት በጥልቅ ኀዘን ታለቅሳላችሁ።

8የሐሴቦን እርሻዎችና የሴባማ ወይን ግንዶች አዝነዋል። የአሕዛብ አለቆች የሰባበሩአቸው ቅርንጫፎች እስከ ኢያዜር ደርሰው ወደ ምድረ በዳ ወጥተው ነበር፤ ቍጥቋጦቹም ተዘርግተው ባሕርን ተሻግረው ነበር።

9ስለዚህ በኢያዜር ልቅሶ ስለ ሴባማ ወይን ግንድ አለቅሳለሁ፤ ሐሴቦንና ኤልያሊ ሆይ፥ በዛፍሽ ፍሬና በወይንሽ መከር የጦር ጩኸት ወድቆአልና በእንባዬ አረካሻለሁ።

10ደስታና ሐሤትም ከፍሬያማው እርሻ ተወስዶአል፥ በወይኑም ቦታዎች ዝማሬና እልልታ የለም፤ በመጥመቂያም ወይን የሚረግጥ የለም፤ የረጋጮቹን እልልታ አጥፍቻለሁ።

11ስለዚህ ልቤ ስለ ሞዓብ አንጀቴም ስለ ቂርሔሬስ እንደ መሰንቆ ትጮኻለች።

12ሞዓብም መጥቶ በኮረብታ መስገጃ ላይ በደከመና ለጸሎት ወደ መቅደሱ በገባ ጊዜ አያሸንፍም።

13እግዚአብሔር በሞዓብ ላይ በድሮ ዘመን የተናገረው ነገር ይህ ነው።

14አሁን ግን እግዚአብሔር፦ በሦስት ዓመት ውስጥ እንደ ምንደኛ ዓመት የሞዓብ ክብርና የሕዝቡ ሁሉ ብዛት ይዋረዳል፥ ቅሬታውም እጅግ ያነሰና የተጠቃ ይሆናል፡ ይላል።

ማብራሪያ

16:1-5 አምላክ ኃጢአተኞች ጥፋትን ለመከላከል ምን ማድረግ እንዳለባቸው ይነግራቸዋል፤ እንደዚሁም ለሞዓብ ያደርጋል። ቀድሞ ለይሁዳ ለመክፈል የገቡትን ግብር ይላኩ። ይህንንም እንደ መልካም ምክር ይውሰዱት። ኃጢአታችሁን በጽድቅ ተው፤ ይህም ዕረፍታችሁን ሊያረዝም ይችላል። ይህ ደግሞ ለክርስቶስ የመገዛት ታላቁ የወንጌል ግዴታ ላይ ሊተገበር ይችላል። በግን ላኩለት፤ ካላችሁ ሁሉ ምርጡን፣ ራሳችሁን ሕያው መስዋዕት በማድረግ። ወደ እግዚአብሔር፣ ታላቁ ገዢ ወደ እርሱ ስትቀርቡ፣ በበጉ ስም፣ በእግዚአብሔር በግ ስም ቅረቡ። ለክርስቶስ የማይገዙ ሰዎች ከጎጆዋ እንደምትቅበዘበዝ ወፍ ይሆናሉ፤ በቀጣዩ አዳኝ ወፍ ትያዛለችና። የእግዚአብሔርን ፍርሃት ለመቀበል ፍቃደኛ ያልሆኑ ለሌላው ሁሉ ፍርሃት እንዲገዙ ይደረጋሉ። እርሱ ለእስራኤል ዘር ደግ እንዲሆኑ ይመክራቸዋል። በችግር ውስጥ ሲሆኑ ጸጋን ለማግኘት የሚጠብቁ፣ ችግር ውስጥ ላሉትም ጸጋን ማሳየት አለባቸው።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6