ትንቢተ ሆሴዕ 12

AMHNIVአማርኛ14 ጥቅሶች2:31 አዳምጥ
አዳምጥ 2:31 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ኤፍሬም የነፋስ እረኛ ነው፤ ቀኑን ሙሉ የምሥራቅን ነፋስ ይከተላል፤ ሐሰትንና ዐመፅን ያበዛል። ከአሦር ጋር ቃል ኪዳን ያደርጋል፤ የወይራ ዘይትንም ወደ ግብፅ ይልካል።

2እግዚአብሔር በይሁዳ ላይ የሚያቀርበው ክስ አለው፤ ያዕቆብን እንደ መንገዱ ይቀጣዋል፤ እንደ ሥራውም ይከፍለዋል።

3በማሕፀን ሳለ የወንድሙን ተረከዝ ያዘ፤ ሙሉ ሰውም ሲሆን ከአምላክ ጋር ታገለ።

4ከመልአኩም ጋር ታገለ፤ አሸነፈውም፤ በፊቱ ሞገስን ለማግኘት አልቅሶ ለመነው፣ እርሱንም በቤቴል አገኘው፤ በዚያም ከእርሱ ጋር ተነጋገረ፤

5እርሱም ሁሉን የሚገዛ አምላክ እግዚአብሔር፣ የሚታወቅበት ስሙም እግዚአብሔር ነው።

6ስለዚህ ወደ አምላክህ ተመለስ፤ ፍቅርንና ፍትሕን ጠብቅ፤ ዘወትርም በአምላክህ ታመን።

7ነጋዴው በሐሰተኛ ሚዛን ይሸጣል፤ ማጭበርበርንም ይወዳል።

8ኤፍሬም እንዲህ እያለ ይታበያል፤ “እኔ ባለጠጋ ነኝ፤ ሀብታምም ሆኛለሁ፤ ይህ ሁሉ ሀብት እያለኝ፣ ምንም ዐይነት በደል ወይም ኀጢአት አያገኙብኝም።”

9“ከግብፅ ምድር ያወጣኋችሁ፣ አምላካችሁ እግዚአብሔር እኔ ነኝ፤ በዓመት በዓላችሁ ቀን ታደርጉ እንደ ነበረው ሁሉ፣ እንደ ገና በድንኳኖች እንድትቀመጡ አደርጋችኋለሁ።

10ለነቢያት ተናገርሁ፤ ራእይንም አበዛሁላቸው፤ በእነርሱም በኩል በምሳሌ ተናገርሁ።

11ገለዓድ ክፉ ነው፤ ሕዝቡም ከንቱ ናቸው፤ ኮርማዎችን በጌልገላ ይሠዋሉን? መሠዊያዎቻቸው በታረሰ መሬት ላይ እንዳለ፣ የድንጋይ ክምር ይሆናሉ።

12ያዕቆብ ወደ ሶርያ ሸሸ፤ እስራኤል ሚስት ለማግኘት ሲል አገለገለ፤ ዋጋዋንም ለመክፈል በጎችን ጠበቀ።

13እግዚአብሔር በነቢይ አማካይነት እስራኤልን ከግብፅ አወጣ፤ በነቢይም በኩል ተንከባከበው።

14ኤፍሬም ግን ክፉኛ አስቈጣው፤ ጌታውም የደም አፍሳሽነቱን በደል በላዩ ላይ ያደርግበታል፤ ስለ ንቀቱም የሚገባውን ይከፍለዋል።

ማብራሪያ

12:1-6 ኤፍሬም ከእግዚአብሔር ጋር ጠላትነት ሲኖረው ከሰው በሚመጣ እርዳታ በከንቱ ተስፋ ይጠበባል። አይሁድም ከአገራቸው ምርት በተሰጠ ስጦታ ግብፃውያንን ከጎናቸው ለማድረግ በከንቱ አሰቡ። ይሁዳም ደግሞ ቅሬታ ቀርቦበታል። እግዚአብሔር የራሱን ሕዝብ ኃጢአት ያያልና በእርሱም ምክንያት ይጠይቃቸዋል። ያዕቆብ ያደረገውን እና እግዚአብሔር ለእርሱ ያደረገውን እንዲያስታውሱ ይነገራቸዋል። የእርሱ በእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ላይ የነበረው እምነት ፍርሃቶቹን ሲያሸንፍ፣ ያን ጊዜ በብርቱነቱ ከእግዚአብሔር ጋር ታገለና ቻለ። እርሱ ይሖዋ ነው፤ የነበረው፣ ያለው፣ የሚመጣውም እርሱ ነው። ለአንዱ የእግዚአብሔር መገለጥ የነበረው፣ ለብዙዎች፣ ለሁሉም ትውልዶች የእርሱ መታሰቢያ ነው። እንግዲያስ ከእግዚአብሔር የራቁት ወደ እርሱ ይመለሱ።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG ኤፍሬም ነፋስን ይበላል፥ የምሥራቅንም ነፋስ ይከተላል፤ ሁልጊዜም ሐሰትንና ተንኰልን ያበዛል፤ ከአሦር ጋር ቃል ኪዳን ያደርጋሉ፥ ወደ ግብፅም ዘይት ይወስዳሉ። አማርኛ ENGNIV Ephraim feeds on the wind; he pursues the east wind all day and multiplies lies and violence. He makes a treaty with As… English BCV ኤፍሬም ንፋስ ይምገብ፤ ደድሕሪ ንፋስ ምብራቕ ከዓ ይስዕብ። ኵሉ መዓልቲ ሓሰትን ዓመፅን የብዝሕ። ምስ ኣሶር ቃል ኪዳን ይኣትዉ፤ ናብ ግብፂ ድማ ዘይቲ ይወስዱ። ትግርኛ GAZBIB “Efreem qilleensaa wajjin in oola, guyyaa guutuus qilleensa gara ba'a-biiftuu duukaa in fiiga; soba, humnaan nama irrat… Afaan Oromoo BCV GIZ ኤፍሬምሰ ጋኔን እኩይ ዘይዴግን ክብረ ወኵሎ ኩንቶ ወሐሰተ አብዝኅ፤ ወተካየደ ኪዳነ ምስለ ፋርስ ወየሐውር ግብፀ ከመ ይምህርዎ። giz GAZGAZ “Efreem qilleensaa wajjin in oola, guyyaa guutuus qilleensa gara ba'a-biiftuu duukaa in fiiga; soba, humnaan nama irrat… Afaan Oromoo BCV aksum ኤፍሬም ንፋስ ይምገብ፤ ደድሕሪ ንፋስ ምብራቕ ከዓ ይስዕብ። ኵሉ መዓልቲ ሓሰትን ዓመፅን የብዝሕ። ምስ ኣሶር ቃል ኪዳን ይኣትዉ፤ ናብ ግብፂ ድማ ዘይቲ ይወስዱ። ትግርኛ SWAHSUV Efraimu hujilisha upepo, na kuandamana na upepo wa mashariki; haachi kuongeza uongo na uharibifu; nao wafanya agano na … Kiswahili